የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 2/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አረጋውያን እንደገና ወጣት የሚሆኑበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ይሖዋ ከሥቃዩ ገላገለው
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ለኢዮብ የተከፈለው ወሮታ የተስፋ ምንጭ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • እርማት በመቀበል ረገድ ምሳሌ የሚሆን ሰው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 2/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

◼ ኢዮብ 33:24 ለኢዮብ ከሞት የሚያድነው “ቤዛ” ስለመገኘቱ ይናገራል። ታዲያ ለኢዮብ ቤዛ የሚሆንለት ማነው?

ኢዮብ ሰብዓዊ ቤዛ አልተሰዋለትም። ሆኖም አምላክ የኢዮብን በደል ይቅር አለ ወይም ሸፈነለት።

ሰይጣን በኢዮብ ላይ ብዙ ችግር አድርሶበት ነበር። “ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው።” የኢዮብ ሁኔታ በጣም አስከፊ ስለነበረ ሚስቱ እንኳን “እግዚአብሔርን ስደብና ሙት” ብላው ነበር። ኢዮብም ቢሆን እንዲህ ያለው መከራ ከሚደርስበት ቢሞት እንደሚሻለው አስቦ ነበር።​—ኢዮብ 2:7-9፤ 3:11

ኢዮብ ሊሞት የተቃረበ በመሰለበት ጊዜ ኤሊሁ የኢዮብን አስጊ ሁኔታ አስተዋለና የሚከተለውን በማለት ኢዮብ የሚኖረውን ተስፋ ገለጸ፦ “ሥጋው እስከማይታይ ድረስ ይሰለስላል። . . . ነፍሱ ወደ ጉድጓዱ ሕይወቱም ወደሚገድሉአት ቀርባለች። የቀናውን መንገድ ለሰው ያስታውቀው ዘንድ ከሺህ አንድ ሆኖ የሚተረጉም መልአክ ቢገኝለት እየራራለት፦ ‘ቤዛ አግኝቼአለሁና ወደ ጉድጓድ እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል። ወደ ጉብዝናውም ዘመን ይመለሳል።”​—ኢዮብ 33:21-25

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ፍጹም ላልሆኑት የሰው ልጆች ተመጣጣኝ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠ እናውቃለን። የእርሱ መሥዋዕት አዳም ላጣው ነገር ማካካሻ ስለሚሆን ከኃጢአት ነፃነት ለማግኘት የሚያስፈልገውን ዋጋ አስገኝቶአል። (ሮሜ 5:12-19፤ 1 ጢሞቴዎስ 2:5, 6) ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ “ቤዛ” በሚለው ቃል የሚጠቀመው በዚህ መንገድ ብቻ አይደለም። በኢዮብ 33:24 ላይ የሚገኘው ቃል መሰረታዊ ትርጉሙ “መሸፈን” ማለት ነው። (ዘፀአት 25:17) አምላክ ከጥንት እሥራኤላውያን ጋር ግንኙነት በነበረው ጊዜ ኃጢአትን ለመሸፈን ወይም ለማስተሰረይ የሚያስችል ዝግጅት ነበረው። በአምላክና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያቃናና ለኃጢአት ሽፋን የሚሰጥ የመሥዋዕት ዝግጅት ነበረው።​—ዘፀዐት 29:36፤ ዘሌዋውያን 16:11, 15, 16፤ 17:11

ይሁን እንጂ ከዚህም ቀደም ብሎ አምላክ የምሥጋና መግለጫ ወይም የኃጢአት ይቅርታ መጠየቂያ ወይም የአምላክን ሞገስ ማግኛ የሆኑ መሥዋዕቶችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኖ ነበር። (ዘፍጥረት 4:3, 4፤ 8:20, 21፤ 12:7፤ 31:54) ኢዮብ ይህ ዓይነቱ መሥዋዕት ያለውን ጠቀሜታ ያውቅ ነበር። እንዲህ እናነባለን፦ “ኢዮብ ምናልባት ልጆቼ በድለው እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበረ። ኢዮብም ማልዶ ተነሣ፣ እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። እንዲሁም ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።” (ኢዮብ 1:5) ኢዮብ አምላክን ለማስደሰት የሚጣጣርና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ስለነበረ እርሱ የሚያቀርበው መሥዋዕት በአምላክ ፊት ዋጋ ነበረው።​—መዝሙር 32:1, 2፤ 51:17

ይሁን እንጂ ኢዮብ ቆየት ብሎ ሕይወቱን ሊያሳጣ የተቃረበ በሽታ ደረሰበት። በተጨማሪም ስለ ራሱ ጻድቅነት የተሳሳተ አመለካከት ነበረው። ስለዚህ እርማት ማግኘት ያስፈልገው ነበር። ይህንንም እርማት ኤሊሁ ሰጠው። (ኢዮብ 32:6፤ 33:8-12፤ 35:2-4) ኢዮብ ወደ ሞትና ወደ ጉድጓድ (ሲኦል ወይም የጋራ መቃብር) እስኪወርድ ድረስ በሐዘን ለመቆራመድ እንደማይገደድ ኤሊሁ ነገረው። ኢዮብ ንሥሐ ቢገባ “ቤዛ” ሊገኝለት ይችላል ብሎ ኤሊሁ ተናገረ።​—ኢዮብ 33:24-28

ኤሊሁ በዚያ የጥንት ዘመን ስለ “ቤዛ” ሲናገር ለኢዮብ ሲል የሚሞት ሰው እንደሚኖር መናገሩ እንደሆነ አድርገን ማሰብ የለብንም። በዚያ ዘመን እውነተኛ አምላኪዎች ያቀርቡ የነበረውን መሥዋዕት ስንመለከት ኤሊሁ ለኢዮብ የነገረው መሥዋዕት የእንስሳ መሥዋዕት ነበር ለማለት እንችላለን። አምላክም ኢዮብን ሲተቹ ለነበሩት ሶስት ጓደኞቹ “የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል” ብሎ ነበር። (ኢዮብ 42:8) ቤዛው ምንም ይሁን ምን ኤሊሁ ሊገልጽ የፈለገው ሐሣብ የኢዮብ ኃጢአት ሊሸፈንለት እንደሚችልና ከዚህም ዘላቂ ጥቅም ሊያገኝ እንደሚችል ነበር።

ኢዮብም ያደረገው ይህን ነበር። አመድና ትቢያ ነስንሶ ንሥሐ ገባ። ከዚያስ በኋላ ምን ሆነ? “[ይሖዋ (አዓት)] ምርኮውን መለሰለት። ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው። . . . ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፣ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።” ቤዛው ኢዮብን ከኃጢአት ነጻ እንዳላወጣው የታወቀ ስለነበረ ከጊዜ በኋላ ሞተ። ሆኖም ዕድሜው መራዘሙ ‘ሥጋው እንደ ሕጻን ሥጋ ለምልሞና ወደ ጉብዝናውም ዘመን ተመልሶ’ እንደነበረ ያረጋግጣል።​—ኢዮብ 33:25፤ 42:6, 10-17

ኢዮብ ከተከፈለለት መጠነኛ ቤዛ ይህን ያህል በረከት ማግኘቱ ያመኑ የሰው ልጆች በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለሚያገኙት የተትረፈረፈ በረከት ጥላ ይሆንልናል። በዚያ ጊዜ የኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ያስገኘልንን ሙሉ ጥቅም እናገኛለን። ኃጢአትና አለፍጽምና ያስከተለብን አደጋና ጉዳት ሁሉ ይወገድልናል። ኤሊሁ እንዳለው ‘የእልልታ ጩኸት’ የምናሰማበት በቂ ምክንያት ይኖረናል።​—ኢዮብ 33:26

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ