እምነትን የሚያጠነክሩ አስደሳች ራእዮች
ከራእይ መጽሐፍ የተገኙ ቁምነገሮች
የይሖዋ ባሪያ ዮሐንስ የሚገኘው በትንሹ እስያ ማዶ በምትገኝ ጳጥሞስ (ፍጥሞ) በምትባል አንዲት ትንሽ ደሴት ነው። እዚያም በዕድሜ የሸመገለ ሐዋርያ አስደናቂ ነገሮችን ማለትም ምሳሌያዊና አብዛኛውን ጊዜም አስፈሪ የሆኑና ቁምነገር ያዘሉ ነገሮችን ይመለከታል። (እነዚህ ያያቸው ነገሮችም ተፈጻሚነት የሚኖራቸው) በጌታ ቀን ማለትም ኢየሱስ በ1914 በዙፋኑ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሺህ ዓመት ግዛቱ መጨረሻ መሆኑን ዮሐንስ ይነግረናል። ዮሐንስ በሰው ልጅ ታሪክ እጅግ ጨለማ በሆነው ሰዓት የሚፈጸሙ ሁኔታዎችን ቢመለከትም ስለ ክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ያየው ነገር እንዴት ግሩም ነበር! ታዛዥ የሰው ዘሮች ያኔ ምን ዓይነት በረከቶችን ያገኛሉ!
ዮሐንስ እነዚህን ራእዮች በመጽሐፍ ቅዱሱ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ መዝግቧቸዋል። በ96 እዘአ አካባቢ የተጻፈው ይህ ራእይ የትንቢት አምላክ በሆነው በይሖዋና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት ያጠነክርልናል።—ለዝርዝሩ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ቀርቧል! የሚለውን በመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትናንሽ መጻሕፍት ማኅበር የታተመውን መጽሐፍ ተመልከቱ።
ክርስቶስ ፍቅራዊ ምክር ይሰጣል
ከአምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከተላለፈው ራእይ መጀመሪያ ላይ የኢየሱስ ተባባሪ የመንግሥት ወራሾች ለሆኑት ሰባት ጉባኤዎች (የተጻፉ) ደብዳቤዎች ቀርበዋል። (1:1 እስከ 3:22) ባጠቃላይ ደብዳቤዎቹ ምስጋናዎችን ይሰጣሉ፤ ችግሮቹን ለይተው ያሳያሉ፤ እርማት ወይም ማበረታቻ ይሰጣሉ፤ እንዲሁም ከታማኝ ታዛዥነት የሚመጡ በረከቶችን ይጠቅሳሉ። የኤፌሶን ክርስቲያኖች ቢታገሡም በመጀመሪያ የነበራቸውን ፍቅር ትተዋል። በመንፈሳዊ ባለጸጋ የሆነው የሰምርኔስ ጉባኤ መከራ ታግሦ በታማኝነት እንዲኖር ተበረታቷል። ስደት የጴርጋሞንን ጉባኤ አላሸነፈውም። ይሁን እንጂ በኒቆላዊነት (በመናፍቅነት) ላይ እርምጃ አልወሰደም። የትያጥሮን ክርስቲያኖች (በመንፈሳዊ ሥራቸው) ተጨማሪ እንቅስቃሴ ቢያሳዩም እዚያው የኤልዛቤላዊ ተጽእኖ ነበረ። የሰርዴስ ጉባኤ በመንፈስ መንቃት ያስፈልገዋል። የፊልድልፍያው ያለውን አጥብቆ እንዲይዝ ተበረታቷል። እንዲሁም ለብ ያሉት የሎዶቂያ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ፈውስ ያስፈልጋቸዋል።
የወደፊቶቹን ሰማያዊ ነገሥታት እንደውም ሁሉንም ክርስቲያኖች የሚያሠለጥኑ እንዴት ያሉ መልካም ቃላት ናቸው! ለምሳሌ ከመካከላችን ለብ ያለ ሰው አለን? እንግዲያውስ እርምጃ ይውሰድ! በሞቃት ቀን (ጥም እንደሚቆርጥ) ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ሁን። እንደዚሁም ደግሞ ለይሖዋና ለአገልግሎቱ ትኩስ (የሚያቃጥል) ቅንዓት ማሳየት ጀምር።—ከማቴዎስ 11:28, 29 እና ከዮሐንስ 2:17 ጋር አወዳድሩ
በጉ መጽሐፉን ሲከፍት
ቀጥሎ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ዕጹብ ድንቅ በሆነ ግርማ ተቀምጦ ታየ። (4:1–5:14) በዙሪያው 24 ሽማግሌዎችና አራት እንስሳት አሉ። በሰባት ማህተም የታተመ መጽሐፍ በእጁ ይዟል። መጽሐፉን ማን ሊከፍት ይችል ይሆን? በጉ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽሐፉን ለመክፈት ብቁ ነው።
በጉ ከማህተሞቹ ስድስቱን ሲከፍት አስደናቂ ሁኔታዎች ይገለጣሉ (ይታያሉ) (6:1–7:17) የመጀመሪያው ማህተም ሲከፈት ክርስቶስ በነጭ ፈረስ ላይ ሆኖ ይታያል። አክሊል (ዘውድ) (1914) ይቀበልና ድል እየነሣ ይወጣል። ሌሎች ሦስት ማህተሞች ሲከፈቱ ሌሎች ፈረሰኞች በሰው ልጅ ላይ ጦርነት፣ ረሃብና ሞት ያመጣሉ። አምስተኛው ማህተም ሲከፈት ስለ ክርስቶስ በሰማዕታዊ ሞት የተገደሉ ሰዎች ደማቸው በቀል እንዲያገኝ ይጮኻሉ። ለእያንዳንዳቸውም ከንጉሣዊ መብቶች ጋር የማይሞቱ መንፈሳዊ ፍጡሮች ሆነው ከመነሣታቸው ጋር የሚዛመድ የጽድቅ አቋም የሚያመለክት ነጭ ልብስ ተሰጣቸው። (ከራእይ 3:5፤ 4:4 ጋር አወዳድሩ) ስድስተኛው ማህተም ሲከፈት የአምላክና የበጉ ቁጣ ቀን በምድር መንቀጥቀጥ ይገለጣል። ይሁን እንጂ ለጥፋት ፍርዱ ምሳሌ የሆኑት “አራት የምድር ነፋሳት” 144,000 የአምላክ ባሪያዎች እስኪታተሙ ድረስ እንዳይነፍሱ ታገዱ። እነሱ በአምላክ መንፈስ ከተቀቡና እንደመንፈሳዊ ልጆቹ ተቀባይነት ሲያገኙ የሰማያዊ ውርሻቸው ቅድሚያ ምልክት ማለትም ማህተም ወይም ማረጋገጫ (ማያዣ) ይቀበላሉ። ከተፈተኑ በኋላ ብቻ ነበር ማህተሙ ቋሚ የሚሆንላቸው። (ሮሜ 8:15-17፤ 2 ቆሮንቶስ 1:21, 22) ዮሐንስ በምድራዊ ገነት የዘላለም ሕይወት ተስፋ ያላቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተውጣጡ “ታላቅ መንጋ” ወይም እጅግ ብዙ ሕዝብ ሲመለከት ምን ያህል ተደንቆ መሆን አለበት! ተወዳዳሪ ከሌለው የሰው ልጅ ችግር “ከታላቁ መከራ” ይመጣሉ።
ሰባተኛው ማህተም ሲከፈት ምን አስፈሪ ድርጊቶች ይፈጸማሉ! (8:1–11:14) የቅዱሳን ጸሎት እንዲሰማ ግማሽ ሰዓት ያህል ዝምታ ከሆነ በኋላ እሳት ከመሠዊያው ወደ ምድር መወርወር ተከተለው። ከዚያም በሕዝበ ክርስትና ላይ የአምላክን መቅሰፍቶች በማወጅ ሰባት መላእክት መለከቶቻቸውን ሊነፉ ተዘጋጁ። መለከቶቹ እስከ ታላቁ መከራ ድረስ በፍጻሜ ዘመን ሁሉ ይነፋሉ። አራት መለከቶች መቅሰፍቶችን በምድር፣ በባሕር፣ በምንጮች፣ በጸሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ይጠራሉ። አምስተኛውን መለከት መንፋት ከ1919 ጀምሮ ጦርነት ሊያደርጉ የሚጐርፉትን ቅቡዓን ክርስቲያኖችን የሚያመለክቱ አንበጣዎችን ይጠራል። ስድስተኛው መለከት ሲነፋ በፈረሰኞች የሚደረግ ጥቃት ይደርሳል። የዚህ ትንቢት ፍጻሜም ቅቡዓኑ ከ1935 ወዲህ “በታላቅ መንጋ” አማካኝነት ተጨማሪ ጦር በማግኘት በሕዝበ ክርስትና የሃይማኖት መሪዎች ላይ የሚያሰቃይ የፍርድ መልእክትን ያውጃሉ።
ቀጥሎም ቅቡዓኑ በሕዝበ ክርስትና ላይ ከሚያውጁት የመለኮታዊ ፍርዶች መግለጫዎችን ከያዘው የአምላክ ቃል ክፍል ልክ ምግብ ያገኙ ያህል የሚሰጣቸው ሥራ መቀበላቸውን ለማመልከት ዮሐንስ አንድ ትንሽ መጽሐፍ ይበላል። ሐዋርያው የቤተ መቅደስ ዝግጅቱንና መለኰታዊ ደረጃዎቹ (ብቃቶቹ) ከቤተመቅደሱ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሁሉ የሚሞሉ መሆናቸውን በሚመለከት የይሖዋን ዓላማዎች እርግጠኛ ፍጻሜ የሚያመለክተውን የቤተመቅደሱ አደባባይ እንዲለካው ታዘዘ። ከዚያም የአምላክ ቅቡዓን “ሁለት ምሥክሮች” ማቅ ለብሰው ትንቢት ይናገራሉ፤ ይገደላሉም። ሆኖም እንደገና ይነሣሉ። ይህም የሚያመለክተው የስብከት ሥራቸው በጠላቶች እንደተገደለ ያህል ሆኖ የነበረበትንና ዳሩ ግን የይሖዋ አገልጋዮች ለአገልግሎታቸው በተአምር እንደገና ሕይወት ያገኙበትን ከ1918-19 ያለውን ጊዜ ነው።
መንግሥቱ ተወለደ!
የሰባተኛው መለከት መነፋት የመንግሥቱን መወለድ ያስታውቃል። (11:15–12:17) በሰማይ አንዲት ምሳሌያዊት ሴት (የይሖዋ አምላክ ሰማያዊ ድርጅት) ወንድ ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ የሆነለት የአምላክ መንግሥት) ትወለዳለች። ዘውዱን (ሰይጣን) ግን ሊውጠው (ሊበላው) ፈልጐ አልተሳካለትም። በ1914 የመንግሥቱን ልደት አስከትሎ የተደረገው ጦርነት ያበቃው ድል አድራጊው ሚካኤል (ኢየሱስ ክርስቶስ) ዘውዱንና የሱን መላእክት ወደ ምድር ወርውሮ በመጣል ነበር። በምድር ላይም ዘንዶው የሰማይቱ ሴት ዘሮች የሆኑትን ቅቡዓን ቀሪዎች መዋጋቱን ይቀጥላል።
በመቀጠልም ዮሐንስ አስከፊ መልክ ያለው አውሬ ይመለከታል። (13:1-18) ይህ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ የወጣው ከባሕር ማለትም ሰብዓዊ መንግሥት ከሚወጣበት ተነዋዋጭ ብዙሐን የሰው ልጅ መሃል ነው። (ከዳንኤል 7:2-8፤ 8:3-8, 20-25 ጋር አወዳድር) የዚህ ምሳሌያዊ ፍጡር የሥልጣን ምንጭ ምንድነው? ከዘንዶው ከሰይጣን በቀር ማንም ሊሆን አይችልም! እስቲ አስበው! ለዚሁ ፖለቲካዊ ግብ ዕዳ ሁለት ቀንድ ያለው አውሬ (የአንግሎ አሜሪካ ኃያል መንግሥት) አሁን የተባበሩት መንግሥታት ተብሎ የሚጠራ “ምስል” ሲያደርግለት ይታያል። ብዙዎችም የሚሠሩአቸውን ነገሮች እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሠሩና ሕይወታቸውን እንዲመራ በመፍቀድ እንዲያመልኩት ይገደዳሉ።
የይሖዋ አገልጋዮች እርምጃ ይወስዳሉ!
ሰባቱ የአምላክ ቁጣ ፅዋዎች ሲፈሱ የተለያዩ የአምላክ አገልጋዮች ሲሠሩ ይታያሉ። (14:1–16:21) አዳምጡ! በሰማያዊው የጽዮን ተራራ ላይ 144,000ዎቹ አዲስ የሆነ ቅኔ (ዝማሬ) ሲዘምሩ ይሰማል። አንድ በሰማይ መካከል የሚበር መልአክ ለምድር ነዋሪዎች ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ይዟል። ይህ ምን ያመለክታል? የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥቱን መልእክት በሚያውጁበት ጊዜ መላእክታዊ እርዳታ እንደሚያገኙ ያመለክታል።
ዮሐንስ የአምላክ ቁጣ ወይን መጥመቂያ በሚረግጥበት ጊዜ የምድር ወይን ሲመረትና መላው ብሔራት ሲጨፈለቁ ሲመለከት እጅግ ተገርሞ መሆን አለበት። (ከኢሳይያስ 63:3-6፤ ኢዩኤል 3:12-14 ጋር አወዳድር) ቀጥሎም በይሖዋ ትዕዛዝ ሰባት መላእክት ሰባቱን የመለኰታዊ ቁጣ ጽዋዎች ያፈሳሉ። መሬት፣ ባሕርና የንጹሕ ውሃ ምንጮች፣ እንዲሁም ፀሐይ፣ የአውሬው ዙፋንና የኤፍራጥስ ወንዝ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ጽዋዎች መፍሰስ ጉዳት የሚደርስባቸው አጋንንታዊ ፕሮፖጋንዳ (ሰብዓውያን) መንግሥታት ወደ አምላክ የአርማጌዶን ጦርነት እየሰበሰባቸው እንዳለ ሲያስተውል ዮሐንስ ምን ያህል ተደንቆ እንደነበረ እስቲ አስብ! ሰባተኛው ጽዋ በአየር ላይ ሲፈስ ውጤቶቹ አውዳሚ ናቸው።
ሁለት ምሳሌያዊ ሴቶች
ዮሐንስ የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የሆነችውን የታላቂቱ ባቢሎንን ፍጻሜ ለመመስከር በመብቃቱና ጥፋቷን ተከትለው የሚመጡ አስደሳች ሁኔታዎችን በመመልከቱ በደስታ ፈንድቆ እንደነበረ አያጠራጥርም። (17:1–19:10) በቅዱሳን ደም ሰክራና አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ያሉትን አውሬ (የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማህበርንና የሱን ተተኪ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) ተፈናጣ ትታያለች። ዋ፣ ቀንዶቹ በሷ ላይ ሲዞሩ ግን እንዴት ዓይነት ውድመት ያጋጥማታል!
ሰማያዊ ድምጾች ስለታላቂቱ ባቢሎን ጥፋት ያህን ሲያመሰግኑ ይሰማሉ። የበጉንና የሱን ሙሽራ ማለትም ትንሣኤ ያገኙት ቅቡዓንን ጋብቻ የሚያስተጋባው ምን ዓይነት ነጎድጓዳማ ምሥጋና ነው!
ክርስቶስ ድል ሲያደርግና ሲገዛ
ቀጥሎ ዮሐንስ የነገሥታቱ ንጉሥ የሰይጣንን የነገሮች ሥርዓት ለማጥፋት ሰማያዊ ሠራዊቶችን ሲመራ ይመለከታል። (19:11-21) አዎ “የእግዚአብሔር ቃል” የሆነው ኢየሱስ በአሕዛብ ላይ ጦርነት ያነሣል። ሐዋርያው አውሬው (የሰይጣን ፖለቲካዊ ድርጅት) እና ሐሰተኛው ነቢይ (የአንግሎ አሜሪካን የዓለም ኃይል) የፍጽምና ዘላለማዊ ጥፋት ምሳሌ በሆነው “የእሳት ባሕር” ሲጣሉ ይመለከታል።
ቀጥሎስ? ዮሐንስ ሰይጣን ወደ ጥልቁ ሲጣል (ሲታሠር) ይመለከታል። ከዚያም የሚቀጥለው ኢየሱስና ከሙታን የተነሱት ተባባሪ ነገሥታቱ በሰው ልጆች ላይ የሚፈርዱበትና ታዛዥ የሆኑትን ወደ ሰብዓዊ ፍጽምና የሚያደርሱበት የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ቅድመ እይታ ነው! (20:1-10) ከዚያ በኋላ ጊዜው የመጨረሻው ፈተና ጊዜ ነው። ከጥልቁ የተለቀቀው ሰይጣን ፍጹም የተደረጉትን የሰው ልጆች ሊያስት ይጀምራል። ይሁን እንጂ የሁሉንም በአምላክ ላይ ያመጹ አጋንንታዊና ሰብዓዊ አመጸኞች ሥራ (በመጪው) ጥፋት ያከትማል።
ዮሐንስ በጊዜው አኳያ ወደኋላ ተመልሰው በሞት በሐዴስ (የሰው ልጆች የጋራ መቃብር) እና በባሕር የነበሩት ሁሉ ተነሥተው በአምላክ ፊት ሲፈርዱ ሲመለከት እንዴት ተመስጦ መሆን አለበት! (20:11-15) ሞት ሐዴስ ከእንግዲህ ማንንም ተጠቂ (ሰው) ላይወስድ ወደ እሳት ባሕር ሲጣል ቅኖች ምን ዓይነት እፎይታ ያገኛሉ!
የዮሐንስ ራእይ ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ አዲስ ኢየሩሳሌምን ያመለክታል። (21:1–22:21) ያች መንግሥታዊ ከተማ ከሰማይ ወርዳ ለአሕዛብ ብርሃንን ታመጣለች ከአዲሲቱ ኢየሩሳሌም መካከል በውስጧ አቋርጦ የሚፈስሰው “የሕይወት ውሃ ወንዝ” የሚያመለክተው ቅዱስ ጽሑፋዊውን እውነትና ታዛዥ የሰው ልጆችን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳንና የዘላለምን ሕይወት ለመስጠት በኢየሱስ መስዋዕት ላይ የተመሠረተውን ማንኛውንም ሌላ ከአምላክ የተሰጠ ዝግጅትን ነው። (ዮሐንስ 1:29፤ 17:3፤ 1 ዮሐንስ 2:1, 2) ዮሐንስ በሁለቱም የወንዙ ዳርቻዎች ይሖዋ ለታዛዥ የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት ለመስጠት ያለውን ዝግጅት በከፊል የሚያመለክቱ ፈዋሽ ቅጠሎች ያሏቸው ዛፎችን ያመለክታል። ከአምላክና ከክርስቶስ የተሰጡ የማጠቃለያ (መደምደሚያ) መልእክቶች ከጥሪ ወይም ከግብዣ ጋር ይተላለፋሉ። መንፈሱና ሙሽራይቱ የተጠማ ሁሉ መጥቶ የሕይወትን ውሃ በነፃ እንዲወስድ ሲጋበዙ መስማት እንዴት ግሩም ነው! የራእይን የመዝጊያ ቃላት ስናነብ “አሜን፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” ካለው የዮሐንስ የጋለ ስሜት ካለበት ድምጽ ጋር እንደምንካፈል።
[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ ሥዕል/ሣጥን]
ነቅታችሁ ኑሩ፦ ስለ አምላክ የአርማጌዶን ጦርነት ከተነገሩት የትንቢት ቃላት መካከል እንዲህ ተብሏል፦ “እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ። እራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” (ራእይ 16:15) ይህ የተነገረው በኢየሩሳሌም የነበረውን ቤተ መቅደሱ የነበረበትን ተራራ የሚጠብቀውን ተቆጣጣሪ ወይም ሹም ተግባሮች በመጥቀስ ሊሆን ይችላል። በጥበቃዎቹ ወቅት ሌዋውያን ዘበኞች በመደበኛ ቦታቸው ነቅተው መሆናቸውን ወይም መተኛታቸውን ለማየት በቤተ መቅደሱ ይዘዋወራል። ተኝቶ የተገኘ ሌዋዊ በበትር ይመታል። መጐናጸፊያዎቹም እንደ አሳፋሪ መቀጫ ይቃጠላሉ። አርማጌዶን በጣም በቀረበበት ባሁኑ ጊዜ “የንጉሣዊው ክህነት” ቅቡዓን ቀሪዎች ወይም “መንፈሳዊ ቤት” በመንፈስ ንቁ ሆነው ለመኖር ቆርጠዋል። ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ባልንጀሮቻቸው “እጅግ ብዙ ሰዎች” እነሱም ለአምላክ በቤተ መቅደሱ ቅዱስ አገልግሎት እያቀረቡ ስላሉ በመንፈስ ነቅተው ለመኖር መቁረጥ አለባቸው። (ራእይ 7:9-17) በተለይ ደግሞ ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች በጉባኤዎች ውስጥ መጥፎ ሁኔታዎች እንዳያድጉ ነቅተው ይጠብቃሉ። በመንፈሳዊ ቤተ መቅደሱ የሚያመልኩት ሁሉም ታማኝ አምላኪዎች ነቅተው ስለሚኖሩም በይሖዋ ምስክርነታቸው የሚያቀርቡትን የተከበረ አገልግሎት የሚያመለክተውን “ልብሳቸውን” (መጐናጸፊያቸውን) ይጠብቃሉ።