የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 2/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ‘ይህ ለመታሰቢያ ይሁናችሁ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ፋሲካ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የጌታ እራት—አምላክን የሚያስከብር በዓል
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 2/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

አንድ ክርስቲያን ቢታመም ወይም በጉዞ ላይ ሆኖ በመታሰቢያው በዓል ላይ ለመገኘት ባይችል ከአንድ ወር በኋላ በዓሉን ማክበር ይኖርበታልን?

በጥንቷ እሥራኤል የማለፍ በዓል በየዓመቱ ኒሳን (ወይም አቢብ) በሚባለው የመጀመሪያው ወር 14ኛ ቀን ላይ ይከበር ነበር። በዘኁልቁ 9:​10, 11 ላይ ግን አንድ ልዩ ዝግጅት ተደንግጎ እናገኛለን:- “ለእሥራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው:- ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፣ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፣ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ። በሁለተኛው ወር [ኢያር ወይም ዚፍ በተባለው ወር] በአሥራ አራተኛ ቀን በመሸ ጊዜ ያድርጉት፤ ከቂጣ እንጀራና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።”

ይህ ዝግጅት ለማንኛውም እሥራኤላዊ ወይም ቤተሰብ በሚመቸው ጊዜ የማለፍን በዓል እንዲያከብር ከሁለት አማራጮች ውስጥ (ከኒሳን 14 ወይም ከዚፍ 14) አንዱን እንዲመርጥ እንዳልደነገገ አስተውሉ። የማለፉ በዓል መብል በሁለተኛው ወር እንዲበላ የተደነገገው ዝግጅት ውስን ነበር። በኒሳን 14 ዕለት በሥርዓት ላልነፃ ወይም የበዓሉ ሥነ ሥርዓት ከሚደረግበት የተለመደ ቦታ ርቆ ለሚገኝ እሥራኤላዊ ብቻ የተወሰነ ነበር።

ይህ ዝግጅት በሠፊው እንደተሠራበት የሚገልጸው ተመዝግቦ የሚገኝ ብቸኛ ሁኔታ ታማኙ ንጉሥ ሕዝቅያስ የቂጣውን በዓል አከባበር እንደገና በመለሰበት ጊዜ ነበር። (ካህናቱ ዝግጁ ስላልነበሩና ሕዝቡም ባለመሰባሰቡ) በመጀመሪያው ወር ላይ ለማክበር ጊዜ አልነበረም። ስለዚህ በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን ተከበረ። — 2 ዜና መዋዕል 29:​17፤ 30:​1–5

ከዚህ ያልተለመደ ሁኔታ በቀር አይሁድ የማለፍን በዓል አምላክ በመረጠው ጊዜ ያከብሩ ነበር። (ዘጸአት 12:​17–20, 41, 42፤ ዘሌዋውያን 23:​5) ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የማለፍን በዓል ሕጉ በሚጠይቀው መሠረት ያከብሩ ነበር እንጂ አቅልለው አልተመለከቱትም። ሉቃስ “ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ፤ [ኢየሱስም] ጴጥሮስንና ዮሐንስን :- ፋሲካን እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን ብሎ ላካቸው” በማለት ዘግቧል። — ሉቃስ 22:​7, 8

በዚያን ዕለት ኢየሱስ ክርስቲያኖች የጌታ ራት ብለው የሚጠሩትን ዓመታዊ የበዓል አከባበር አቋቋመ። ክርስቲያኖች በጌታ ራት ላይ መገኘት አለባቸው ቢባል ከልክ በላይ የተጋነነ ሊሆን አይችልም። በዓመቱ ውስጥ ለይሖዋ ምስክሮች ከቀናት ሁሉ የሚበልጠው ቀን ይኸኛው ነው። ይህ የሆነበትን ምክንያት የኢየሱስ ቃላት ያሳያሉ። እርሱ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሏል። (ሉቃስ 22:​19) በመሆኑም እያንዳንዱ የይሖዋ ምስክር የበዓሉን ዕለት ከሌሎች ቀጠሮዎች ሁሉ ነፃ ለማድረግ ከወራት አስቀድሞ ዕቅድ ማውጣት ይኖርበታል። የዘንድሮው የጌታ ራት ማክሰኞ ሚያዝያ 6, 1993 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይከበራል።

በጣም ልዩ የሆኑ ሁኔታዎች ለምሳሌ ልዩ ሕመም ወይም በጉዞ ላይ መዘግየትን የመሳሰሉ ያልታሰቡ አንዳንድ ሁኔታዎች አንድን ክርስቲያን ከበዓሉ ሊያስቀሩት ይችላሉ። ታዲያ በእንዲህ ዓይነቱ ጊዜ ምን መደረግ ይኖርበታል?

በበዓሉ ሥነ ሥርዓት ወቅት ያልቦካው ቂጣና ቀይ የወይን ጠጅ በተሰብሳቢዎቹ ፊት እንዲያልፍ ይደረጋል። በአምላክ መንፈስ ቅዱስ የተቀቡትና ለሰማያዊ ሕይወት የተመረጡትም ይካፈላሉ። (ማቴዎስ 26:​26–29፤ ሉቃስ 22:​28–30) በየዓመቱ ከቂጣውና ከወይኑ ይካፈል የነበረ አንድ ክርስቲያን በዚህ ዓመት ግን ታሞ በቤት ወይም በሆስፒታል ቢተኛ ከጉባኤ ሽማግሌዎች አንዳቸው ከቂጣውና ከወይኑ ሊወስዱለትና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሊያወያዩትና ከምሳሌያዊው ቂጣና ወይን እንዲካፈል ሊያቀርቡለት ይችላሉ። አንድ ቅቡዕ ክርስቲያን ከራሱ ጉባኤ በራቀ ቦታ የሚገኝ ከሆነ በበዓሉ ዕለት በሚገኝበት አካባቢ ባለው ጉባኤ ለመገኘት ዝግጀት ሊያደርግ ይችላል።

ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አንድ ቅቡዕ የሆነ ክርስቲያን የጌታን ራት በዘኁልቁ 9:​10, 11 በተሰጠው ትዕዛዝና በ2 ዜና መዋዕል 30:​1–3, 15 ላይ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት 30 ቀን (አንድ የጨረቃ ወር) አሳልፎ እንዲያከብር የሚገደድበት ሁኔታ የሚያጋጥመው በጣም ጥቂት ነው።

በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ተስፋ ያላቸው ከኢየሱስ የ“ሌሎች በጎች” ክፍል የሆኑ ክርስቲያኖች ግን ከቂጣውና ከወይኑ እንዲካፈሉ አልታዘዙም። (ዮሐንስ 10:​16) በዓመታዊው የጌታ ራት በዓል ላይ መገኘት አስፈላጊ ቢሆንም ከምሳሌአዊው ቂጣና ወይን አይካፈሉም። ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ ቢታመም ወይም በጉዞ ላይ ሆኖ በዚያ ምሽት ከማንኛውም ጉባኤ ጋር ለማክበር ባይችል እርሱ ወይም እርሷ ተገቢ የሆኑትን ጥቅሶች (ኢየሱስ በዓሉን ያቋቋመበትን ዕለት የሚመለከቱትን ጭምር) በግሉ ወይም በግሏ ሊያነቡና በዓለም ዙሪያ በሚካሄደው በዚህ በዓል ላይ ይሖዋ በረከቱን እንዲሰጥ ሊጸልዩ ይችላሉ። ከወር በኋላ ሌላ ስብሰባ ወይም የተለየ የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት ለማድረግ ማንኛውንም ዝግጅት ማድረግ ግን አስፈላጊ አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ