አንዳንዶች ለመንግሥቱ ስብከት ሥራ እርዳታ የሚሰጡበት መንገድ
◻ ለዓለም አቀፉ ሥራ የሚደረግ መዋጮ፦ ብዙዎች “ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራ የሚደረግ መዋጮ—ማቴዎስ 24:14” ተብሎ የተለጠፈባቸው ሣጥኖች ውስጥ የሚያስገቡትን የተወሰነ የገንዘብ መጠን ይመድባሉ ወይም ወጪ ያደርጋሉ። ጉባኤዎች ይህን ገንዘብ በየወሩ በብሩክሊን ኒው ዮርክ ወዳለው ዋና መሥሪያ ቤት ወይም በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ቢሮ ይልካሉ።
◻ ስጦታዎች፦ በፈቃደኛነት የሚደረጉ የገንዘብ እርዳታዎች በቀጥታ Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania, 25 Columbia Hieghts, Brooklyn, New York 11201–2483 በሚለው አድራሻ ወይም በአቅራቢያው ወደሚገኝ የማኅበሩ ቅርንጫፍ ቢሮ ሊላክ ይችላል። ጌጣጌጦች ወይም ሌሎች ውድ ዕቃዎችም በእርዳታ ሊሰጡ ይችላሉ። የተላከው ነገር ስጦታ መሆኑን የሚገልጽ አጭር ደብዳቤም አብሮ መላክ ይኖርበታል።
◻ ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት፦ አንድ ሰው ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የሰጠውን ገንዘብ ሊጠቀምበት በሚፈልግበት ጊዜ ሊመለስለት የሚያስችል ዝግጅት በማድረግ እስኪሞት ድረስ ማኅበሩ በአደራ መልክ እንዲይዘው ሊሰጥ ይችላል።
◻ ኢንሹራንስ፦ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የአንድ የሕይወት ዋስትና ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ስም ሊዛወርለት ይችላል። እንዲህ ዓይነት ዝግጅት ሲደረግ ለማኅበሩ ማስታወቅ ይገባል።
◻ የባንክ ሒሳብ፦ የባንክ ሒሳቦች፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ወይም ተናጠል የሆኑ የጡረታ ሒሳቦች የአካባቢው ባንክ በሚፈቅደው መሠረት በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ሊሰጥ ይችላል። ማንኛውም እንዲህ ዓይነቱ ዝግጅት መደረጉን ለማኅበሩ ማስታወቅ ይገባል።
◻ አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችና ቦንዶች በይፋ ስጦታነትም ሆነ ገቢው ለሰጪው በተከታታይ እንዲመለስለት ዝግጅት ተደርጎ ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በእርዳታ ሊሰጥ ይችላል።
◻ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፦ ሊሸጡ የሚችሉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በይፋ ስጦታነት ወይም ሰጪው በሕይወት እስካለ ድረስ በንብረቱ በመተዳደር እንዲቀጥል መብቱን በማስጠበቅ ለማኅበሩ በእርዳታ ሊሰጥ ይችላል። አንድ ሰው ማንኛውንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማኅበሩ ከማስተላለፉ አስቀድሞ ከማኅበሩ ጋር መገናኘት ይኖርበታል።
◻ ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ለፔንሲልቫንያው የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተፈጻሚነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት በውርሻ ሊሰጥ ወይም ማኅበሩ በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ እንደሆነ ስም ሊተላለፍለት ይችላል። አንድ የሃይማኖት ድርጅት እንዲጠቀምበት በአደራ የተሰጠ ንብረት በቀረጥ ረገድ አንዳንድ ጥቅሞች አሉት። የኑዛዜው ወይም ንብረት በአደራ የተሰጠበት ስምምነት ቅጂ ለማኅበሩ ሊላክ ይገባል።
◻ በእቅድ የሚደረግ ስጦታ፦ ማኅበሩ “በእቅድ ስለሚደረግ ስጦታ” አንዳንድ ሐሳቦችን አጠናቅሯል። ለማኅበሩ አሁን ልዩ ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ ውርስ ለመተው እያቀዱ ያሉ ሰዎች ይህ ሐሳብ ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። በተለይም አንዳንድ የቤተሰብ ግብ ለማከናወን ወይም ውርሱ የሚያስከፍለውን ቀረጥ በሕጋዊ መንገድ ለማስቀነስ በሚፈልጉበት ጊዜ ይህ ሐሳብ ሊረዳቸው ይችላል። ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ወደ ማኅበሩ በመጻፍ ይህን መረጃ ማግኘት ይቻላል።
እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Treasurer’s Office, Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania, 25 Columbia Heights, Brooklyn, New York 11201–2483 በሚለው አድራሻ ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ የማኅበሩ ቅርንጫፍ ቢሮ መጻፍ ይቻላል።