የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 4/15 ገጽ 28
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?
    ንቁ!—2002
  • የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 4/15 ገጽ 28

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ተግባራዊ ጥቅም አግኝተህባቸዋልን? ታዲያ ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች አማካኝነት ምን ያህሉን እንደምታስታውስ ራስህን ለምን አትፈትንም?

◻ ኢየሱስ የተወለደበት ነው የተባለውን ስፍራ እንደ ቅዱስ ነገር መመልከትን የሚጻረሩ ምን ሁኔታዎች አሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የተወለደበትን ስፍራ በትክክል አይጠቅስም። የማቴዎስና የሉቃስ ወንጌሎች የሚጠቅሱት በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነጥቦች ብቻ ነው። (ማቴዎስ 2:1, 5፤ ሉቃስ 2:4-7) በዮሐንስ 7:40-42 ላይ ያለው ምንባብ አጠቃላዩ ሕዝብ ኢየሱስ የተወለደበትን ስፍራ እንደማያውቅ ያሳያል። አንዳንዶች በገሊላ እንደተወለደ አድርገው ያስቡ ነበር። ኢየሱስም ቢሆን በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ስለ ትውልዱ ዝርዝር ሁኔታዎች እየዞረ አይናገርም ነበር።​—24-111 ገጽ 5

◻ አንድ ክርስቲያን እንደ ሕመም፣ የመንፈስ ጭንቀትና የገንዘብ ችግር ያሉ ፈተናዎች ሲያጋጥሙት ደስታውን ሳያጠፋ መኖር የሚችለው እንዴት ነው?

በዚህ ጊዜ የሚያስፈልገውን ማጽናኛና መመሪያ የአምላክ ቃል ይሰጣል። የመዝሙርን መጽሐፍ በማንበብ ወይም በቴፕ የተቀረጸውን በመስማት መንፈስን ማደስ ይቻላል። ዳዊት “ትካዜህን [በይሖዋ (አዓት)] ላይ ጣል እርሱም ይደግፍሃል” ሲል መክሮናል። (መዝሙር 55:22፤ 65:2) የይሖዋ ድርጅት በሚያወጣቸው ጽሑፎችና በጉባኤ ሽማግሌዎች አማካኝነት ከችግሮቻችን ጋር በምናደርገው ትግል እኛን ለመርዳት ምን ጊዜም ዝግጁ ሆኖ ቆሞአል።​—1/1 ገጽ 14-15

◻ ኢየሱስ ወደሚሰቀልበት ቦታ ሲሄድ “በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ በደረቀውስ እንዴት ይሆን?” ሲል የተናገረው ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? (ሉቃስ 23:31)

ኢየሱስ ዛፍ ሲል የአይሁድን ሕዝብ ማለቱ ነበር። ኢየሱስና በእርሱ ያመኑ የአይሁድ ቀሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ስለነበሩ አገሩ የሕይወት እርጥበት በትንሹ ነበረው። ነገር ግን እነርሱ ከሕዝቡ መካከል ከጠፉ የሚቀረው በመንፈሣዊ በድን የሆነ፤ ወይም የደረቀ ብሔራዊ ድርጅት ብቻ ይሆናል።​—1/15 ገጽ 9

◻ በማቴዎስ 5:8 ላይ የተጠቀሱት ልበ ንጹሓን ‘አምላክን የሚያዩት’ እንዴት ነው?

በአቋማቸው ጸንተው ለሚኖሩ ሰዎች የሚያደርጋቸውን ነገሮች በማየት እርሱን ያያሉ። (ከዘጸአት 33:20 እና ከኢዮብ 19:26፤ 42:5 ጋር አወዳድር) ይሁን እንጂ በማቴዎስ 5:8 ላይ የሚገኘው “ማየት” የሚለው ግሪክኛ ቃል “በአእምሮ ማየት፣ ማስተዋል፣ ማወቅ” የሚሉ ተጨማሪ ትርጉሞች አሉት። ኢየሱስ የአምላክን ባሕርያት በፍጽምና ደረጃ ስላንጸባረቀ የእርሱን ጠባዮች ጠለቅ ብሎ ማስተዋላቸው ልበ ንጹሐን ‘አምላክን ለማየት’ አስችሏቸዋል። (ዮሐንስ 14:7-9)​—1/15 ገጽ 16

◻ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ኢየሱስ ነው ብለን የምንደመድመው ለምንድን ነው?

የአምላክ ቃል የሚጠቅሰው ሊቀ መላእክት አንድ ብቻ ነው። ከሞት የተነሳውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማስመልከት ስለዚያ መልአክ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ራሱ በትእዛዝ፣ በመላእክትም አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና።” (1 ተሰሎንቄ 4:16) በይሁዳ 9 ላይ የዚህ የመላእክት አለቃ ስም ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን።​—2/1 ገጽ 17

◻ ለሌሎች ሰዎች አክብሮት የምናሳይባቸው አራት መስኮች ምንድን ናቸው?

ለፖለቲካ መሪዎች፣ ለአሠሪዎች፣ ለቤተሰብ አባሎችና በጉባኤ ላሉት አክብሮት ማሳየት አለብን።​—2/1 ገጽ 20-2

◻ ኢየሱስ ከመሞቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ያረጁ ወላጆች ላሉአቸው ምን ጥሩ ምሳሌ አሳይቷቸዋል?

ኢየሱስ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ በስቃይ ላይ እያለ ስለ እናቱ ሰብዓዊና መንፈሣዊ ደኅንነት አስቧል። የሚወደው ደቀ መዝሙር ዮሐንስ እንዲይዛት አደረገ። (ዮሐንስ 19:25-27)​—2/15 ገጽ 8

◻ በኢየሱስ ላይ ስቃይ መድረስ የነበረበት ለምንድን ነው?

ኢየሱስ መሰቃየቱ የአምላክ አገልጋዮች በአቋማቸው ስለመጽናታቸው ለተነሳው አከራካሪ ጥያቄ መልስ ሆኖአል። በተጨማሪም የደረሰበት መከራ ለሰው ልጆች አዛኝ ሊቀ ካህናት እንዲሆን አስችሎታል። (ዕብራውያን 4:15)​—2/15 ገጽ 14-15

◻ በዔደን ላይ የተደረገው አመጽ ምን አከራካሪ ጥያቄዎችን አስነሳ?

ሰው ያለ አምላክ እርዳታ ራሱን ሊያስተዳድርና ውጤቱ ሊሰምርለት ይችላልን? አምላክ ሰዎች የበላይ ገዥነቱን እንዲያከብሩ መጠየቁ ትክክለኛ አድራጎት ነበርን? ይኸኛውም ሌላ ጥያቄ ያስነሳል፦ ሰዎች የስስት ጥቅም እናገኛለን ብለው ሳያስቡ በነጻ ምርጫ ተጠቅመው አምላክን ለማገልገል ይመርጡ ይሆንን?​—3/1 ገጽ 6

◻ አንዳንዶች ከመታሰቢያው ቂጣና ወይን ጠጅ በስሕተት የተካፈሉት በምን ምክንያት ነው?

አንዳንድ ያልበሰሉ ግለሰቦች ስለ አምላክ ዓላማዎች ሚዛኑን የጠበቀ ዕውቀት የላቸውም። መቀባት “ለወደደ ወይም ለሮጠ [ሳይሆን] ከሚምር ከእግዚአብሔር” መሆኑን አያውቁና አልተቀበሉ ይሆናል። (ሮሜ 9:16) ወደ አዲሱ ቃል ኪዳን መግባትና ከክርስቶስ ጋር ወራሽ መሆን በግለሰቡ ፍላጎትና ውሳኔ ላይ የተመሠረተ አይደለም። ዋጋ ያለው የይሖዋ ምርጫ ነው። ያ ምርጫ በሚኖርበት ጊዜም መንፈስ ምሥክርነቱን ይሰጣል። (ሮሜ 8:16፤ 1 ቆሮንቶስ 12:18)​—3/15 ገጽ 21

◻ በሶፎንያስ 3:9 ላይ የተጠቀሰው “ንጹሕ ልሳን” ምንድን ነው?

ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ የሚናገረውን እውነት በትክክል መረዳት ማለት ነው።​—4/1 ገጽ 21-2

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ