የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 1/15 ገጽ 5-7
  • በቅርቡ ጦርነት የሌለበት ዓለም ይመጣል!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በቅርቡ ጦርነት የሌለበት ዓለም ይመጣል!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአእምሮ ውስጥ ሰላም እንዲሰርጽ ማድረግ
  • አምላክ ሰላምን የሚያመጣው እንዴት ነው?
  • ሃይማኖታዊ እንቅፋቶችን ማስወገድ
  • እውነተኛ ሰላም—ከየት ይገኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • እውነተኛውን ሰላም ፈልጉ፣ ተከተሉትም!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ጦርነት የሚያከትምበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • “የአምላክ ሰላም” ልባችሁን ይጠብቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 1/15 ገጽ 5-7

በቅርቡ ጦርነት የሌለበት ዓለም ይመጣል!

ታኅሣሥ 24, 1914 ጂም ፕሪንስ የተባለ አንድ ወጣት እንግሊዛዊ ወታደር ለሁለቱም ጦሮች ድንበር የሆነን ቦታ አቋርጦ የጀርመን እግረኛ ጦር አባል የሆነ አንድ ወታደር ለማነጋገር ሄደ። የጀርመን ወታደር የሆነው “እኔ ጀርመናዊ ነኝ አንተም ከጀርመን የሄድክ እንግሊዛዊ ነህ። የምንዋጋው ለምንድን ነው?” አለው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ፕሪንስ “የዚህን ጥያቄ መልስ አሁንም አላውቅም” ሲል ተናግሯል።

በ1914 በአንድ ልዩ ሳምንት የእንግሊዝና የጀርመን ወታደሮች የወዳጅነት የእግር ኳስ ግጥሚያ አድርገዋል፣ የገና ስጦታም ሳይቀር ተለዋውጠዋል። እርግጥ ይህ የተኩስ ማቆም ስምምነት በባለ ሥልጣኖች የተፈቀደ አልነበረም። የጦር ጄኔራሎች “ጠላት” ጨካኝ አረመኔ ነው የሚለው የጦርነት ፕሮፓጋንዳ ሐሰት መሆኑን ወታደሮቻቸው እንዲያውቁ አይፈልጉም ነበር። አልበርት ሞርን የተባለ የእንግሊዝ ወታደር “የተኩስ ማቆሙ ለሌላ ሳምንት ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ ጦርነቱን እንደገና ለመጀመር በጣም አስቸጋሪ ይሆን ነበር” ሲል ትዝታውን ገልጿል።

በፈቃደኝነት ተደርጎ የነበረው ይህ ተኩስ አቁም፣ ሥልጠና የተሰጣቸው ብዙ ወታደሮችም እንኳ ሳይቀሩ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን እንደሚናፍቁ ያሳያል። የጦርነትን አሰቃቂነት ያወቁ አብዛኞቹ ወታደሮች “ጦርነትን ያላወቀ ወደ ጦር ሜዳ ይሂድ” በሚለው የእስፓኝ ምሳሌ እንደሚስማሙ የታወቀ ነው። የዓለም ሕዝብ አስተያየቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ አብዛኛው ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እንደሚመርጥ አያጠራጥርም። ታዲያ ለሰላም ያለው ይህ ዓለም ዓቀፋዊ ምኞት ጦርነት የሌለበት ዓለም ሊያስገኝ የሚችለው እንዴት ነው?

ጦርነት ከመጥፋቱ በፊት የአስተሳሰብ ለውጥ መደረግ አለበት። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ያወጣው የመተዳደሪያ ደንብ “ጦርነት የሚጀምረው በሰዎች አእምሮ ውስጥ በመሆኑ የሰላም መጠበቂያ ምሽግ መገንባት ያለበትም በሰዎች አእምሮ ውስጥ ነው” በማለት ይገልጻል። ሆኖም ጥርጣሬና ጥላቻ የተስፋፋበት አሁን ያለው ኅብረተሰብ ሰላማዊ ከመሆን ይልቅ ይበልጥ እየተበጠበጠ በመሄድ ላይ ነው።

የሆነው ሆኖ አንድ ቀን አምላክ ራሱ የጽድቅ ዝንባሌ ባላቸው ሰዎች አእምሮ ውስጥ ሰላምን እንደሚቀርጽ ቃል ገብቷል። አምላክ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል እንዲህ ብሏል፦ “በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ሰልፍም [ጦርነትም] ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።”—ኢሳይያስ 2:4

በአእምሮ ውስጥ ሰላም እንዲሰርጽ ማድረግ

እንዲህ ያለ አስደናቂ የአስተሳሰብ ለውጥ ሊደረግ ይችላልን? ሰዎች ጦርነትን ከማሞገስ ይልቅ ሰላም መጠበቅን ይማሩ ይሆንን? የቩልፍጋንግ ኩሲሮን ምሳሌ እንውሰድ። ይህ የ20 ዓመት ጀርመናዊ ‘ጦርነትን አልማርም’ በማለቱ በ1942 በናዚዎች አንገቱን ተቆርጦ ተገድሏል። ለመሞት የመረጠው ለምን ነበር? ቃሉን ባሰፈረበት የጽሑፍ መግለጫ ላይ “ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ” እንዲሁም “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ” የሚሉትን ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረተ ሥርዓቶች ጠቅሶ ነበር። (ማቴዎስ 22:39፤ 26:52) ከዚያም “ፈጣሪያችን ይህን ሁሉ ያጻፈው ለዛፎች ነበርን?” ሲል መርማሪዎቹን አጠንክሮ ጠየቀ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገበው የአምላክ ቃል ‘ኃይል አለው፤’ ይህንንም ወጣት የይሖዋ ምስክር በሕይወቱ ቆርጦ ሰላምን እንዲከተል ገፋፍቶታል። (ዕብራውያን 4:12፤ 1 ጴጥሮስ 3:11) ይሁን እንጂ በዚህ መንገድ ሰላምን የተከተለው ቩልፍጋንግ ኩሲሮ ብቻ አልነበረም። ጄ ኤስ ኮንዌ ዘ ናዚ ፐርስኪውሽን ኦቭ ዘ ቸርችስ ከ1993–45 በተባለው መጽሐፍ የይሖዋ ምስክሮች በቡድን ደረጃ የጦር መሣሪያ ለማንሣት ፈቃደኞች እንዳልነበሩ የናዚ መንግሥት መዝገብ ቤቶች የሚያሳዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እንዲህ ያለው ድፍረት የተሞላበት አቋም መውሰድ በራስ ላይ የሞት ፍርድ እንደመፈረም ያህል የሚቆጠር እንደነበር ኮንዌ ጠቅሰዋል።

ዛሬም ቢሆን የይሖዋ ምስክሮች የዘር ወይም የዜግነት ልዩነት ሳያግዳቸው ሰላምን መከተላቸውን ቀጥለዋል። በዚህ አቋማቸው የቀጠሉት ለምንድን ነው? ምክንያቱም እውነተኞቹ የአምላክ አገልጋዮች ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ወደ ማረሻ መለወጥ ያለባቸው መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ በመማራቸው ነው። ለመኖር በ1987 ወደ እስራኤል የሄደው አሌካንድሮ የተባለ አርጀንቲናዊ ወጣት በበኩሉ ለዚህ ሐቅ የምስክርነት ቃሉን ሊሰጥ ይችላል።

አሌካንድሮ ዩኒቨርሲቲ እየተማረና በልዩ ልዩ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች እየሠራ በአንድ የእስራኤል የሰፈራ መንደር ለሦስት ዓመት ተቀምጧል። በዚህ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ ምርምር ማድረግ ጀመረ። ከሁሉም ይልቅ ሰዎች በሰላምና በፍትህ ተደስተው የሚኖሩበትን ዓለም ለማየት ይናፍቅ ነበር። አሌካንድሮ በትውልዱ አይሁዳዊ ቢሆንም በአይሁዶችና በአረቦች መካከል ይሠራ ነበር። ቢሆንም የትኛውንም ወገን አያስበልጥም ነበር።

በ1990 ከይሖዋ ምስክሮች ጋር በማጥናት ላይ የነበረ አንድ ጓደኛው በሃይፋ ሙሉ ቀን በሚደረግ ስብሰባ እንዲገኝ አሌካንድሮን ጋበዘው። በስብሰባው 600 የሚያህሉ አይሁዶችና አረቦች ተደባልቀው በአንድ ላይ ደስ ብሏቸው በማየቱ በልቡ ‘ሰዎች ሊኖሩበት የሚገባ ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው’ ሲል አሰበ። በስድስት ወራት ውስጥ እርሱ ራሱ የይሖዋ ምስክር ሆነ፤ አሁን አብዛኛውን ጊዜውን የመጽሐፍ ቅዱስን የሰላም መልእክት ለመስበክ ያውለዋል።

አምላክ ሰላምን የሚያመጣው እንዴት ነው?

ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ ከላይ እንደተጠቀሰው ያሉ ልብን የሚነኩ ምሳሌዎች የተለመዱ አይደሉም። ምንም እንኳ አሁን ያለው ሥርዓት ለሰላም የአፍ ድጋፍ ቢሰጥም የጦርነት ዘሮችን ውኃ ያጠጣል። ነዋሪዎቹ ከገቢያቸው ከ7 እስከ 16 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ ለጦር መሣሪያና ቤታቸውን ለመጠበቅ በሚያጠፉበት አካባቢ ለመኖር ትፈልጋለህን? በቅርብ ዓመታት መንግሥታት ለወታደራዊ ጉዳዮች የመደቡት ወጪ ልክ ይህንኑ እንደሚያደርጉ ያሳያል። አምላክ ‘በብዙ ሰዎች መካከል ያሉትን ሁኔታዎች እስከሚያስተካክልበት’ ጊዜ ድረስ መላው የሰው ዘር ሰይፉን ቀጥቅጦ ወደ ማረሻ እንደማይለውጥ የኢሳይያስ ትንቢት መናገሩ አያስደንቅም። አምላክ ሁኔታውን የሚያስተካክለው እንዴት ነው?

ሁኔታዎችን የምታስተካክለው ዋነኛዋ መሣሪያ የይሖዋ አምላክ መንግሥት ነች። ነቢዩ ዳንኤል ‘አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት እንደሚያቋቁም’ አስቀድሞ ተንብዮአል። ይህች መንግሥት “እነዚያንም መንግሥታት [ዓለማዊ መንግሥታትን] ሁሉ ትፈጫቸዋለች፣ ለዘላለምም ትቆማለች” በማለት ዳንኤል አክሎ ተናግሯል። (ዳንኤል 2:44) እነዚህ ቃላት ወደፊት የአምላክ መንግሥት መላዋን ምድር በእርግጥ እንደምትቆጣጠር ያሳያሉ። መንግሥቲቱ ብሔራዊ ድንበሮችን በማስወገድ በአገሮች መካከል የሚታየው ፉክክር ጊዜ ያለፈበት ነገር እንዲሆን ታደርጋለች። ከዚህም በላይ የመንግሥቲቱ ተገዢዎች ‘ከይሖዋ የተማሩ’ ስለሚሆኑ ሰላማቸው “ብዙ ይሆናል።” (ኢሳይያስ 54:13) ኢየሱስ “መንግሥትህ ትምጣ” ብለን ወደ አምላክ እንድንጸልይ መናገሩ አያስገርምም!—ማቴዎስ 6:10

ሃይማኖታዊ እንቅፋቶችን ማስወገድ

በተጨማሪም አምላክ ሃይማኖታዊ የሰላም እንቅፋቶችን ያስወግዳል። ሃይማኖት በታሪክ ከተደረጉት ጦርነቶች ሁሉ ለረጅም ጊዜ ለቆዩት ማለትም በ1095 እዘአ በጳጳስ ኧርባን ሁለተኛ ለተከፈቱት “የመስቀል ጦርነቶች” ወይም “ቅዱስ ጦርነቶች” በመባል ለሚታወቁት ጦርነቶች ምክንያት ሆኗል።a በያዝነው መቶ ዘመን ቀሳውስት ጦርነት እንዲነሣና ሃይማኖት ነክ ያልሆኑ ጦርነቶችንም እንኳ ሳይቀር እንዲቀሰቀሱ በመገፋፋትና የሕዝብን ድጋፍ ለማግኘት በሚደረገው ጥረት ቀንደኛ ተዋናይ እየሆኑ መጥተዋል።

ታሪክ ጸሐፊው ፖል ጆንሰን በስም ብቻ ክርስቲያን የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የነበራቸውን ሚና በመጥቀስ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፦ “ቀሳውስት የክርስትናን እምነት ከብሔራዊ ስሜት ለማስቀደም አልቻሉም፤ ብዙውን ጊዜም ፈቃደኞች አልነበሩም። አብዛኞቹ ቀላሉን መንገድ መርጠው ክርስትናን ካገር ፍቅር ጋር እኩል አድርገው ነበር። ከሁሉም የሃይማኖት ወገን የመጡ ወታደሮች በአዳኛቸው በክርስቶስ ስም እርስ በእርሳቸው እንዲገዳደሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ነበር።”

ሃይማኖት ሰላምን ከማራመድ ይልቅ ጦርነትን ለመቆስቆስ ብዙ ሲጥር ኖሯል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ የሐሰት ሃይማኖትን ከዓለም ነገሥታት ጋር እንደምታመነዝር አንዲት “ጋለሞታ” አድርጎ ይገልጸዋል። (ራእይ 17:1, 2) አምላክ በምድር ለታረዱት ሁሉ ደም በኃላፊነት የምትጠየቀዋ ቀንደኛ ወንጀለኛ እርሷ እንደሆነች አስታውቋል። (ራእይ 18:24) በዚህ ምክንያት ይሖዋ አምላክ ይህችን የሰላም እንቅፋት ለአንዴና ለመጨረሻ ያጠፋታል።—ራእይ 18:4, 5, 8

ሰዎችን የከፋፈሉት እንደ ፖለቲካና የሐሰት ሃይማኖት ያሉት ኃይሎች ከጠፉ በኋላም ቢሆን ታላቁ ጦርነት ቆስቋሽ ሰይጣን ዲያብሎስ ካልተወገደ በስተቀር በአስተማማኝ ሁኔታ ሰላም ሊሰፍን አይችልም። የአምላክ መንግሥት በመላዋ ምድር ፍጹም ሰላምን ለማስፈን ባላት ፕሮግራም ውስጥ የምታከናውነው የመጨረሻ ተግባር ይህ ይሆናል። የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የሆነው የራእይ መጽሐፍ ሰይጣን ‘እንደሚያዝ’፣ ‘እንደሚታሰር’ እና ‘አሕዛብን ወደፊት እንዳያስት ወደ ጥልቅ እንደሚጣል’ ይናገራል። ከዚያም በኋላ ሙሉ በሙሉ ይደመሰሳል።—ራእይ 20:2, 3, 10

ጦርነት ፈጽሞ እንደማይኖር የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ከንቱ ሕልም አይደለም። ይሖዋ አምላክ ሰላምን ለማምጣት ያለው ዝግጅት በሥራ ላይ መዋል ከጀመረ ቆይቷል። የአምላክ መንግሥት በሰማይ ተቋቁማለች፤ ዋስትና ያለው ዓለም አቀፍ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነች። እስከዚያው ድረስ ይህችን ሰማያዊት መንግሥት የሚደግፉ በሚልዮን የሚቆጠሩ የይሖዋ ምስክሮች በሰላም መኖርን ተምረዋል።

እንግዲያው ጦርነት ሊቀር እንደሚችል ለማመን የሚያስችሉን በቂ ምክንያቶች መኖራቸው ግልጽ ነው። ከዚህም የበለጠ በቅርቡ ይሖዋ የጦር መሣሪያዎችን ለዘላለም ሲያጠፋ የምናይበትን ቀን ልንጠባበቅ እንችላለን። (መዝሙር 46:9) ይሖዋ፣ በቅርቡ ጦርነት የማይኖርበት ዓለም ያመጣል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አንዳንድ ጊዜ ሃይማኖታዊ መሪዎች ራሳቸው የተዋጉበት ጊዜ አለ። በእንግሊዝ ጦርነት ጊዜ (በ1066) የካቶሊክ አቡን የነበሩት ኦዶ ከሰይፍ ይልቅ መቋሚያቸውን በመጠቀም በጦርነቱ የነበራቸውን ተሳትፎ አሳይተዋል። ደም እስካላፈሰሰ ድረስ አንድ የአምላክ ሰው ሕጋዊ ግድያ መፈጸም ይችላል ብለውም ተናግረዋል። ይህ ከሆነ ከአምስት መቶ ዘመን በኋላ ካርዲናል ኪመንስ ራሳቸው ሰሜን አፍሪካን ለመውረር የመጣውን የስፔይንን ጦር መርተዋል።

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጦርነት በማይኖርበት አዲስ ዓለም ለመኖር ትችላለህ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ