የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 3/1 ገጽ 31
  • ‘አምላክ ለሰው ፊት አያደላም’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘አምላክ ለሰው ፊት አያደላም’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንደምትወጂያቸው ንገሪያቸው
    የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን [ደስተኛ አዓት] ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 3/1 ገጽ 31

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

‘አምላክ ለሰው ፊት አያደላም’

ከአሥራ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ ተገፋፍቶ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያዳላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ” ነው በማለት ጽፏል። (ሥራ 10:34, 35) በይሖዋ ምስክሮች መካከል ከሁሉም ዘሮችና ሃይማኖቶች የመጡ ሰዎች ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች ጽድቅን ይወዳሉ አምላክንም ይፈራሉ። ይሖዋ በቻድ ለምትገኝ አንዲት ሴት እንዳደረገው ወደ አዲሱ ዓለም የሚመጡትን ሁሉ በደስታ ይቀበላል።

ይህች ሴት የነበረችበት ሃይማኖት አላረካትም ነበር። ከዓመታት በፊት ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት የተባለውን በይሖዋ ምስክሮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ወስዳ ነበር። በመጽሐፉ ውስጥ በሚገኙት ጥሩ ምክሮች ተደሰተች። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረላትና ጥናቷን ሳታቋርጥ ማጥናት ቀጠለች። ይሁን እንጂ በመንግሥት አዳራሽ በሚደረገው ስብሰባ እንድትገኝ የተሰጣትን ማበረታቻ ሁሉ አልተቀበለችም። ለምን? ባሏ ማጥናቷን ባይቃወምም በመንግሥት አዳራሽ በሚደረገው ስብሰባ እንድትገኝ አልፈቀደላትም ነበር።

ሚስቱ በክልል ስብሰባ ላይ ለመገኘት በፈለገች ጊዜ ጥናቱን የምትመራው ምስክር ለባሏ ፕሮግራሙን አሳየችውና የሚቀርቡትን ጥሩ ጥሩ ምክሮች ገለጸችለት። “ለአንዴ ብቻ” እንድትሄድ ፈቀደላት። በስብሰባው ላይ ተገኘችና ፕሮግራሙን በሙሉ በደንብ ተከታተለች። ከስብሰባው የተማረችውን በዝርዝር ካስረዳችው በኋላ በሌሎች ስብሰባዎች ላይ እንዳትገኝ መከልከሉን አቆመ። ጉባኤው ከተለያዩ ጎሳዎች በመጡና እርስ በርሳቸው በሚተሳሰቡ ሰዎች መሞላቱን ስትመለከት በጣም ተገረመች። ከዚያ በኋላ በወረዳ ስብሰባ ላይ ተገኘችና ከሌሎች አገሮች የመጡ ምስክሮች ልጆቿን ጭናቸው ላይ አስቀመጧቸው። ምስክሮቹ ከልጆቹ ጋር አብረው በመብላት እንደ ቤተሰብ ስለቆጠሯቸው በጣም ተደነቀች። ይህ ወቅት በሕይወቷ ውስጥ የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ሆነ።

ይሁን እንጂ ወዲያው ተቃውሞ ደረሰባት። በተፈጥሮዋ ፈሪ ብትሆንም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ሐሳብ በመስጠት መሳተፍ ጀመረች። እንዲሁም ከዘመዶቿና ጎረቤቶቿ ለሚሰነዘሩት አፍራሽ ሐሳቦች በድፍረት መልስ መስጠት ጀመረች። ከባሏ ጋር ብዙ ዓመታት የኖረች ብትሆንም ሕጋዊ ጋብቻ አልነበራቸውም። እንዴት አድርጋ ሕጋዊ ጋብቻ ስለመፈጸም ትነግረው ይሆን? ወደ ይሖዋ ከልብ ከጸለየች በኋላ ባሏን አነጋገረችውና በነገሩ እንደሚያስብበት ነገራት። በመጨረሻም በሐሳቡ ተስማማና ባልና ሚስቱ በሕግ ተጋቡ።

አብራቸው የምትኖር የባሏ እኅት ብዙ ችግር ትፈጥርባት ነበር። ባልየው ግን በሚስቱ ጎን ቆመ። ቀጥሎም የባሏ አባት ሊጠይቋቸው መጡ። ሃይማኖቷን ስለ ቀየረች ሚስቱን እንዲፈታ ልጃቸውን አዘዙት። አባትየው ሌላ “የተሻለች ሚስት” ቢያገባ ራሳቸው ጥሎሽ እንደሚከፍሉለት ለልጃቸው ነገሩት። ልጃቸውም “ይህን አላደርገውም። እርሷ ጥሩ ሚስት ናት። ራስዋ መሄድ ከፈለገች ያ ሌላ ነገር ነው። እኔ ግን ሂጂ አልላትም” በማለት መልስ ሰጣቸው። ሚስትየው የባሏን አባት በአክብሮት ይዛቸው ስለ ነበረ ባሳዩት ጠባይ አፍረው ተመለሱ። ይሁን እንጂ ወደ ሰፈራቸው ከተመለሱ በኋላ ለልጃቸው ከባድ ማስጠንቀቂያ ያዘለ ደብዳቤ ጻፉለት። ሚስትህን ለማባረር እምቢ ካልክ ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ልጄ አልቆጥርህም አሉት። አሁንም ልጁ ሚስቱን ደግፎ በአቋሙ ጸና። ባሏ እንደዚህ የመሰለ ቆራጥ አቋም ሲወስድ ማየቷ ሚስቲቱን ምን ያህል እንዳስደሰታት መገመት ይቻላል።

በአሁኑ ጊዜ ሁለቱ ትንንሽ ወንዶች ልጆች ከእናታቸው ጋር ወደ መንግሥት አዳራሽ መሄድ ያስደስታቸዋል። እንዲያውም ንግግር የሚያደርጉ ወንድሞች ሁሉ ከረባት ሲያደርጉ ስለሚያዩ እነሱም ከረባት እንዲገዛላቸው አባታቸውን ጠየቁት። ዛሬ ይህች ሴት የተጠመቀች እኅት ናት።

እርስዋም በእውነት ‘አምላክ ለሰው ፊት እንደማያደላ’ በመገንዘብ የይሖዋን መንግሥት ምሥራች በቻድ ውስጥ ከሚያውጁት 345 ደስተኛ ምስክሮች መካከል አንዷ ሆናለች።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ