የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 12/15 ገጽ 3-4
  • ወንጌል በእርግጥ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወንጌል በእርግጥ ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወንጌል ምንድን ነው?
  • ወንጌልን ለይቶ ማወቅ
  • ከሌላው ሁሉ ለየት ያለ መልእክት
  • “የይሁዳ ወንጌል” ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ወንጌል ሊጠቅምህ የሚችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ስለ ኢየሱስ የሚተርኩት ዘገባዎች የተጻፉት መቼ ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ወንጌሎች ምን ያህል እምነት የሚጣልባቸው ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 12/15 ገጽ 3-4

ወንጌል በእርግጥ ምንድን ነው?

በገና በዓል ሰሞን በብዙ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ስለ ወንጌል ይሰማሉ፤ በየበኩላቸውም ይነጋገሩበታል። ቃሉ በጣም የተለመደ ነው፤ ነገር ግን ብዙዎች ከሚገምቱት የበለጠ ትርጉም አለውን? ወንጌል ለአንተና ለምትወዳቸው ሰዎች በጣም ግሩም የሆነ ትርጉም ይኖረው ይሆን?

“ወንጌል” ማለት “የምሥራች” ማለት ነው። የምሥራች ወይም መልካም የሆነ ዜና ደግሞ በገና ጊዜ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ በደስታ ሊቀበሉት የሚገባ መሆኑ የተረጋገጠ ነው። “ወንጌሉ” ግን ተራ የሆነ መልካም ዜና አይደለም። ከአንድ ልዩ ምንጭ የመጣ ስለ አንድ የተወሰነ ነገር የሚናገር የተለየ የምሥራች ነው። እንዲያውም አምላክ ለሁሉም የሰው ዘር እንዲታወጅ የወሰነው መልእክት ነው።

በብራዚል የሪዮ ዲ ጃኔሮ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ኤውጄንዮ ሳሌስ “ከርዕዮተ ዓለም ይልቅ ከወንጌል ጋር የሚጣጣም ነገር መሥራት ይኖርብናል” በማለት አጥብቀው ባሳሰቡ ጊዜ ስለዚህ ወንጌል ተናግረዋል። ሊቀ ጳጳሱ ትክክል ነበሩ። ይሁን እንጂ ከወንጌል ጋር የሚጣጣም ነገር ለማድረግ ወንጌል ምን ማለት እንደሆነ እንድናውቅ ይፈለግብናል። ታዲያ ወንጌል ምን እንደሆነ እንዴት ለማወቅ እንችላለን? ከወንጌሉ ጋር የሚስማማ ነገር ማድረግስ እኛን ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

ወንጌል ምንድን ነው?

ብዙውን ጊዜ ሰዎች የወንጌሉን መንፈስ በተሳሳተ ሁኔታ ይረዱታል። በ1918 በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት አሁን የሌለውን የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር በምድር ላይ የአምላክ መንግሥት ፖለቲካዊ መግለጫ ነው በማለት በጭብጨባ ተቀብሎት ነበር። እንዲሁም “ከወንጌል የመነጨ ነው” በማለት ገልጾታል። የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ሰላምን ለማስጠበቅ የነበረው ዓላማ በሚያሳዝን ሁኔታ ከሽፎበታል። በግልጽ እንደሚታየው ምክር ቤቱ ተሳስቶ ነበር። የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኀበር ከወንጌል ጋር ምንም ግንኙነት አልነበረውም።

በቅርብ ዓመታት በነፃ አውጪነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖታዊ ትምህርት አራማጆች ስለ ፖለቲካዊ ወይም ማኅበራዊ የተሃድሶ አስተሳሰቦቻቸው በነፃነት ከወንጌል እየጠቀሱ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ እንዲህ በማድረጋቸው እውነተኛውን ወንጌል ችላ ብለውታል። ቬዣ የተባለው የብራዚል መጽሔት “የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለማኅበራዊ መንግሥት የበለጠ ግምት በመስጠት ምእመናኗ የሚያስፈልጋቸውን መንፈሳዊ ነገር ችላ ማለት ጀምራለች። በአንድ ስብከት ውስጥ አምላክ የሚለውን ቃል ለመስማት የሚፈልጉ አብዛኛውን ጊዜ የሚያገኙት በማኅበራዊ በደሎች ላይ የሚደረግ መልስ የማይሰጥበት ጭቅጭቅ ብቻ ሆኖ ነው” በማለት ተችቷል።

የኑሮ ሁኔታ መሻሻልና የፖለቲካ ሥርዓቶች መለወጥ ለአንዳንዶች ምሥራች ይሆንላቸው ይሆናል። ሆኖም አምላክ ለሰው ዘር ሁሉ እንዲነገር የፈለገው ምሥራች ወይም ይህ ወንጌል አይደለም። ቤተ ክርስቲያናቸው እውነተኛውን ወንጌል እንደማታስተምር በማመን አንድ ጳጳስ እንዲህ አሉ፦ “ከ1960ዎቹ ወዲህ በመሠረተ ትምህርቶቻችን ውስጥ ቁሳዊ ነገሮችን ጣልቃ በማስገባታችን ምክንያት ለምእመናን መንፈሳዊ ነገሮች ማስተማርን ችላ ብለነዋል።”

የዩ ኤስ የዜና መጽሔት በሆነው ታይም ላይ የቀረበ አንድ ሪፖርት ፕሮቴስታንቶች እንኳን ስለ ወንጌል ማሰብን እንደተዉ አመልክቷል። መጽሔቱ “ባሕላዊ ሃይማኖቶች ያቃታቸው መልእክቱን ሰው ሊረዳው እንደሚችል አድርጎ ማስተላለፍ ብቻ አይደለም፤ መልእክቱ ራሱ ምን እንደሆነ እንኳን እርግጠኞች አይደሉም” ሲል ጠቅሷል። መልእክታቸው ምን መሆን ይኖርበታል? ወንጌል ምንድን ነው?

ወንጌልን ለይቶ ማወቅ

ዘጠነኛው የዌብስተር ኮሊጂየት መዝገበ ቃላት በትልቅ ፊደል (Capital letter) የሚጀምረውን “ወንጌል” የሚል ትርጉም ያለውን “Gospel” የተባለ የእንግሊዝኛ ቃል “ክርስቶስን፣ የአምላክን መንግሥትና መዳንን የሚመለከት መልእክት” የሚል ፍቺ ሰጥቶታል። በትንሽ ፊደል (Small letter) የሚጀምረው “ወንጌል” የሚል ትርጉም ያለው “gospel” የተባለው የእንግሊዝኛ ቃል ደግሞ “ለክርስትና መልእክት የተሰጠው ትርጉም (ማኅበራዊ ወንጌል)”፣ “የአንድ ሃይማኖታዊ አስተማሪ መልእክት ወይም ትምህርቶች” ተብሎ ተተርጉሟል። እነዚህ ትርጉሞች ሁሉ አግባብነት ያላቸው ናቸውን? አምላክ ለሰው ዘር ሁሉ እንዲነገር ስለሚፈልገው ወንጌል እየተናገርን ከሆነ ሁሉም ትርጉሞች አግባብነት ያላቸው አይደሉም። እውነተኛው ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው። በመሆኑም ከእነዚህ ሦስት ፍቺዎች ትክክለኛው የመጀመሪያው ፍቺ ብቻ ነው። የኋለኞቹ ሁለት ትርጉሞች በትንሽ ፊደል የሚጀምረው “ወንጌል” የሚል ትርጉም ያለው “gospel” የተባለው የእንግሊዝኛ ቃል በዛሬው ጊዜ የሚሠራበትን ሁኔታ የሚያመለክቱ ናቸው።

ከዚህ አስተሳሰብ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ቫይንስ ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት ወርድስ በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች (በ“አዲስ ኪዳን”) ውስጥ ወንጌል “የአምላክን መንግሥትና ሥርየት በሚያስገኘው ሞቱ ላይ በተመሠረተ እምነት በክርስቶስ በኩል የሚገኘውን የመዳን ምሥራች የሚያመለክት ነው” ብሎ ገልጿል። ይህንን መረዳታችን በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም እውነተኛውን ምሥራች በትክክል መረዳታችን ከአሁኑ ደኅንነታችንና ከወደፊቱም ደስታችን ጋር ብዙ ግንኙነት አለው።

ከሌላው ሁሉ ለየት ያለ መልእክት

ቀደም ሲል የጠቀስነው የቃላትን ፍቺ የያዘ መጽሐፍ እንደሚያሳየው ወንጌሉ ከክርስቶስ ጋር በጣም የተያያዘ ከመሆኑ የተነሳ በምድር ላይ ስለነበረው ሕይወቱ የሚገልጹት አራቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች አራቱ ወንጌሎች ተብለው ተሰይመዋል። ሰው ሆኖ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስለ ኢየሱስ የሚነገረው ዜና ሁሉ የምሥራች ነበር። አንድ መልአክ ስለ ኢየሱስ መወለድ ሲያበስር “እነሆ፣ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች [ወይም ወንጌል] እነግራችኋለሁና . . . መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና” ብሎ ነበር።—ሉቃስ 2:10, 11

ሕፃኑ ኢየሱስ ካደገ በኋላ ተስፋ የተሰጠበት መሲህ ማለትም ክርስቶስ ሊሆን ነው። የአምላክን የመዳን ዓላማ መግለጽ፣ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ለሰው ዘር ሲል መስጠት፣ ትንሣኤ ማግኘት ከዚያም የተመረጠው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ መሆን ነበረበት። እውነትም የምሥራች! ስለእርሱ የሚነገረው መልእክት ወንጌል ተብሎ የተጠራው ለዚህ ነው።

ኢየሱስ አጭር በነበረው ምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ምሥራቹን በመስበክ በኩል በጣም ቀናተኛ ነበር። በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥትንም ወንጌል [መልካም ዜና የ1980 ትርጉም] እየሰበከ፣ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፣ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር” የሚል እናነባለን። (ማቴዎስ 9:35) ስብከቱ ሰዎች እንዲጽናኑ የሚያደርግ ብቻ አልነበረም። ማርቆስ ስለ ኢየሱስ እንዲህ በማለት መዝግቧል፦ “ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።” (ማርቆስ 1:15) አዎን፣ ለምሥራቹ አዎንታዊ ምላሽ የሰጡና የታዘዙት ሰዎች ምሥራቹ ሕይወታቸውን የሚለውጥ ሆኖ አግኝተውታል።

ከኢየሱስ ሞት በኋላ ተከታዮቹ ወንጌሉን መስበካቸውን ቀጠሉ። ስለ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ትንሣኤ እንዳገኘና በሰማይ በአምላክ ቀኝ እንደተቀመጠ እንዲሁም ፍጹም የሆነውን ሰብዓዊ ሕይወቱን ለሰው ዘር ሲል መሥዋዕት አድርጎ እንዳቀረበ የሚገልጸውን አስደሳች ዜና ጨምረው ይናገሩ ነበር። በምድር ሁሉ ላይ እንዲገዛ በአምላክ የተመረጠ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ በመሆን የአምላክን ጠላቶች የሚያጠፋና ምድርን ወደ ገነትነት የሚመልስ የአምላክ ወኪል ይሆናል።—ሥራ 2:32-36፤ 2 ተሰሎንቄ 1:6-10፤ ዕብራውያን 9:24-28፤ ራእይ 22:1-5

በዛሬው ጊዜ ምሥራቹ ሌላም ነገር ይጨምራል። ከትንቢቱ ፍጻሜ በተገኙት ማስረጃዎች መሠረት አሁን ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፤ የምንኖረውም በዚህ የነገሮች ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ውስጥ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5፤ ራእይ 12:7-12) መንግሥቲቱ በአምላክ ጠላቶች ላይ እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ በፍጥነት እየቀረበ ነው። ከዚህ የተሻለ ምን ዜና ሊኖር ይችላል?

በሚቀጥለው ርዕሰ ትምህርት ወንጌሉ ምን ያህል ኃያል እንደሆነ እንመለከታለን። ወንጌሉ በክፉ መናፍስት ተይዛ የነበረችን ሴት ነፃነት እንድታገኝ ረድቷታል። በስርቆት ተጠላልፎ የነበረ አንድ ሰውም ደስታ እንዲያገኝ ረድቶታል። ምሥራቹን ሰምተህ ከታዘዝከው አንተንም በጣም ይጠቅምሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ