የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 2/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • አምላክ “ልዕልት” ብሎ ጠርቷታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • አብርሃም እና ሣራ—እምነታቸውን መኮረጅ ትችላለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • በመጨረሻ ልጅ ወለዱ!
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 2/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ዘፍጥረት 12:19 በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ እንደሚገልጸው ፈርዖን የአብርሃምን ሚስት ሣራን አግብቷት ነበር?

አላገባትም። ፈርዖን ሣራን ሚስቱ አድርጎ እንዳይወስድ ተከልክሎአል። ስለዚህ የሣራ ክብርና ንጽሕና አልተደፈረም።

በዙሪያው ያሉትን ሐሳቦች መመልከት ይህንን ለመረዳት ይረዳናል። አብርሃም (አብራም) በግብጽ ጊዜያዊ ጥገኝነት እንዲፈልግ ያስገደደው ረሃብ ነበር። እዚያም ውብ በሆነችው ሚስቱ በሣራ ምክንያት ሕይወቱ አደጋ እንዳይደርስበት ፈራ። አብርሃም ገና ከሣራ ልጅ አልወለደም ነበርና የምድር ነገዶች ሁሉ የሚባረኩበት የዘር መሥመር እሱ ከሞተ ሊቋረጥ ነው። (ዘፍጥረት 12:1-3) ስለዚህ አብርሃም ሣራን እህቱ ነኝ እንድትል ነገራት። በእርግጥም ግማሽ እህቱ ነበረች።—ዘፍጥረት 12:10-13፤ 20:12

ፍርሃቱ መሠረት የሌለው አልነበረም። ኦገስት ኖቤል የተባሉ ምሁር “አብርሃም በግብጽ ምድር ሳለ እንዳይገደል ሣራ እህቱ ነኝ እንድትል ጠይቋታል። ባል ያላት ሴት መሆኗ ከታወቀ አንድ ግብጻዊ እሷን ሊያገኝ የሚችለው ባሏን በመግደል ነበር። እንደ እህቱ ከታየች ግን ሠላማዊ በሆነ መንገድ ከወንድሟ አስፈቅዶ መውሰድ ይቻል ነበር” በማለት ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የግብጽ መሳፍንት ፈርዖን ሣራን እንዲያገባት ከአብርሃም ጋር አልተደራደሩም። ዝም ብለው ብቻ ውቢቷን ሣራን ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዷት። የግብጹ መሪም ወንድሟ ነው ለተባለው ለአብርሃም ስጦታ ሰጠው። ከዚህ በኋላ ግን ይሖዋ የፈርዖንን ቤተሰብ በመቅሰፍት መታ። በአንድ ያልተገለጸ መንገድ እውነተኛው ጉዳይ ለፈርኦን በተገለጸለት ጊዜ ለአብርሃም “ለምን እህቴ ናት አልህ? እኔ ሚስት ላደርጋት ወስጃት ነበር። አሁንም ሚስትህ እነኋት ይዘሃት ሂድ” አለው።—ዘፍጥረት 12:14-19

ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብልና ሌሎች ትርጉሞች ሚስቴ አድርጌ ወስጃት ነበር በማለት ወይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም ባለው ሌላ ቃል ተርጉመውታል። አተረጓጎሙ በራሱ ስህተት ያለበት ባይሆንም ፈርዖን ሣራን እንዳገባት ወይም ጋብቻው ያለቀለት የተፈጸመ ጉዳይ መስሎ ሊታይ ይችላል። በዘፍጥረት 12:19 ላይ “መውሰድ” ተብሎ የተተረጐመው የዕብራይስጥ ግሥ ድርጊቱ ያልተፈጸመ ወይም ያልተሟላ ሁኔታን የሚያሳይ ነው። አዲሲቱ ዓለም ትርጉም ይህን የዕብራይስጥ ግሥ የግሱን ሁኔታ በግልጽ በሚያንጸባርቅና በዙሪያው ካለው ሐሳብ ጋር በሚስማማ ሁኔታ “ሚስቴ አድርጌ ልወስዳት ነበር” በማለት ተርጉሞታል።a ፈርዖን ሣራ ሚስቱ እንድትሆን “ሊወስዳት” የነበረ ቢሆንም አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም የጋብቻ ሥርዓት ገና አላሟላም ነበር።

አብርሃም በዚህ ጉዳይ በወሰደው አቋም ምክንያት ብዙ ጊዜ ሲወቀስ ቆይቷል። ይሁን እንጂ እርምጃ የወሰደው ተስፋ ለተገባው ዘርና ለመላው የሰው ዘር ጥቅም ሲል ነበር።—ዘፍጥረት 3:15፤ 22:17, 18፤ ገላትያ 3:16

በጣም አደገኛ ሊሆን በሚችል ተመሳሳይ ወቅትም ይስሐቅ ሚስቱን ርብቃን ባል ያላት መሆኗን እንዳትገልጽ አድርጎ ነበር። በዚያን ጊዜ የዘሩ መሥመር የሚመጣበት ወንድ ልጅ ያዕቆብ ተወልዶና አድጎ ወጣት ልጅ ሆኖ ነበር። (ዘፍጥረት 25:20-27፤ 26:1-11) ይሁን እንጂ ከዚህ በቅንነት የተደረገ ብልሀት በስተጀርባ የነበረው ምክንያት ከአብርሃም ጋር አንድ ሊሆን ይችላል። ረሀብ በነበረበት አንድ ወቅት ይስሐቅና ቤተሰቡ በፍልስጥኤም አቤሜሌክ በሚባል ንጉሥ አገር ይቀመጡ ነበር። ርብቃ የይስሐቅ ሚስት መሆኗን ቢገነዘብ የይስሐቅን ቤተሰብ በሙሉ ሊፈጃቸው ይችል ነበር። ይህም በያዕቆብም ላይ ሞት ሊያስከትል ይችል ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይም ይሖዋ አገልጋዮቹንና የዘሩን መሥመር ለመጠበቅ ጣልቃ ገብቷል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በጄቢ ሮዘርሃም የተዘጋጀው ትርጉም “ለምን እህቴ ናት አልክ? ሚስቴ እንድትሆነኝ ልወስዳት ነበር” በማለት ይነበባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ