የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 5/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው?”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ክርስቶስ በመንግሥቱ በበጎችና በፍየሎች ላይ ይፈርዳል
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 5/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ሰዎች አሁን እውነተኛውን ክርስትና ባይቀበሉና ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ቢሞቱ ትንሣኤ ያገኛሉን?

ዋጋ የሚኖረው ይሖዋ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በመጨረሻው የሚበይነው ፍርድ መሆኑን በመቀበል ማንኛውንም ዓይነት የመፍረድ ዝንባሌ ሁላችንም ብንገታው ጥሩ ነው። (ዮሐንስ 5:​22፤ ሥራ 10:​42፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:​1) ሆኖም ቅዱሳን ጽሑፎች ከላይ ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣሉ።

የአምላክ መንግሥት ምሥራች በዓለም ዙሪያ መሰበኩ ‘የኢየሱስን መገኘት’ ከሚያሳውቀው ዓቢይ ምልክት አንዱ ክፍል ነው። ይህ ምልክት ከዚህ መቶ ዘመን መባቻ አንስቶ በግልጽ ሲታይ ቆይቷል። የስብከቱ ሥራ በሁሉም ብሔራት የሚገኙትን ሰዎች “በጎች” እና “ፍየሎች” አድርጎ በመከፋፈል ኢየሱስ የሰጠው ምሳሌ ፍጻሜውን እንዲያገኝ አድርጓል። ይህ የስብከትና ሰዎችን በሁለት ወገን የመለያየት ሥራ ሙሉ በሙሉ ሲፈጸም የአሁኑ ክፉ የነገሮች ሥርዓት “በታላቁ መከራ” አማካኝነት ወደ ፍጻሜው ይመጣል። — ማቴዎስ 24:​3, 21, 22፤ 25:​31–46

የመንግሥቱን መልእክት አልቀበልም ያለና ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት የሞተ የማንኛውም ሰው ዕጣ ከፍየሎች ጋር መመደቡንና አለመመደቡን የሚፈርዱት ይሖዋ እና ልጁ ብቻ ይሆናሉ። ፍየሎቹ “ወደ ዘላለም ጥፋት” እንደሚሄዱ ኢየሱስ ተናግሮአል። ስለዚህ ፍየል ናቸው ብሎ አምላክ የበየነባቸው ሰዎች ትንሣኤ አያገኙም ብለን ልንደመድም እንችላለን። እነዚህ ሰዎች በታላቁ መከራ ወቅት “በዘላለም ጥፋት” እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ሰዎች የሚያገኙት ዓይነት ፍርድ ያገኛሉ። — 2 ተሰሎንቄ 1:​9

ይሁን እንጂ በእነዚህ “መጨረሻ ቀኖች” ወቅት ከመሞታቸው በፊት እውነትን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ ማድረግ ይችሉ ዘንድ የመንግሥቱን መልእክት ለመስማት በቂ አጋጣሚ ያገኙ የሚመስሉ ሰዎችስ ምን ይሆናሉ? — 2 ጢሞቴዎስ 3:​1

የስብከቱ ሥራ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት የሚሞቱ ብዙዎች ትንሣኤ እንደሚያገኙ ከአንዳንድ ጥቅሶች መረዳት ይቻላል። በራእይ 6:​7, 8 ላይ የሚገኘው ስለ ምሳሌያዊ ፈረሰኞች የተሰጠው መግለጫ ይህን ይጠቁምልናል። ብዙ ሰዎች የጦርነት፣ የረሃብና የቸነፈር ሰለባ በመሆን ሞተዋል። እነዚህን “የሞት” ሰለባዎች ሰብስቦ የሚውጣቸው “ሲኦል” ስለሆነ በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ውስጥ ሲኦል በውስጡ ያሉትን ሙታን በሚሰጥበት ጊዜ ትንሣኤ ያገኛሉ። (ራእይ 20:​13) ከሞት ከሚነሱት መካከል በርከት ያሉት ከመሞታቸው በፊት ከመንግሥቱ መልእክት ጋር መጠነኛ ትውውቅ የነበራቸው ይሆኑ ይሆናል።

ኢየሱስ እነማን በግ መሰሎች እነማን ደግሞ ፍየል መሰሎች እንደሆኑ የመወሰኑን ሥራ ለሰዎች ባለመተዉ ምን ያህል አመስጋኞች ልንሆን ይገባል? አንድ ሰው ምሥራቹን ሰምቶ ለመቀበል የሚያበቃ ምን ያህል አጋጣሚ አግኝቶ እንደነበረ ለመገምገም ፍጽምና የሌላቸው ሰዎች አይችሉም። የልቡ ሁኔታ ምን እንደነበረ ወይም ደግሞ በትክክል ጽድቅን ያፈቅር የነበረ መሆኑን ለማወቅ እንችላለንን? ለእውነት ያሳየው ምላሽ በቤተሰቡ፣ በነበረው ሃይማኖታዊ አስተዳደግ ወይም በሌሎች ተጽዕኖዎች ምን ያህል እንደተነካ ለመለካት እንችላለንን? እንደማንችል ግልጽ ነው። ነገር ግን ይሖዋና ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ነገሮች ለመገምገምና ፍጹም፣ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነ ፍርድ ለመስጠት ችሎታው እንዳላቸው እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። — ዘዳግም 32:​4፤ ኢሳይያስ 11:​1–5

ስለዚህ በቅርቡ ከሞቱት ሰዎች መካከል ከሞት ይነሳሉ ወይም አይነሱም ብለን የግምት ሐሳብ የምንሰጥበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ይህን እንድናደርግ ሥልጣን አልተሰጠንም። (ከሉቃስ 12:​13, 14 ጋር አወዳድር።) ጻድቅ ፈራጆች የሆኑት ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጡትን ውሳኔ መጠበቁ በጣም የተሻለ ነው። ይህም የይሖዋ አገልጋዮች ሆነን ስንኖር የበለጠ የአእምሮ ሰላም ይሰጠናል። በተጨማሪም ‘አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት እንድናደርግና’ ኢየሱስ ‘እንዲጠብቁ ያዘዘውን እንድናስተምር’ በተሰጠን ሥራ ላይ የበለጠ እንድናተኩር ይረዳናል። — ማቴዎስ 28:​19, 20

[ምንጭ]

Leicester sheep, Meyers

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ