የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 5/15 ገጽ 24-25
  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ታይላንድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ታይላንድ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስደተኞች የምሥራቹን ሰሙ
  • የቪዲዮ ፊልም የሰዎችን ፍላጎት ቀሰቀሰ
  • “የባዕድ አገር ሰዎች” ይሖዋን ‘በደስታ እንዲያገለግሉት’ መርዳት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • የስደተኞች ቀውስ—በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዩክሬንን ለቀው እየተሰደዱ ነው
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 5/15 ገጽ 24-25

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ታይላንድ

“የነፃ ሰዎች ምድር።” ይህ ታይላንድ የሚለው ስም ትርጉም ነው። ከ 57,000,000 የሚበልጡት ደርባባና ሥራ ወዳድ የሆኑት ነዋሪዎቿ የተለያዩ ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦች አሏቸው። ምንም እንኳ የቡድሂዝም እምነት ገንኖ ቢታይም በደቡብ ምሥራቅ እስያ በምትገኘው በዚህች አገር ውስጥ የሕዝበ ክርስትና የተለያዩ ሃይማኖቶችም ይገኛሉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች የመንግሥቱን ዜና መስማት ያስፈልጋቸዋል።—ማቴዎስ 24:14a

ስደተኞች የምሥራቹን ሰሙ

በማያንማር ድንበር አካባቢ ባሉት የታይላንድ ኮረብቶች ላይ በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩ ከ10,000 የሚበልጡ ስደተኞች አሉ። የካረን ሕዝቦች በመባል በሚታወቁት በእነዚህ ከማያንማር በመጡ ስደተኞች ዘንድ እውነት እየተስፋፋ ነው። በዚያ አካባቢ የሚኖር የአንድ የካረን ቤተሰብ አባላት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው። በስደተኞቹ መካከል የምሥራቹን ሲያሰራጩ ቆይተዋል። ግን ሥራቸው እንዴት ተጀመረ?

ከሦስትና ከአራት ዓመታት በፊት አንድ ወጣት ከአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረውን ግንኙነት በማቋረጥ ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ ይሆናል። ቤተሰቦቹ ግን በቄሳቸው ቀስቃሽነት ይህንን ወጣት ተቃወሙት። ይሁን እንጂ በትዕግሥት በመጽናቱ የቤተሰቡ ተቃውሞ እየረገበ መጣ። የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ቄሶች ግን ከሁለት ዓመታት በፊት ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት ፈጽመው ከቢሮአቸው እስከተባረሩበት ቀን ድረስ ይዘብቱበት ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኗ ያለ እረኛ ስለቀረች የምሥክሩ የቅርብ ቤተሰቦችና ሌሎች ዘመዶች ተደናግጠውና ባዷቸውን ቀርተው ነበር። ከእነርሱ መካከል አሥራ አንዱ ስማቸውን ከቤተ ክርስቲያናቸው መዝገብ አሰርዘው ምሥክሮቹ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስጠኗቸው ጠየቁ።

የቪዲዮ ፊልም የሰዎችን ፍላጎት ቀሰቀሰ

በስደተኞቹ መካከል ገና ብዙ የቁጥር እድገት ማድረግ የሚቻልበት አጋጣሚ አለ። በ1993 በተከበረው የመታሰቢያ በዓል ላይ 57 ሰዎች ተገኝተዋል። በዚያው ዓመት በግንቦት ወር በክልል የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት ወቅት ንግግሩን ለማዳመጥ 67 ሰዎች ተገኝተው ነበር። በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የወጣው የይሖዋ ምሥክሮች ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የሚለው የቪዲዮ ፊልም ሲታይ ደግሞ 250 ተገኝተዋል።

በዚያው በካምፑ ውስጥ የሚኖር የአንድ የባብቲስት ፓስተር ሚስት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ንግግር በምሥክሮቹ ሲሰጥ በዚያ ተገኝታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሲብራሩ አስተዋለች። ከዚያም ለባለቤቷ በእነርሱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጠው ተደጋጋሚ ስብከት እንዴት እንደሰለቻት ነገረችው። እርሷ ወደ ይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ የምትሄድ ከሆነ ሌሎች ምዕመናንም እርሷን እንደሚከተሏት በመናገር ተቃወማት። በድጋሚ ወደ ስብሰባው ስትሄድ ቢላዋ አንሥቶ አባረራትና በስብሰባው ላይ የጻፈቻቸውን ማስታወሻዎችና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቿን ሁሉ አቃጠለባት። ይህንን ሁሉ ቢያደርግባትም የሺዲዮ ፊልሙ ሲታይ እንደገና በዚያ ተገኘች። ከዚያ በኋላ ይህች ሴት ያየችውን ነገር ለባሏ ነገረችው። ከበፊቱ የተለየ አመለካከት በመያዝ ቪዲዮውን ለማየት ፍላጎት አደረበት። ማስታዎሻዎቿንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቿን ስላቃጠለባትም አዘነ።

ስለዚህ በታይላንድ የሚገኙ እነዚህ ሕዝቦች ምሥራቹን እየሰሙ ነው። አዎን፣ “በነጻ ሰዎች ምድር” ላይ መንፈሳዊ ነጻነት እያገኙ ነው።—ዮሐንስ 8:32

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የ1994ቱን የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ይመልከቱ።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የ1993 የአገልግሎት ዓመት የአገሪቱ ሪፖርት መግለጫ

የምሥክሮቹ ከፍተኛ ቁጥር፦1,434

የምስክሮቹ ቁጥር ከአገሩ ሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር፦

1 ምሥክር ለ40,299

በመታሰቢያው በዓል የተገኙ ተሰብሳቢዎች፦3,342

የአቅኚዎች ብዛት በአማካይ፦232

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ብዛት በአማካይ፦1,489

የተጠማቂዎች ብዛት፦92

የጉባኤዎች ብዛት፦39

ቅርንጫፍ ቢሮው የሚገኝበት ቦታ፦ባንኮክ

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች በቅንዓት የምሥራቹን ሲሰብኩ

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በ1947 የነበረው የመጀመሪያው ቅርንጫፍ ቢሮ

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የቤቴል ቤተሰብ የካቲት 8, 1992 ከተመረቀው በባንኮክ ከሚገኘው አዲስ የቅርንጫፍ ቢሮ ፊት ለፊት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ