የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 4/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ድክመትን፣ ክፋትንና ንስሐን ለይቶ ማወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • መልስ የሚያገኙት የእነማን ጸሎቶች ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የጸሎቶችህን ይዘት ይበልጥ ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 4/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተደስተሃልን? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ትችል እንደሆነ ተመልከት፦

▫ የጥንቶቹ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ልደት ያላከበሩት ለምንድን ነው?

ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ እንደሚናገረው “የጥንቶቹ ክርስቲያኖች [የኢየሱስን] ልደት አላከበሩም፤ ምክንያቱም የማንኛውንም ሰው የልደት በዓልን ማክበር አረማዊ ልማድ አድርገው ይመለከቱት ነበር።”—12/15፣ ገጽ 4

▫ ጸሎቶች ወደ ኢየሱስ መቅረብ ይኖርባቸዋል?

አይኖርባቸውም፤ ምክንያቱም ጸሎት ሁሉን ለሚችለው አምላክ ብቻ የሚቀርብ አንዱ የአምልኮ ክፍል ነው። ጸሎቶቻችንን ሁሉ ወደ ይሖዋ አምላክ በማቅረብ “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ” ብለን እንድንጸልይ ኢየሱስ የሰጠንን መመሪያ እንደምንከተል እናሳያለን። (ማቴዎስ 6:9)—12/15፣ ገጽ 25

▫ ዳዊት ለፈጸመው ከባድ ኃጢአት የተሰጠው ፍርድ ሐናንያና ሰጲራ ለፈጸሙት ኃጢአት ከተሰጠው ፍርድ የተለየ የሆነው ለምንድን ነው? (2 ሳሙኤል 11:2–24፤ 12:1–14፤ ሥራ 5:1–11)

ዳዊት ከባድ ኃጢአት ሊሠራ የቻለው በሥጋዊ ድክመት የተነሣ ነው። ኃጢአቱ ያስከተለበትን መዘዝ እየቀመሰ ለመኖር ቢገደድም እንኳ በሠራው ሥራ ሲወነጀል ንስሐ ገብቷል፤ ይሖዋም ይቅር ብሎታል። ሐናንያና ሰጲራ ኃጢአት የሠሩት የክርስቲያን ጉባኤን ለማታለል በመሞከር በግብዝነት በመዋሸት ነው። በዚህ መንገድ ‘መንፈስ ቅዱስንና አምላክን ዋሹ።’ (ሥራ 5:3, 4) ይህም ክፉ ልብ እንደነበራቸው አረጋግጧል። በመሆኑም የከፋ ፍርድ ተቀብለዋል።—1/1፣ ገጽ 27, 28

▫ ይሖዋን ከልብ በመነጨ ደስታ እንድናገለግለው ምን ሊረዳን ይችላል?

ላገኘናቸው በረከቶችና አምላክ ለሰጠን የአገልግሎት መብት ቀና የሆነ እንዲሁም አድናቆት የተሞላበት አመለካከት ማዳበር ይኖርብናል። የአምላክን ቃል በመከተል እሱን እያስደሰትነው እንዳለን በፍጹም መርሳት አይገባንም።—1/15፣ ገጽ 16, 17

▫ ውጤታማ ማበረታቻ ለመስጠት ምን ሁለት ነገሮችን በአእምሮአችን መያዝ ይገባናል?

አንደኛ ማበረታቻህ ግልጽ እንዲሆን ስለምትናገረው ነገር አስብ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ምስጋና ወይም ማበረታቻ ሊሰጠው የሚገባውን ሰው ቀርበህ ለማነጋገር የሚያስችሉህን አጋጣሚዎችን ፈልግ።—1/15፣ ገጽ 23

▫ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ‘በእጆቻቸው የዘንባባ ዝንጣፊዎችን የያዙት’ ለምንድን ነው? (ራእይ 7:9)

የዘንባባ ዝንጣፊዎቹ መውለብለብ “እጅግ ብዙ ሰዎች” በደስታ የይሖዋን መንግሥትና በእርሱ የተቀባውን ንጉሥ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን በእልልታ እንደሚቀበሉ ያመለክታል። (ዘሌዋውያን 23:39, 40ን ተመልከት።)—2/1፣ ገጽ 17

▫ በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ ምን ጠቃሚ ትምህርቶች ይገኛሉ?

የኢዮብ መጽሐፍ ችግሮችን እንዴት መቋቋም እንደምንችል ያሳያል። ችግሮች ላጋጠሙት ሰው እንዴት ምክር ሊሰጠው እንደሚገባና እንደማይገባ የሚጠቁሙ ማራኪ ምሳሌዎችን አቅፏል። ከዚህም በተጨማሪ የኢዮብ የራሱ ተሞክሮ በከባድ ችግሮች ስንገላታ ሚዛናችንን እንድንጠብቅ ሊረዳን ይችላል።—2/15፣ ገጽ 27

▫ ከኢየሱስ ተአምራት ምን ትምህርቶች እናገኛለን?

የኢየሱስ ተአምራት ክርስቲያኖች አምላክን እንዲያወድሱ ምሳሌ በመተው አምላክን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ። (ሮሜ 15:6) መልካም ማድረግን፣ ለጋስነትንና ርኅራኄ ማሳየትን አበረታተዋል።—3/1፣ ገጽ 8

▫ ሽማግሌዎች ራሳቸውን ከወሰኑ አዳዲስ ሰዎች ጋር አስቀድመው የተዘጋጁ ጥያቄዎችን የሚከልሱት ለምንድን ነው?

አስቀድሞ የተዘጋጁ ጥያቄዎችን መከለሱ እያንዳንዱ የጥምቀት ዕጩ መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ሙሉ በሙሉ እንደተረዳና የይሖዋ ምሥክር መሆን ምን ምን ነገሮችን እንደሚጠይቅ በሚገባ ያውቅ እንደሆነ ለማረጋገጥ ያስችላል።—3/1፣ ገጽ 13

▫ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩት ጸሎቶች እንዴት ሊጠቅሙን ይችላሉ?

ቅዱስ ጽሑፋዊ ጸሎቶችን በጥልቀት በመመርመር እኛ ባለንበት ተመሳሳይ ሁኔታ ሥር የቀረቡትን ጸሎቶች ለይተን ለማወቅ እንችላለን። እንዲህ ዓይነቶቹን ጸሎቶች ፈልጎ ማግኘት፣ ማንበብና በእነርሱ ላይ ማሰላሰል ከይሖዋ ጋር ያለህን የግል የሐሳብ ግንኙነት ይበልጥ ለማሻሻል ሊረዳህ ይችላል።—3/15፣ ገጽ 3, 4

▫ አምላካዊ ፍርሃት ምንድን ነው?

አምላካዊ ፍርሃት ይሖዋን ቅር እንዳናሰኝ መፍራትና የይሖዋን ግርማና ቅድስና ማድነቅ ማለት ነው። (መዝሙር 89:7)—3/15፣ ገጽ 10

▫ መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ ፊት ውድ እንደሆንን የሚያሳይባቸው ሦስት መንገዶች ምንድን ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዳችን በአምላክ ፊት ዋጋ እንዳለን ያስተምራል (ሉቃስ 12:6, 7)፤ ይሖዋ እንዴት አድርጎ እንደሚመለከተን ግልጽ ያደርግልናል (ሚልክያስ 3:16)፤ በተጨማሪም ይሖዋ ለእኛ ያለውን ፍቅር በተግባር ለማሳየት ምን እንዳደረገ ይገልጻል። (ዮሐንስ 3:16)—4/1, ገጽ 11, 12, 14

▫ በዕብራውያን 10:24, 25 ላይ የሚገኙት ቃላት ክርስቲያኖች አንድ ላይ እንዲሰበሰቡ የሚያሳስብ ትእዛዝ ከመሆንም የበለጠ ትርጉም ያላቸው ለምንድን ነው?

እነዚህ የጳውሎስ ቃላት ለሁሉም ክርስቲያናዊ ስብሰባዎችም ሆነ ክርስቲያኖች አንድ ላይ ለሚገናኙበት ማንኛውም አጋጣሚ የሚያገለግል በመንፈስ አነሳሽነት የተነገረ መሥፈርት ያስተላልፋሉ።—4/1, ገጽ 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ