የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 9/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • የሙሴ ሕግ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
  • የክርስቶስ ሕግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • በአሥሩ ትእዛዛት ሥር ነንን?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 9/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

◼ሐዋርያው ጳውሎስ በሮም 7:19 ላይ እንደገለጸው እርሱ ሊያደርገው ያልቻለው “በጎ ነገር” ምን ነበር?

በመሠረቱ ጳውሎስ እዚህ ላይ የጠቀሰው በሙሴ ሕግ ውስጥ የተጠቀሱትን መልካም ነገሮች ሁሉ ለመፈጸም አለመቻሉን ነው። በአለፍጽምናና በኃጢአት ምክንያት ለጳውሎስም ሆነ፣ ለሌሎች (ለእኛም ጭምር) ይህን ማድረጉ የማይቻል ነው። ይሁን እንጂ ተስፋ መቁረጡ አስፈላጊ አይደለም። የክርስቶስ መስዋዕት ከአምላክ ይቅርታን ለማግኘትና በእርሱ ፊት ጥሩ አቋም ለመያዝ መንገድ ከፍቷል።

ሮሜ 7:19 እንዲህ ይላል፦ “የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም።” በጥቅሱ ዙሪያ ያለው አሳብ ጳውሎስ እዚህ ላይ “በጎውን” ሲል በአንደኛ ደረጃ እየተናገረ ያለው በሕጉ ላይ ከተገለጸው አንፃር መሆኑን ያሳያል። በቁጥር 7 ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትም ባላወቅሁም ነበርና።” አዎን፣ ሕጉን ማንም ሙሉ በሙሉ ሊፈጽመው ስላልቻለ ሁሉም ሰዎች ኃጢአተኞች መሆናቸውን ግልጽ አደረገ።

ጳውሎስ ቀጥሎ “ድሮ እኔም ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ” በማለት ጠቀሰ። ይህ የሆነው መቼ ነበር? ይሖዋ ሕጉን ከመስጠቱ በፊት በአብርሃም ወገብ በነበረበት ጊዜ ነበር። (ሮሜ 7:9፤ ከዕብራውያን 7:9, 10 ጋር አወዳድር) አብርሃም ፍጽምና የሌለው ሰው ቢሆንም እንኳ በዚያን ጊዜ ሕጉ ገና አልተሰጠም ነበር፤ ስለዚህ በዛ ያላ ቁጥር ያላቸውን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ባለመቻሉ ምክንያት ኃጢአተኛ ነህ የሚል ማሳሰቢያ አልተሰጠውም። ታዲያ ይህ ሲባል ሕጉ ከተሰጠና የሰውን አለፍጽምና ካሳየ በኋላ መጥፎ ውጤቶችን አስከተለ ማለት ነውን? አይደለም። ጳውሎስ ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት።”​—ሮሜ 7:12

ጳውሎስ ሕጉን “ቅዱስ” እና “በጎም” ናት ብሎ እንደገለጸ ልብ በሉ። በሚቀጥሉት ቁጥሮች ላይ “በጎ የሆነው” ማለትም ሕጉ እርሱ ኃጢአተኛ መሆኑንና ይህም ኃጢአት ሞት የሚገባው ሰው እንዳደረገው ገልጿል። ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጻፈ፦ “የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም። የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፣ በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጂ።”​—ሮሜ 7:13-20

በዚህ ጥቅስ ዙሪያ ባለው ሐሳብ ላይ ጳውሎስ የሚናገረው በአጠቃላይ ስለ ጥሩነት ወይም የደግነት ሥራዎችን ስለ መሥራት አይደለም። (ከሥራ 9:36፤ ከሮሜ 13:3 ጋር አወዳድር) እርሱ በተለይ እየጠቀሰ ያለው ከበጎው የአምላክ ሕግ ጋር የሚስማሙትን ነገሮች ስለማድረግ (ወይም ስላለማድረግ) ነው። እርሱ ቀደም ሲል የአይሁድን ሃይማኖት በቅንዓት ይከተል ስለነበር ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር “ያለ ነቀፋ” ነበር። ይሁን እንጂ በአእምሮው ለዚህ በጎ ሕግ ትጉሕ ባሪያ የነበረ ቢሆንም ከሕጉ ጋር ሙሉ በሙሉ ተስማምቶ አልነበረም። (ፊልጵስዩስ 3:4-6) ሕጉ የአምላክን ፍጹም የአቋም ደረጃዎች ያንጸባርቃል። ለሐዋርያውም በሥጋው እርሱ ለኃጢአት ሕግ ባሪያ እንደሆነና በዚህም ምክንያት ሞት እንደሚገባው አሳይቶታል። ይሁን እንጂ ጳውሎስ እንደ ጻድቅ ሊቆጠር ለቻለበት ማለትም ከኃጢአትና ካስከተለው ተገቢ ውጤት ይኸውም ከሞት ፍርድ ለዳነበት የክርስቶስ መስዋዕት አመስጋኝ ሊሆን ይችል ነበር።​—ሮሜ 7:25

የሙሴ ሕግ በመከራው እንጨት ላይ ስለተጠረቀ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች በሙሴ ሕግ ሥር አይደሉም። (ሮሜ 7:4-6፤ ቆላስይስ 2:14) ሆኖም ይህ ልንረሳው የሚያስፈልግ ሸክም የሆነ ሕግ እንዳልነበረ ብናውቅ ጥሩ ነው። በመሠረቱ ሕጉ በጎ ወይም ጥሩ ነበር። ስለዚህ ሕጉን የያዙትን መጻሕፍት የምናነብበትና ከእስራኤላውያን ምን ይጠይቅባቸው እንደነበር የምናጠናበት ምክንያት አለን። በመላዋ ምድር ላይ የሚገኙ የይሖዋ ምስክሮች በቅርቡ ሣምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራማቸውን ሲያደርጉ ይህን ያጠኑታል።

ሕጉን ስናነብ በተለያዩት ድንጋጌዎቹ ውስጥ ጎልተው የተገለጹትን መሠረታዊ ሥርዓቶችና የአምላክ ሕዝብ እነዚህን ጥሩ ትእዛዞች ለመከተል ሲሞክሩ ያገኙአቸውን ጥቅሞች ወደኋላ መለስ እያልን ብናስብባቸው ጥሩ ነው። እንዲሁም እኛ ፍጽምና የጎደለን በመሆናችን ከአምላክ ቃል የተማርነውን በጎ ነገር ሁሉ አሟልተን ለመከተል እንደማንችል መገንዘብ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ከኃጢአት ሕግ ጋር እየታገልን ክርስቶስ ባቀረበልን መስዋእት በመጠቀም ለመዳን እንደምንችል ባለን ተስፋ ልንደሰት እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ