የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 4/15 ገጽ 12-17
  • “የተሰጡ” ሰዎች፣ የይሖዋ ዝግጅት ክፍል ናቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የተሰጡ” ሰዎች፣ የይሖዋ ዝግጅት ክፍል ናቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እሥራኤላውያን ከባቢሎን ተመለሱ
  • እሥራኤላውያን ያልሆኑም ተመልሰዋል
  • ዘመናዊ አምሳያ
  • ለልዩ አገልግሎት የተሰጡ
  • በዛሬው ጊዜ ራሳችንን መስጠት
  • ማስታወቂያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • የዕዝራ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • “የአምላክ እስራኤል” እና “እጅግ ብዙ ሰዎች”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመልሶ በተቋቋመው “ምድር” አንድ ላይ የሚኖሩ ሰዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 4/15 ገጽ 12-17

“የተሰጡ” ሰዎች፣ የይሖዋ ዝግጅት ክፍል ናቸው

“መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ።”​—ኢሳይያስ 61:5

1. “ሰጪ” የሚለው ቃል ይሖዋን የሚያስታውሰን ለምንድን ነው?

አምላክ ምንኛ ለጋስ ሰጪ ነው! ሐዋርያው ጳውሎስ “[ይሖዋ (አዓት)] ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣል” ብሏል። (ሥራ 17:25) እያንዳንዳችን ከአምላክ ስለምንቀበላቸው ‘በጎ ስጦታዎችና ፍጹም በረከቶች’ ብናሰላስል ብዙ ልንጠቀም እንችላለን።​—ያዕቆብ 1:5, 17፤ መዝሙር 29:11፤ ማቴዎስ 7:7፤ 10:19፤ 13:12፤ 21:43

2, 3. (ሀ) ለአምላክ ስጦታ ምላሽ የምንሰጠው እንዴት መሆን ይኖርበታል? (ለ) ሌዋውያን “የተሰጡ” የነበሩት በምን መንገድ ነበር?

2 መዝሙራዊው የይሖዋን ውለታ እንዴት እንደሚመልስ ያሳሰበው በቂ ምክንያት ስለነበረው ነው። (መዝሙር 116:12) እርግጥ ፈጣሪያችን ሰዎች ያላቸው ወይም እነሱ ሊሰጡ የሚችሉት ማንኛውም ነገር አያስፈልገውም። (መዝሙር 50:10, 12) ቢሆንም ይሖዋ ሕዝቦቹ ለእውነተኛ አምልኮ ራሳቸውን በአድናቆት ሲሰጡ እንደሚደሰት ገልጿል። (ከዕብራውያን 10:5-7 ጋር አወዳድር) ሰዎች ሁሉ ራሳቸውን ለፈጣሪ መወሰንና መስጠት ይገባቸዋል። ፈጣሪ ደግሞ በጥንቶቹ ሌዋውያን ረገድ እንደታየው ተጨማሪ መብቶችን ሊዘረጋላቸው ይችላል። ሁሉም እሥራኤላውያን የአምላክ ውስን ሕዝቦች የነበሩ ቢሆንም በመገናኛው ድንኳንና በቤተ መቅደሱ ካህናት ሆነው መሥዋዕቶችን እንዲያቀርቡ የመረጠው ሌዋዊ የሆነውን የአሮን ቤተሰብ አባሎችን ነበር። የቀሩት ሌዋውያንስ?

3 ይሖዋ ለሙሴ “የሌዊን ነገድ አቅርባቸው። . . . የመገናኛውንም ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቁ። . . . ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ። ከእሥራኤል ልጆች ለእርሱ ፈጽመው ተሰጡ [በዕብራይስጥ ነቱኒም]።” (ዘኁልቁ 3:6, 8, 9, 41) ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን ሥራ እንዲያከናውኑ ለአሮን ‘ተሰጥተዋል።’ ስለዚህ አምላክ “እነርሱም ከእሥራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጡ” ሊል ችሎአል።” (ዘኁልቁ 8:16, 19፤ 18:6) አንዳንድ ሌዋውያን የሚያከናውኑት ቀላል ተግባሮችን ሲሆን ሌሎች ደግሞ የአምላክን ሕጎች ማስተማርን የመሰለ ከፍ ያለ የአገልግሎት መብት ተቀብለዋል። (ዘኁልቁ 1:50, 51፤ 1 ዜና መዋዕል 6:48፤ 23:3, 4, 24-32፤ 2 ዜና መዋዕል 35:3-5) አሁን ደግሞ ትኩረታችንን በሌሎች ‘የተሰጡ’ ሰዎችና በዘመናዊ አምሳያዎቻቸው ላይ እናድርግ።

እሥራኤላውያን ከባቢሎን ተመለሱ

4, 5. (ሀ) ከባቢሎን ምርኮ የተመለሱት የትኞቹ እሥራኤላውያን ነበሩ? (ለ) በዘመናችን እሥራኤላውያን ከምርኮ ከመመለሳቸው ጋር የሚመሳሰል ምን ድርጊት ተፈጽሞአል?

4 እሥራኤላውያን ቀሪዎች በገዢው በዘሩባቤል እየተመሩ እውነተኛውን አምልኮ ለማቋቋም ከባቢሎን ወደ አገራቸው እንዴት እንደተመለሱ ዕዝራና ነህምያ ተርከዋል። ሁለቱም በጻፉአቸው ታሪኮች ላይ ወደ ይሁዳ የተመለሱት ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 42,360 እንደነበረ ተዘግቧል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት “ከእሥራኤል ወገን የሆኑ ሰዎች” ነበሩ። ታሪኩ በመቀጠል የካህናትን ዝርዝር መዝግቦአል። ከዚያም ሌዋውያን መዘምራንንና በረኞችን ጨምሮ 350 ሌዋውያን ተመዝግበዋል። ዕዝራና ነህምያ ከጻፉአቸው መካከል በሺህ የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎች ደግሞ የዘር ሐረጋቸውን ከትውልድ መጽሐፍ ሊያረጋግጡ ያልቻሉ እሥራኤላውያን እንዲያውም ካህናት ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች ነበሩ።​—ዕዝራ 1:1, 2፤ 2:2-42, 59-64፤ ነህምያ 7:7-45, 61-66

5 እነዚህ በምርኮኛነት ወደ ባቢሎን ተወስደው የነበሩትና በኋላ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ የተመለሱት የእሥራኤል ቀሪዎች ከፍተኛ የሆነ ለይሖዋ የማደርና ለእውነተኛ አምልኮ የመወሰን ጠባይ አሳይተዋል። በ1919 ከታላቂቱ ባቢሎን ነፃ የወጡት የመንፈሳዊ እሥራኤል ቀሪዎች ሁኔታም ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ቀደም ብለን ተመልክተናል።

6. አምላክ በጊዜያችን በመንፈሳዊ እሥራኤላውያን የተጠቀመው እንዴት ነው?

6 የክርስቶስ ቅቡአን ቀሪዎች ወንድሞች ከባቢሎን ነፃ ከወጡበት ከ1919 ጀምሮ በእውነተኛ አምልኮ ጎዳና በቅንነት ወደፊት ተራምደዋል። ይሖዋም “የእግዚአብሔር እሥራኤል” የሆኑትን የ144,000 የመጨረሻ ቀሪዎች ለመሰብሰብ ያደረጉትን ጥረት ባርኮላቸዋል። (ገላትያ 6:16፤ ራእይ 7:3, 4) ቅቡአን ቀሪዎች እንደ አንድ ቡድን በመሆን ሕይወት ሰጪውን መንፈሳዊ ምግብ ለማቅረብ የሚያገለግለው “የታማኝና ልባም ባሪያ” ክፍል ሆነዋል። ይህን ሕይወት ሰጪ መንፈሳዊ ምግብ በምድር ዙሪያ ለማዳረስ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው።​—ማቴዎስ 24:45-47

7. ከቅቡአን ጋር በእውነተኛ አምልኮ በመተባበር ላይ የሚገኙት እነማን ናቸው?

7 ባለፈው ርዕሰ ትምህርት ላይ እንደተገለጸው በዛሬው ጊዜ የይሖዋ ሕዝብ በቅርቡ ከሚመጣው ታላቅ መከራ በሕይወት የማለፍ ከአምላክ የተሰጠ ተስፋ ያላቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩትን “ሌሎች በጎች” ይጨምራል። እነሱም ዳግመኛ በማይራቡበትና በማይጠሙበት እንዲሁም ዓይኖቻቸው የኀዘን እንባ በማያፈሱበት ምድር ላይ ለዘላለም ይሖዋን ለማገልገል ይመኛሉ። (ዮሐንስ 10:16፤ ራእይ 7:9-17፤ 21:3-5) ታዲያ ከባቢሎን ከተመለሱት የይሖዋ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ በዘመናችን ካሉት “ሌሎች በጎች” ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ እናገኛለንን? እንዴታ!

እሥራኤላውያን ያልሆኑም ተመልሰዋል

8. ከባቢሎን ከተመለሱት እሥራኤላውያን ጋር አብረው የተመለሱት እነማን ነበሩ?

8 በባቢሎን ይኖሩ ለነበሩ የይሖዋ አፍቃሪዎች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመለሱ ጥሪ በተላለፈላቸው ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ እሥራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎችም ጥሪውን ተቀብለዋል። ዕዝራና ነህምያ ባሰፈሩት ዝርዝር ላይ ጠቅላላ ቁጥራቸው 392 ስለሆኑ “ናታኒም” (ትርጉሙ “የተሰጡ ሰዎች” ማለት ነው) እና ስለ ሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች እናነባለን። በዕዝራና በነህምያ ታሪኮች ላይ ከ7,500 በላይ የሆኑ ሎሌዎችና ገረዶች እንዲሁም ሌዋውያን ያልሆኑ “ወንዶችና ሴቶች መዘምራን” ተጠቅሰዋል። (ዕዝራ 2:43-58, 65፤ ነህምያ 7:46-60, 67) ይህን ያህል ብዛት ያላቸው እሥራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመለሱ የገፋፋቸው ምን ነበር?

9. የአምላክ መንፈስ ከምርኮ በመመለስ ጉዳይ ተካፋይ የነበረው እንዴት ነበር?

9 ዕዝራ 1:5 “የ[ይሖዋ (አዓት)]ን ቤት ለመሥራት ይወጡ (ይሄዱ) ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሳሳው ሁሉ ተነሱ” በማለት ይናገራል። አዎን፣ እነዚህ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ይሖዋ ያነሳሳቸው ነበሩ። ይሖዋ መንፈሳቸውን ማለትም የሚገፋፋቸውን የአእምሮ ዝንባሌ አነሳስቶታል። አምላክ በሰማይ ላይ ሆኖ አንቀሳቃሽ ኃይሉ የሆነውን መንፈስ ቅዱሱን በመጠቀም መንፈሳቸውን ሊያነሳሳው ችሎ ነበር። ስለዚህ “የ[ይሖዋ (አዓት)]ን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ” የተነሱት ሁሉ የታገዙት “[በአምላክ] መንፈስ” ነበር።​—ዘካርያስ 4:1, 6፤ ሐጌ 1:14

ዘመናዊ አምሳያ

10, 11. ከባቢሎን ከተመለሱት እሥራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች ጋር የሚመሳሰሉት እነማን ናቸው?

10 እነዚህ እሥራኤላውያን ያልሆኑ ተመላሾች ጥላ የሆኑት ለእነማን ነው? ብዙ ክርስቲያኖች ‘ናታኒም ከአሁኖቹ “ሌሎች በጎች” ጋር ይመሳሰላሉ’ በማለት መልስ ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ እውነት ቢሆንም ለሌሎች በጎች ጥላ የሚሆኑት ናታኒም ብቻ አይደሉም፤ ምክንያቱም እሥራኤላውያን ያልሆኑ ተመላሾች በሙሉ የሚያመለክቱት የዛሬዎቹን መንፈሳዊ እሥራኤላውያን ያልሆኑ ክርስቲያኖች ነው።

11 ከአርማጌዶን በሕይወት ተርፈህ ወደ አዲሲቱ ዓለም ልትገባ ትችላለህa የተሰኘው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ እንደሚከተለው ይላል፦ “ከገዢው ከዘሩባቤል ጋር ባቢሎንን ለቀው የወጡት 42,360 እሥራኤላውያን ቀሪዎች ብቻ አልነበሩም። . . . በሺዎች የሚቆጠሩ እሥራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎችም ነበሩ። . . . ከናታኒም በተጨማሪ ሌሎች እሥራኤላውያን ያልሆኑ ባሪያዎች፣ የሠለጠኑ ወንዶችና ሴቶች መዘምራንና የንጉሥ ሰሎሞን አገልጋዮች ልጆችም ነበሩ።” መጽሐፉ እንደሚከተለው አብራርቷል፦ “እሥራኤላውያን ያልሆኑ ናታኒም፣ ባሪያዎች፣ ዘማሪዎችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ከእሥራኤላውያን ቀሪዎች ጋር ሆነው በምርኮኛነት ይኖሩበት የነበረውን አገር ለቀው ወጡ። . . . ታዲያ በዛሬው ጊዜ መንፈሳዊ እሥራኤላውያን ያልሆኑ የተለያየ ዜግነት ያላቸው ሕዝቦች የይሖዋ አምላክን አምልኮ ለማስፋፋት ከመንፈሳዊ እሥራኤል ቀሪዎች ጋር ይተባበራሉ ብሎ ማሰብ ተገቢ ነውን? አዎን።” እነዚህ መንፈሳዊ እስራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች ‘የናታኒም፣ የመዘምራንና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ዘመናዊ አምሳያ ሆነዋል።’

12. አምላክ መንፈሱን ለመንፈሳዊ እሥራኤላውያን በተለየ መንገድ የሚጠቀመው እንዴት ነው? ሆኖም አምላኪዎቹ በሙሉ መንፈሱን ለማግኘት እንደሚችሉ እርግጠኞች ልንሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

12 አምላክ አምሳያዎቻቸው ለነበሩት የጥንት ሕዝቦች እንዳደረገው ሁሉ ለእነዚህ በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ለሚያደርጉ ሕዝቦችም መንፈሱን ይሰጣል። እርግጥ እነዚህ ሰዎች ዳግም ልደት ያገኙ አይደሉም። እያንዳንዱ የ144,000 አባል ግን የአምላክ መንፈሳዊ ልጅ በመሆንና በመንፈስ ቅዱስ በመቀባት ዳግመኛ የተወለደ ነው። (ዮሐንስ 3:3, 5፤ ሮሜ 8:16፤ ኤፌሶን 1:13, 14) በእርግጥ ይህ መቀባት ለታናሽ መንጋ ብቻ የተደረገ የአምላክ መንፈስ ልዩ መገለጫ ነው። ይሁን እንጂ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግም መንፈሱ ያስፈልጋል። በመሆኑም ኢየሱስ ‘በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን ይሰጣል’ ብሏል። (ሉቃስ 11:13) መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጠው የሚጠይቀው ሰው ሰማያዊ ተስፋ ያለውም ይሁን የሌሎች በጎች አባል የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም የይሖዋን መንፈስ በብዛት ማግኘት ይችላል።

13. መንፈሱ በሁሉም የአምላክ አገልጋዮች ላይ ሊሠራ የሚችለው እንዴት ነው?

13 የአምላክ መንፈስ እሥራኤላውያንንም ሆነ እሥራኤላውያን ያልሆኑትን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አነሳስቷቸዋል፤ ዛሬም የአምላክን ታማኝ ሕዝቦች በሙሉ ያበረታቸዋል፣ ይረዳቸዋልም። አንድ ክርስቲያን ከአምላክ የተሰጠው የሕይወት ተስፋ ሰማያዊም ሆነ ምድራዊ የምሥራቹን መስበክ ይኖርበታል። በዚህም ሥራ ታማኝ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ ይረዳዋል። ማንኛችንም ብንሆን ተስፋችን ምንም ይሁን ምን በተሟላ ሁኔታ የሚያስፈልጉንን የመንፈስ ፍሬዎች መኮትኮት ያስፈልገናል።​—ገላትያ 5:22-26

ለልዩ አገልግሎት የተሰጡ

14, 15. (ሀ) ከምርኮ ከተመለሱት እሥራኤላውያን ያልነበሩ ወገኖች መካከል ተለይተው የተጠቀሱት የትኞቹ ሁለት ቡድኖች ናቸው? (ለ) ናታኒም እነማን ነበሩ? ምንስ አድርገዋል?

14 ወደ ይሁዳ እንዲመለሱ መንፈሱ ካነሳሳቸው እሥራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች መካከል የአምላክ ቃል ናታኒምና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ብሎ ለይቶ የሚናገርላቸው ሁለት አነስተኛ ቡድኖች ይገኙበታል። እነዚህ ናታኒምና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች እነማን ነበሩ? ምንስ አድርገዋል? ይህስ ለዛሬው ጊዜ ምን ትርጉም ይኖረዋል?

15 ናታኒም ከሥረ መሠረታቸው እሥራኤላውያን ያልነበሩና ከሌዋውያን ጋር ለማገልገል መብት ያገኙ ቡድኖች ነበሩ። “ለማህበሩና ለይሖዋ መሠዊያ እንጨት ለቃሚዎችና ውኃ ቀጂዎች” የሆኑትን የገባኦን ከነዓናውያን አስታውሱ። (ኢያሱ 9:27) በዳዊት ዘመነ መንግሥትና በሌሎችም ጊዜያት ናታኒም ሆነው ከተጨመሩት እንዲሁም ከባቢሎን ከተመለሱት ናታኒም መካከል ምናልባት የገባኦናውያን ዝርያዎች ሳይኖሩ አይቀሩም። (ዕዝራ 8:20) ናታኒም ምን ያደርጉ ነበር? ሌዋውያን ካህናትን እንዲረዱ ለአሮንና ለልጆቹ የተሰጡ ሲሆኑ በኋላ ደግሞ ናታኒም ሌዋውያንን እንዲረዷቸው ተሰጡ። ናታኒም የተገረዙ እንግዶች ቢሆኑም እንኳን ይህ ለእነርሱ ትልቅ መብት ነበር።

16. የናታኒም የሥራ ድርሻ ከጊዜ በኋላ የተለወጠው እንዴት ነው?

16 ከባቢሎን ከተመለሱት ሰዎች መካከል የተገኙት ሌዋውያን ቁጥር ከካህናቱ ወይም ከናታኒምና “ከሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች” ጋር ሲወዳደር በጣም ጥቂት ነበር። (ዕዝራ 8:15-20) ዶክተር ጀምስ ሀስቲንግስ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ “ከጊዜ በኋላ [ናታኒም] የተሟላ ቅዱስ ሥልጣንና የአገልግሎት መብት የተሰጣቸው የተደላደሉ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ሆነው እናገኛቸዋለን” ብለዋል። ቬቱስ ቴስታመንቱም የተሰኘ ምሁራዊ ጆርናል “ለውጥ ተደርጓል። ከምርኮ መልስ በኋላ እነዚህ [እንግዶች] የቤተ መቅደስ ባሪያዎች እንደሆኑ ተደርገው መቆጠራቸው ቀርቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ የአምልኮ ሥርአቶችን ለመፈጸም የሚያስችል ሥልጣን ካላቸው ሌሎች አገልጋዮች ጋር የሚተካከል ማዕረግና ደረጃ እንዳላቸው ሰዎች መታየት ጀመሩ” ይላል።​—“የደረጃ ለውጥ” የሚለውን ሣጥን ተመልከቱ።

17. ናታኒም ተጨማሪ ሐላፊነት የተቀበሉት ለምን ነበር? ለዚህስ ምን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለ?

17 እርግጥ ናታኒም የካህናትና የሌዋውያን እኩዮች አልሆኑም። ካህናትና ሌዋውያን በይሖዋ በራሱ የተመረጡ እሥራኤላውያን ስለነበሩ እሥራኤላውያን ባልሆኑ ሰዎች የሚተኩ አልነበሩም። ሆኖም የሌዋውያን ቁጥር በማነሱ ምክንያት ናታኒም በአምላክ አገልግሎት የሚሠሩት ተጨማሪ ሥራ እንደተሰጣቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። ናታኒም በቤተ መቅደሱ አቅራቢያ በነበሩ መኖሪያ ቤቶች እንዲቀመጡ ተደልድለው ነበር። በነህምያ ዘመን በቤተ መቅደስ አቅራቢያ የነበረውን ግድግዳ ለማደስ ከካህናት ጋር አብረው ሠርተዋል። (ነህምያ 3:22-26) የፋርስ ንጉሥ ሌዋውያን በቤተ መቅደስ ስለሚያገለግሉ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ እንዳደረገ ሁሉ ናታኒምም ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ አውጆ ነበር። (ዕዝራ 7:24) ይህም በዚያ ጊዜ እነዚህ “የተሰጡ ሰዎች” (ሌዋውያንና ናታኒም) ከመንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር ምን ያህል የቅርብ ግንኙነት እንደነበራቸውና ናታኒምም ሌዋውያን እንደሆኑ ተደርገው የማይታዩ ቢሆኑም አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ መጠን የሥራ ምድባቸው መጨመሩን ያመለክታል። ቆየት ብሎ ዕዝራ ወደ ይሁዳ የሚመለሱ ምርኮኞችን በሰበሰበ ጊዜ በመጀመሪያ በመካከላቸው ማንም ሌዋዊ አልነበረም። ስለዚህ ሌዋውያንን ለማሰባሰብ ጥረቱን አጠናክሮ ነበር። ይህም ጥረት “ለአምላካችን ቤት አገልጋዮች” ሆነው የሚያገለግሉ 38 ሌዋውያንና 220 ናታኒም አስገኝቷል።​—ዕዝራ 8:15-20

18. የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ምን ተግባር አከናውነው ሊሆን ይችላል?

18 ሌሎቹ ተለይተው የተጠቀሱ እሥራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች ሁለተኛ ቡድን የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለእነርሱ የሚሰጠው ዝርዝር መግለጫ ጥቂት ነው። አንዳንዶቹ “የሶፌሬት ልጆች” ነበሩ። ዕዝራ በዚህ ስም ላይ ጠቃሽ አመልካች በመጨመር ሀሶፌሬት ይለዋል። ትርጉሙም ምናልባት “ጸሐፊው” ማለት ሊሆን ይችላል። (ዕዝራ 2:55፤ ነህምያ 7:57) ስለዚህ ፀሐፊዎች ወይም መጽሐፍ ገልባጮች ወይም የቤተ መቅደሱ የአስተዳደር ፀሐፊዎች ሳይሆኑ አይቀሩም። የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ከእንግዳ ዝርያ የተገኙ ቢሆኑም የይሖዋን አምልኮ መልሶ በማቋቋሙ ሥራ ለመካፈል ሲሉ ባቢሎንን ለቀው ወደ ይሁዳ በመመለስ ለይሖዋ ያደሩ መሆናቸውን አሳይተዋል።

በዛሬው ጊዜ ራሳችንን መስጠት

19. በዛሬው ጊዜ በቅቡዓንና በሌሎች በጎች መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው?

19 አምላክ በጊዜያችን ለንጹሕ አምልኮ ግንባር ቀደም እንዲሆኑና የምሥራቹን እንዲያውጁ በቅቡዓን ቀሪዎች በጣም ተጠቅሞአል። (ማርቆስ 13:10) እነሱም በአሥር ሺዎች፣ በመቶ ሺዎችና በኋላም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች በጎች በአምልኮ ሲተባበሩአቸው በመመልከታቸው እጅግ ተደስተዋል። በቅቡዓን ቀሪዎቹና በሌሎች በጎች መካከል ያለው ትብብርስ ምንኛ የሚያስደስት ነው!​—ዮሐንስ 10:16

20. ከናታኒምና ከሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ጋር የሚመሳሰሉ ቡድኖችን በሚመለከት የተገኘው ምክንያታዊና ተገቢ እውቀት ምንድን ነው? (ምሳሌ 4:18)

20 ከጥንቷ ባቢሎን ምርኮኛነት የተመለሱት እሥራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ከመንፈሳዊ እሥራኤል ቀሪዎች ጋር ከሚያገለግሉት ሌሎች በጎች ጋር ይመሳሰላሉ። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ናታኒምንና የሰሎሞንን ባሪያዎች ልጆች ነጥሎ ስለ መጥቀሱ ምን ሊባል ይቻላል? በጥንቱ ዘመን ናታኒምና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ከሌሎች እሥራኤላውያን ያልነበሩ ተመላሾች የሚበልጡ መብቶች ተሰጥተዋቸው ነበር። ይህም አምላክ በዛሬው ጊዜ ለአንዳንድ የጎለመሱና ፈቃደኞች የሆኑ የሌሎች በጎች አባላት ልዩ መብትና ተጨማሪ ሥራ እንደዘረጋላቸው የሚያመለክት ጥላ ሊሆን ይችላል።

21. ምድራዊ ተስፋ ያላቸው አንዳንድ ወንድሞች ተጨማሪ ሥራና መብት የተቀበሉት እንዴት ነው?

21 የናታኒም ተጨማሪ መብቶች ከመንፈሳዊ ሥራዎች ጋር በቀጥታ የሚገናኙ ነበሩ። የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች የአስተዳደር ሐላፊነቶችን የተቀበሉ ይመስላል። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ሕዝቦቹን በሚያስፈልጉአቸው ሁሉ የሚያገለግሉ “የሰዎችን ስጦታዎች” በመስጠት ባርኳቸዋል። (ኤፌሶን 4:8, 11, 12) በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የጎለመሱና ‘የመንጋው እረኞች’ ሆነው የሚያገለግሉ፣ የክልልና የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በመጠበቂያ ግንብ ማህበር 98 ቅርንጫፎች የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙ ተሞክሮ ያላቸው ወንድሞች በዚህ ‘የሰዎች ስጦታ’ ዝግጅት ውስጥ የሚጠቃለሉ ናቸው። (ኢሳይያስ 61:5) በማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት “በታማኝና ልባም ባሪያ”ና በአስተዳደር አካሉ አመራር ሥር የሚሠሩ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ወንዶች መንፈሳዊ ምግብ በማዘጋጀት ሥራ እንዲያግዙ የሚያስችላቸው ሥልጠና እየተሰጣቸው ነው። (ሉቃስ 12:42) ሌሎች የረዥም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው ውስን ፈቃደኛ አገልጋዮች የቤቴልንና የፋብሪካዎችን ሥራ እንዲያካሂዱና አዳዲስ የቅርንጫፍ ሕንፃዎችንና ለክርስቲያናዊ አምልኮ የሚውሉ አዳራሾችን በመገንባቱ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሐ ግብሮችን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ የሚያስችላቸው ማሠልጠኛ ተሰጥቷቸዋል። እነሱም የንጉሣዊ ክህነቱ አባሎች የሆኑት ቅቡዓን ቀሪዎች የቅርብ ረዳት ሆነው በማገልገል ረገድ በልጠው ተገኝተዋል።​—ከ1 ቆሮንቶስ 4:17፤ 14:40፤ ከ1 ጴጥሮስ 2:9 ጋር አወዳድር።

22. በአሁኑ ጊዜ ከሌሎች በጎች መካከል ለአንዳንዶቹ ከበድ ያሉ ሐላፊነቶች ሊሰጣቸው ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንንስ እንዴት ባለ መንፈስ መቀበል ይኖርብናል?

22 በጥንት ዘመን ካህናትና ሌዋውያን በአይሁድ ሕዝብ መካከል የማይቋረጥ አገልግሎት ይሰጡ ነበር። (ዮሐንስ 1:19) በዛሬው ጊዜ ግን በምድር ላይ ያሉት የመንፈሳዊ እሥራኤል ቀሪዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄድ አለበት። (ከዮሐንስ 3:30 ጋር አወዳድር።) በመጨረሻም ከታላቂቱ ባቢሎን ጥፋት በኋላ “የታተሙት” 144,000 በሙሉ ለበጉ ሠርግ በሰማይ ይገኛሉ። (ራዕይ 7:1-3፤ 19:1-8) ሌሎች በጎች ግን በቁጥር እየጨመሩ መሄድ አለባቸው። ከናታኒምና ከሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ጋር በሚመሳሰል መንገድ ከሌሎች በጎች መካከል አንዳንዶቹ በቅቡዓን ቀሪዎች የበላይ ተመልካችነት ሥር ከበድ ላሉ ሐላፊነቶች እየተመደቡ መሆናቸው ከልክ በላይ በራሳቸው እንዲተማመኑ ወይም ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ምክንያት አይሆናቸውም። (ሮሜ 12:3) ይህም የአምላክ ሕዝቦች ‘ከታላቁ መከራ በሚያልፉበት’ ጊዜ በሌሎች በጎች መካከል የመሪነት ቦታ ለመያዝ የተዘጋጁ ተሞክሮ ያላቸው “መሳፍንት” የሚሆኑ ሰዎች እንደሚኖሩ እርግጠኞች ለመሆን የሚያስችለን ምክንያት ይሰጠናል።​—ራእይ 7:14፤ ኢሳይያስ 32:1፤ ከሥራ 6:2-7 ጋር አወዳድር

23. የአምላክን አገልግሎት በሚመለከት ሁላችንም የለጋስነት መንፈስ መኮትኮት ያለብን ለምንድን ነው?

23 ከባቢሎን የተመለሱት ሰዎች በሙሉ ጠንክረው ለመሥራትና ለይሖዋ አምልኮ በሐሳባቸውና በልባቸው የመጀመሪያውን ቦታ እንደሚሰጡ ለማሳየት ፈቃደኞች ነበሩ። ዛሬም እንዲሁ ነው። ከቅቡዓን ቀሪዎች ጋር ሆነው “መጻተኞች (እንግዶች) ቆመው በጎቻቸውን ያሠማራሉ።” (ኢሳይያስ 61:5) ስለዚህ ከአምላክ የተሰጠን ተስፋ ምንም ይሁን ምን፣ የይሖዋ ሉዓላዊነት በአርማጌዶን ከመረጋገጡ በፊት በመንፈስ ለተሾሙ ሽማግሌዎች የሚዘረጉላቸው መብቶች ምንም ይሁኑ ምን፣ ሁላችንም ራስ ወዳድነት የሌለበትና ጤናማ የሆነ የልግስና መንፈስ እንኮትኩት። ይሖዋ ላደረገልን ታላላቅ ውለታዎች በሙሉ ውለታ ልንመልስለት ፈጽሞ የማንችል ብንሆንም በድርጅቱ ውስጥ የምናደርገውን ማንኛውም ሥራ በሙሉ ነፍሳችን የምናደርግ እንሁን። (መዝሙር 116:12-14፤ ቆላስይስ 3:23) ይህን በማድረጋችንም ሌሎች በጎች “በምድር ላይ እንዲነግሡ” ከተወሰኑት ቅቡዓን ጋር ቅርብ ለቅርብ ሆነው በሚያገለግሉበት በዚህ ጊዜ ሁላችንም ራሳችንን ለእውነተኛ አምልኮ ለመስጠት እንችላለን።​—ራዕይ 5:9, 10

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትናንሽ ጽሑፎች ማህበር የተዘጋጀውን ይህን መጽሐፍ ገጽ 142-8 ተመልከት

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

◻ በጥንቷ እሥራኤል ሌዋውያን “የተሰጡ” ሰዎች የነበሩት በምን መንገድ ነው?

◻ ከምርኮ ተመልሰው የነበሩት የትኞቹ እሥራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች ናቸው? ጥላነታቸውስ ለማን ነው?

◻ ናታኒምን በሚመለከት ምን ለውጥ የተደረገ ይመስላል?

◻ በናታኒምና በሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ረገድ በዛሬው ጊዜ ምን ተመሳሳይነት ያለው ሁኔታ መገንዘብ ተችሏል?

◻ በቅቡዓንና በሌሎች በጎች መካከል ያለው ትብብር ምን አይነት ትምክህት አስገኝቷል?

[በገጽ 14 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የደረጃ መለወጥ

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትና ኢንሳይክሎፒዲያዎች ከምርኮ የተመለሱ አንዳንድ እሥራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች ስላጋጠሟቸው ለውጦች አስተያየት ሰጥተዋል። ለምሳሌ ያህል ኢንሳይክሎፒዲያ ቢብሊካ “በደረጃቸው ላይ የተደረገ ለውጥ” በሚል ርዕስ ሥር “ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው ማህበራዊ ደረጃቸውም አብሮ ከፍ ብሎ ነበር ሊባል ይቻላል። [ናታኒም] ከዚያ በኋላ ባሪያ በሚለው ቃል ደንበኛ አገባብ መሠረት ባሪያዎች የነበሩ አይመስልም” ብሏል። (በቼይኔና በብላክ የተዘጋጀው፣ ጥራዝ 3 ገጽ 3399) ጆን ኪቶ በሳይክሎፒዲያ ኦቭ ቢብሊካል ሊትሬቸር ውስጥ “አብዛኞቻቸው [ናታኒም] ለዚህ ዝቅተኛ ደረጃ ወደ ፓለስቲና ምድር ይመለሳሉ ተብሎ አይጠበቅም ነበር። . . . እነዚህ ሰዎች ያሳዩት የውዴታ ታማኝነት የናታኒምን ደረጃ በጣም ከፍ አድርጎላቸዋል”ብለዋል። (ጥራዝ 2 ገጽ 417) ዘ ኢንተርናሽናል እስታንዳርድ ባይብል ኢንሳይክሎፒዲያ “የሰሎሞን ባሪያዎች ከሰሎሞናዊው ዘመን ጋር በነበራቸው ግንኙነትና የሥራ መደብ አንፃር ሲታይ በሁለተኛው ቤተመቅደስ ትልቅ ሐላፊነት እንደነበራቸው ሊገመት ይችላል” በማለት ይናገራል።​—በጂ ደብልዩ ብሮሚሊ የተዘጋጀው፣ ጥራዝ 4 ገጽ 570

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

እሥራኤላውያን ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመገንባት በተመለሱ ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ እሥራኤላውያን ሰዎች አብረዋቸው ተመልሰዋል

[ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የኮሪያው ቅርንጫፍ ኮሚቴ። እንደ ጥንቶቹ ናታኒም ሁሉ የሌሎች በጎች ሰዎችም በዛሬም ጊዜ በእውነተኛ አምልኮ ውስጥ ከባድ ሐላፊነቶች አሏቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ