የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 11
  • በቀላሉ የሚገባ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በቀላሉ የሚገባ
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ተጠምቀው ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • “ለዘላለም በደስታ ኑር!” ተጠቅመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት—እንዴት?
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ‘ለማስተማር ጥበብህ’ ትኩረት ስጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህን ልብ ለመንካት ጣር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 11

ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ኢየሱስ በባሕር አቅራቢያ ሰዎችን ሲያስተምር። ሰማይ ላይ ወፎች ሲበርሩ እንዲሁም በአካባቢው የሜዳ አበቦች ይታያሉ።

ማቴ. 6:25-27

ምዕራፍ 11

በቀላሉ የሚገባ

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ [ይሁን]።”—1 ቆሮ. 14:9

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስ በባሕር አቅራቢያ ሰዎችን ሲያስተምር። ሰማይ ላይ ወፎች ሲበርሩ እንዲሁም በአካባቢው የሜዳ አበቦች ይታያሉ።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ፣ አባታችን እንደሚንከባከበን በምሳሌ አስረዳ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ማቴዎስ 6:25-27ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ኢየሱስ ይሖዋ የሚያደርግልንን እንክብካቤ በምሳሌ ያስረዳው እንዴት ነው?

  2. ለ. ኢየሱስ ስለ ወፎች ብዙ ነገር ቢያውቅም በየትኛው ቀላል ነጥብ ላይ አተኩሯል? ይህስ ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. ቀላል በሆነ መንገድ የምናስተምር ከሆነ ሰዎች ትምህርቱን ለማስታወስ አይቸገሩም፤ ልባቸውም ይነካል።

ኢየሱስን ምሰል

3. ብዙ አታውራ። ስለ አንድ ርዕስ የምታውቀውን ነገር ሁሉ ከማውራት ይልቅ ማጥኛ ጽሑፉ ውስጥ ባለው ሐሳብ ላይ አተኩር። የምታስጠናውን ሰው አንድ ጥያቄ ከጠየቅኸው በኋላ መልስ እስኪሰጥህ በትዕግሥት ጠብቀው። መልሱን ካላወቀው ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ከተናገረ፣ ተጨማሪ ጥያቄዎች ተጠቅመህ ጉዳዩን በደንብ እንዲያስብበት እርዳው። ዋናው ነጥብ ከገባው ወደ ቀጣዩ ነጥብ እለፍ።

4. አዳዲስ ትምህርቶችን ቀድሞ ከተማረው ነገር ጋር እንዲያዛምድ እርዳው። ለምሳሌ ስለ ትንሣኤ የምታጠኑበት ምዕራፍ ላይ ደርሳችኋል እንበል፤ የሞቱ ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ የተማረውን ነገር በአጭሩ በመከለስ መጀመር ትችላለህ።

5. ምሳሌዎችን በጥንቃቄ ምረጥ። አንድ ምሳሌ ከመጠቀምህ በፊት ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  1. ሀ. ‘ምሳሌው ያልተወሳሰበ ነው?’

  2. ለ. ‘የማስጠናው ሰው በቀላሉ ይረዳዋል?’

  3. ሐ. ‘ምሳሌውን ብቻ ሳይሆን ዋናውን ነጥብም ማስታወስ ይችላል?’

ተጨማሪ ጥቅሶች

ማቴ. 11:25፤ ዮሐ. 16:12፤ 1 ቆሮ. 2:1

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ