የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 3/1 ገጽ 3
  • መዘግየት ሕይወት ያሳጣል!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መዘግየት ሕይወት ያሳጣል!
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የእሳተ ገሞራ አደጋ ባንዣበበበት አካባቢ መኖር
    ንቁ!—2007
  • ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ነቅታችሁ ኑሩ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • አምላክ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሰምተህ እርምጃ ት ወ ስ ዳ ለ ህ ን ?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • መንትዮቹ ሕንጻዎች የተደረመሱበት ዕለት
    ንቁ!—2002
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 3/1 ገጽ 3

መዘግየት ሕይወት ያሳጣል!

ሰባት አዋቂዎችና ስድስት ትናንሽ ልጆች ያሉባቸው ሦስት ቤተሰቦች ሕይወታቸውን ለማዳን በፍጥነት እየሮጡ ነበር። ከላይ ከሚዘንብባቸው ድንጋይ ለማምለጥ ሲሉ በአንድ ሰው ቤት ውስጥ አንዳቸው በሌላው ላይ ተረባርበው ቆይተው ነበር። ይሁን እንጂ ይሰማ የነበረው የድንጋይ ውርጅብኝ ጸጥ እንዳለ አዲስ አስፈሪ ነገር ተፈጠረ። የሚያፍን አመድ የተሞላ ጥቁር ደመና ማንዣበብ ጀመረ። አሁን ከመሮጥ ሌላ ምንም ዓይነት አማራጭ አልነበረም።

ስንቅ ያለበትን ቀረጢት በትከሻው አንግቶ ከፊት እየመራ ይሮጥ የነበረው ሰው አሽከር ሳይሆን አይቀርም። የአራትና የአምስት ዓመት አካባቢ ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንዶች ልጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው እየሮጡ ይከተሉት ነበር። ሌሎቹ ደግሞ በፍርሐት ተውጠው እየተደናበሩና እየተደናቀፉ ሕይወታቸውን ለማዳን በፍጥነት ይከተሉአቸዋል። ለመተንፈስ ሞከሩ፤ ወደ ውስጥ የሳቡት ግን አየር ሳይሆን እርጥብ አመድ ነበር። አሥራ ሦስቱም አንድ በአንድ ወድቀው ተዘረሩ። በመጨረሻም ይወርድባቸው የነበረው አመድ ቀበራቸው። 2,000 ዓመት ከሚያክል ጊዜ በኋላ የመሬት ቁፋሮ አጥኚዎች አስከሬናቸውን አግኝተው በመጨረሻው የደረሰባቸውን አሳዛኝ ዝርዝር ሁኔታ አጥንተው በግልጽ እስኪረዱ ድረስ ተረስተው ኖሩ።

እነዚህ 13 ሰዎች ነሐሴ 24 ቀን 79 እዘአ በኢጣልያ አገር በጥንታዊቱ የፖምፔ ከተማ በግምት ከሞቱት 16,000 ሰዎች ጥቂቶቹ ብቻ ነበሩ። ከከተማው ነዋሪዎች ብዙዎቹ የቬሱቪየስ ተራራ የመጀመሪያውን ፍንዳታ ካሰማ በኋላ ከከተማው ሸሽተው ስለነበረ ከጥፋቱ ለማምለጥ ችለዋል። ሳይሸሹ የዘገዩት በአብዛኛው ቤታቸውንና ንብረታቸውን ትተው ለመሄድ ያልፈለጉ ሀብታም ሰዎች ግን 6 ሜትር የሚያክል ጥልቀት ባለው የድንጋይና የአመድ ክምር ተቀበሩ።

2,000 ዓመት ከሚያክል ጊዜ በፊት በፖምፔ የደረሰው አደጋ ዘመኑ ያለፈበት የጥንት ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ በብዙ መልኩ በዛሬው ዘመን በመላው የሰው ልጅ ፊት የተደቀነውን ሁኔታ ይመስላል። በቬሱቪየስ ተራራ ተሰምቶ ከነበረው ጉርምርምታ ይበልጥ የጎላ ምድር አቀፍ ምልክት ይህ የአሁኑ የዓለም ሥርዓት ጥፋት እንደተደቀነበት በማስጠንቀቅ ላይ ነው። ከጥፋቱ ለመዳን ከፈለግን አሁንኑ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል። መዘግየት ሞት ያስከትልብናል። ይህ ጥፋት መምጣቱን የሚያስጠነቅቀው ምልክት ምን እንደሆነና እንዴት ያለ የጥበብ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባን በሚቀጥለው ርዕሰ ትምህርት እንመረምራለን።

[ምንጭ]

Cover photo by National Park Service

[ምንጭ]

Soprintendenza Archeologica di Pompei

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ