የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 10/1 ገጽ 29-30
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • የአንድን አስፋፊ የማያምን የትዳር ጓደኛ መርዳት ትችላላችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • የንግድ ሥራህ ምን መሥዋዕት እንድትከፍል ያስገድድሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 10/1 ገጽ 29-30

የአንባብያን ጥያቄዎች

መጽሐፍ ቅዱስ “ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ” ስለሚል አንድ ክርስቲያን ከማያምን ሰው ጋር የንግድ ሸሪክ ቢሆን ተገቢ ነውን?

ይህንን ምክር በ2 ቆሮንቶስ 6:​14–16 ላይ እናገኘዋለን:- “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው?”

ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ከማያምን ሰው ጋር የንግድ ሽርክናን በሚመስሉ ነገሮች እንዳይካፈሉ ለመከልከል አስቦ ይህንን ምክር እንደጻፈው አድርገን ለማመን ምንም ምክንያት የለንም። ይሁን እንጂ ምክሩ እንደዚህ ባለው ጉዳይ ላይና በሌሎች የኑሮ ዘርፎች ላይም ይሠራል።

ጳውሎስ ይህንን ምክር የጻፈው በጥንቷ የቆሮንቶስ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ክርስቲያን ወንድሞቹ ነበር። ብልሹ በሆኑ ነገሮች በተሞላችው ከተማ ውስጥ ሲኖሩ በየዕለቱ የሚገጥሟቸውን ስነ ምግባራዊና መንፈሳዊ አደጋዎች መታገል ነበረባቸው። ካልተጠነቀቁ በስተቀር ጥሩ ላልሆኑ ተጽእኖዎች መጋለጡ “የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን” ለመሆን ያደረጉትን ቁርጥ ውሳኔ ቀስ በቀስ ሊያዳክምባቸው ይችል ነበር። — 1 ጴጥሮስ 2:​9

ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 6:​14–16 ላይ የሚገኘውን ምክር ከመጻፉ በፊት በቆሮንቶስ ጉባኤ በሚገኙት ወንድሞቹ መካከል የተነሣውን ከበድ ያለ ችግር ጠቅሶ ነበር። ከባድ ብልግና በመካከላቸው ተፈጽሞ ዝም በማለታቸው ጳውሎስ ንስሐ ያልገባው ኃጢአተኛ ከጉባኤው እንዲወገድ መመሪያ አስተላለፈ። (1 ቆሮንቶስ 5:​1) መጥፎ ባልንጀርነት ወይም ገደብ በሌለው መንገድ ወደዚህ ዓለም ሥነ ምግባራዊ አዘቅት ጠልቆ መግባት ክርስቲያኖችን ሊነካቸው እንደሚችል ይህ ሰው የሠራው መጥፎ ድርጊት አሳይቷል።

የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ከተወገደው ሰው ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ማቆም ነበረባቸው። ነገር ግን እንደዚያ ማለት ሙት ባሕር አጠገብ በሚገኘው ኩምራን ወደተባለው ስፍራ እንደገቡት አይሁዳውያን የመነኮሳት መናፍቅ ከማያምኑ ሰዎች ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነታቸውን ፈጽሞ ያቋርጡ ማለት ነውን? እስቲ ጳውሎስ ይመልስልን:- “ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን . . . አላልሁም፤ ይህስ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር።” — 1 ቆሮንቶስ 5:​9, 10

የእነዚህ ቃላት ትርጉም ግልጽ ነው። ክርስቲያኖች በዚህች ፕላኔት ላይ ነዋሪዎች እንደመሆናቸው በስነ ምግባር ዝቅ ያሉና የአቋም ደረጃቸው የተለየ ከሆኑት የማያምኑ ሰዎች ጋር በየዕለቱ እንደሚገናኙና አብረው እንደሚኖሩ ጳውሎስ ተገንዝቧል። በመሠረቱ ይህንን ማስወገድ የማይቻል ስለሆነ እንደዚህ ያለው ንክኪ ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ንቁዎች መሆን ይገባቸዋል።

እስቲ አሁን ደግሞ እንደገና የጳውሎስን ሁለተኛ ደብዳቤ እንመርምረው። ቅቡዓን ክርስቲያኖች ክርስቶስን ተክተው የሚሠሩ አምባሳደሮች በመሆን ብቃቱን ያሟሉ የአምላክ አገልጋዮች መሆናቸውን ጳውሎስ ጠቅሷል። አገልግሎታቸው በመጥፎ እንዲታይ ሊያደርግ የሚችል ምንም ዓይነት የመሰናከያ ምክንያት እንዳይሆኑ መጠንቀቅ እንዳለባቸው ነግሯቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 4:​1 እስከ 6:​3) እንደ መንፈሳዊ ልጆቹ ለነበሩት ለቆሮንቶስ ወንድሞቹ ፍቅራቸውን እንዲያሰፉት በቀጥታ አሳስቧቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 6:​13) ከዚያ በኋላ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ” በማለት አሳሰባቸው። ይህንን ነጥብ ከበድ አድርጎ ለመግለጽ መልስ የማይሰጥባቸው ነገሩን ለማጤን የሚረዱ ጥያቄዎች አከታትሎ አቀረበ።

በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ እንደሚያሳየው ጳውሎስ እንደ ንግድ ሥራ ወይም ተቀጥሮ ስለ መሥራት ባለ በአንድ የተወሰነ የኑሮ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ሥራ ላይ ሊውል የሚገባው አንድ ዓይነት የሕግ ሥርዓት አላወጣም። ከዚህ ይልቅ ለሚወዳቸው ወንድሞች ሰፋ ያለ፣ ጤናማና ሊረዳ የሚችል ምክር ማቅረቡ ነበር።

ለምሳሌ ያህል ለማግባት ፍላጎት ላለው ለአንድ ክርስቲያን ይህ ምክር ሊሠራ ይችላልን? አዎን፣ ሊሠራ ይችላል። ሐዋርያው በመጀመሪያው ደብዳቤው ላይ ለማግባት የሚያስቡትን “በጌታ” ብቻ እንዲያገቡ መክሯቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 7:​39) ይህንን ምክር መከተል ጥበብ መሆኑን ቆይቶ በ2 ቆሮንቶስ 6:​14–18 በጻፈው ደብዳቤው ላይ ጎላ አድርጎታል። አንድ ክርስቲያን የይሖዋ አገልጋይ ያልነበረና የክርስቶስ ተከታይ ያልሆነን ሰው ለማግባት ቢያስብ እርሱ ወይም እርሷ ከማያምን ጋር ለመቆራኘት እያሰቡ ነው ማለት ነው። (ከዘሌዋውያን 19:​19 እና ከዘዳግም 22:​10 ጋር አወዳድር።) በግልጽ እንደሚታየው አቻ አለመሆናቸው መንፈሳዊ ነገሮችንም ጨምሮ ብዙ ችግር ያስከትላል። ለምሳሌ ያህል የማያምነው የትዳር ጓደኛ በአሁኑ ሰዓት ወይም ወደፊት የሐሰት አምላክ አምልኮን ይከተል ይሆናል። ጳውሎስ “ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው?” በማለት ነገሩን ለማመዛዘን የሚረዳ ጥያቄ አቅርቧል።

ስለ ሌላው የኑሮ ገጽታ ማለትም ከማያምን ሰው ጋር የንግድ ሽርክና ስለ መክፈትስ ምን ሊባል ይቻላል? አንድ ክርስቲያን በአንዳንድ ሁኔታዎች ኑሮን ለመቋቋምና ቤተሰብን ለመንከባከብ ክርስቲያን ካልሆነ ሰው ጋር የንግድ ሽርክና መግባት እንደሚያስፈልገው ሆኖ ይሰማው ይሆናል። (1 ጢሞቴዎስ 5:​8) እስቲ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ተመልከት:-

አንድ ክርስቲያን አንድ ዓይነት ዕቃ ለመሸጥ ይፈልግ ይሆናል፤ ነገር ግን ያለው አማራጭ አስፈላጊዎቹን ዕቃዎች ወይም ለሥራው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማግኘት ከሚችል የማያምን ሰው ጋር መሻረክ ሊሆን ይችላል። ሌላው ክርስቲያን ደግሞ የእርሻ ሥራ ሊሠራ ወይም (ከብት ሊያረባ) ይፈልግ ይሆናል። ይሁን እንጂ መሬት ላያገኝ ስለሚችል መሬቱን ቢጠቀምበት ትርፉን ሊካፈሉ የሚችሉበት አንድ ዓይነት ስምምነት ላይ በመድረስ ተጣምሮ መሥራት ይጀምር ይሆናል። ቄሣር የተወሰኑ የንግድ ፈቃዶችን ብቻ ለቧንቧ ሥራ የሚሰጥ በመሆኑና እነዚያም ስለተወሰዱ ምናልባት አንድ ሌላ ክርስቲያን የሚኖረው ምርጫ የንግድ ፈቃድ ካለው የማያምን ዘመዱ ጋር ተጣምሮ የቧንቧ ሥራ መጀመር ይፈልግ ይሆናል። — ማርቆስ 12:​17

እነዚህ ምሳሌ እንዲሆኑ የቀረቡ ብቻ ናቸው። ያሉትን አማራጮች ሁሉ ለመዘርዘር ወይም ይህን ደግፈን ያንን ለመንቀፍ በመሞከር ላይ አይደለንም። ነገር ግን እነዚህን ምሳሌዎች ወደ አእምሮአችሁ በማምጣት የ2 ቆሮንቶስ 6:​14–18 ምክር ቸል ሊባል የሚገባው አለመሆኑ አይታያችሁምን?

ዘመድም ይሁን አይሁን ከማያምን ሰው ጋር የንግድ ሽርክና ውስጥ የገባ ክርስቲያን ያልታሰቡ ችግሮችና ፈተናዎች ሊያጋጥሙት ይችላል። ምናልባትም የመንግሥትን ሕግ ቢጥስም ጥሩ ትርፍ የማግኛው መንገድ ገቢን አሳንሶ ሪፖርት ማድረግና የሠራተኞችን ስም ዝርዝርና ገቢያቸውን የሚያሳየውን መዝገብ መደበቅ ነው ብሎ ሊደመድም ይችላል። በሕጋዊ ደረሰኝ ላይ ሳይመዘግብ ለደንበኞቹ ዕቃዎችን ለመሸጥም ይፈልግ ይሆናል። አንድ ክርስቲያን እንደዚህ በመሰለው ነገር መካፈል ወይም ተመሳሳይ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም ይገባዋልን? የቀረጥ መቀበያ ወረቀቶች ላይ ወይም ንግዳቸውን እንዴት እንደሚያከናውኑ የሚገልጹበት ሌላ ሕጋዊ ሰነድ ላይ ሁለቱም መፈረም የሚኖርባቸው ጊዜ ሲመጣ ክርስቲያኑ ምን ያደርጋል? — ዘጸአት 23:​1፤ ሮሜ 13:​1, 7

ወይም የማያምነው የንግድ ሽርካ ከአረመኔ በዓሎች ጋር የተያያዙ ዕቃዎችን ሱቁ ውስጥ ለሽያጭ ያስቀምጥ፣ በኩባንያው ስም የዓመት በዓል ካርዶችን ይልክ፣ እንዲሁም የንግድ ድርጅቱን በሃይማኖታዊ በዓሎች ወቅት ማስጌጥ ይፈልግ ይሆናል። ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና” በማለት ጥያቄ አቅርቧል። “ስለዚህም ጌታ:- ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኩስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ:- እኔም እቀበላችኋለሁ” የሚሉት ሐሳቦች ምንኛ ተገቢ ናቸው! (2 ቆሮንቶስ 6:​16, 17) ይህን ጥበብ የተሞላበት ምክር በሥራ ላይ በማዋል ብዙ ክርስቲያኖች በተቻለ መጠን ችግር የማይፈጥርባቸውን የሥራ ዓይነት መርጠዋል። — ዕብራውያን 13:​5, 6, 18

ክርስቲያኖች የአንድ ንግድ ድርጅት ባለቤቶችም ይሁኑ ተቀጥረው የሚሠሩ፣ በሰብአዊ ሥራቸው ላይ ምን በመሥራት ላይ እንዳሉ የመከታተል ወይም የመመርመር ኃላፊነት ጉባኤው አልተሰጠውም። እርግጥ አንድ ክርስቲያን በሥራ ቦታው ላይ የሐሰት አምልኮን የሚያራምድ ሆኖ ቢገኝ ወይም በአንድ ዓይነት ውሸት ወይም ሥርቆት ተካፍሎ ቢገኝ ጉባኤው የይሖዋን የአቋም ደረጃዎች ለማስከበር እርምጃ መውሰድ ይኖርበ⁠ታል።

ይሁን እንጂ እዚህ ላይ ቁልፍ ነጥቡ ጳውሎስ በመንፈስ አነሣሽነት “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ” ብሎ የጻፈው ምክር ክርስቲያኖች ችግሮችንና የፍርድ እርምጃ የሚያስከትሉ ነገሮችን እንዲሸሹ ይረዳቸዋል። ጥበበኛ ክርስቲያኖች ይህንን ምክር ይሠሩበታል፣ ምርጫቸውም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዲያፈርሱ የሚደርስባቸውን ተጽእኖ በሚያባብሱ ሁኔታዎች ውስጥ አለመግባት ነው። አንድ ሰው ከማያምን ጋር አብሮ መሥራት እንደሚኖርበት ሆኖ ከተሰማው ምርጫው የሚያስከትልበትን ነገር ሁሉ ለመቀበል ኃላፊነቱን እንደሚወስድ በአእምሮአቸው በመያዝ ሌሎች በእሱ ላይ ለመፍረድም ሆነ እሱን ለመተቸት መቸኮል የለባቸውም። በመሠረቱ ጳውሎስ ከማያምን ጋር መሥራትን የሚመለከት ጉባኤውም ተከታትሎ ሊያስፈጽመው የሚችል አንድ ዓይነት ሥርዓት ማውጣቱ አልነበረም። ቢሆንም ምክሩ ቸል ሊባል አይገባም። አምላክ ይህ ምክር በመንፈስ አነሣሽነት እንዲጻፍና ተመዝግቦ እንዲቆይልን ያደረገው ለእኛው ጥቅም ነው። ብንሠራበት ጥበበኞች እንሆናለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ