የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 6/1 ገጽ 30-31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ከአምላክ ለተቀበልነው ጸጋ አመስጋኝ መሆን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • በጸጋው ነፃ ወጥታችኋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች አውጁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 6/1 ገጽ 30-31

የአንባብያን ጥያቄዎች

በዕብራውያን 4:15, 16 ላይ የተጠቀሰው የክርስቶስ ኢየሱስ የሊቀ ካህንነት አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ለ“ሌሎች በጎች” የሚጠቅመው እንዴት ነው?

ምንም እንኳን ኢየሱስ በሊቀ ካህንነቱ የሚጫወተው ሚና በአንደኛ ደረጃ የሚጠቅመው በሰማይ ከእርሱ ጋር የሚሆኑትን ቢሆንም ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች አሁንም እንኳ ከኢየሱስ የክህነት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

ከአዳም ጀምሮ የሰው ልጆች ኃጢአትን ተሸክመዋል። ልክ እንደ እስራኤላውያን እኛም በወረስነው አለፍጽምና ምክንያት እንሠቃያለን። እስራኤላውያን ለሕዝቡና ለራሳቸው መሥዋዕቶችን የሚያቀርቡ ሊቀ ካህናትና ተባባሪ ካህናትን ለረጅም ጊዜ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ “እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት” ካህን ሆኖ ተቀባ። ከሞት ከተነሳ በኋላ የፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ዋጋ በይሖዋ ፊት አቀረበ።—መዝሙር 110:1, 4

ይህ ዛሬ ለእኛ ምን ትርጉም አለው? ጳውሎስ ለዕብራውያን በጻፈው ደብዳቤ ላይ ስለ ኢየሱስ የሊቀ ካህንነት አገልግሎት ገልጾ ነበር። በዕብራውያን 5:1 ላይ “ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ስለ ሰው ይሾማል” ይላል። ከዚያም በመቀጠል ጳውሎስ በቁጥር 5, 6 ላይ ኢየሱስ ሊቀ ካህናት እንደሆነና ይህም ለእኛ ጥቅም እንደሚያመጣ ገልጿል።

ጥቅም የሚያስገኝልን እንዴት ነው? ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ምንም ልጅ ቢሆን፣ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።” (ዕብራውያን 5:8, 9) ይህ ጥቅስ በመጀመሪያ ለአምላክና ለኢየሱስ ታማኝ የሆኑ ሁሉ የኃጢአት ስርየት አግኝተው የዘላለም ሕይወት በሚያገኙበት ጊዜ በአዲሱ ዓለም ውስጥ እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደምንችል እንድናስብ ሊያደርግን ይችላል። ይህ ተስፋ ኃጢአት በሚያስተሰርየው የኢየሱስ መሥዋዕትና በሊቀ ካህንነቱ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ ተስፋ ነው።

ይሁን እንጂ፣ አሁንም እንኳ ቢሆን ሊቀ ካህናት በመሆን ከሚያከናውነው ሥራ ወይም አገልግሎት ጥቅም ልናገኝ እንችላለን። ዕብራውያን 4:15, 16ን ልብ በል፦ “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፣ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” ‘የሚያስፈልገን ጊዜ’ የተባለው መቼ ነው? ምሕረትና ጸጋ ወይም ይገባናል የማንለው ደግነት በሚያስፈልገን ጊዜ ነው። ሁላችንም ባለፍጽምናችን ምክንያት ይህ ነገር አሁን እንደሚያስፈልገን ሊሰማን ይገባል።

ዕብራውያን 4:15, 16 በአሁኑ ጊዜ ካህን ሆኖ በሰማይ የሚያገለግለው ኢየሱስ ሰው ሆኖ እንደነበረና ራሱን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ ችግራቸውንና ሁኔታቸውን ሊረዳ እንደሚችል ይገልጻል። ራሱን የሚያስቀምጠው በእነማን ቦታ ነው? በእኛ ቦታ ነው። ይህን የሚያደርግልን መቼ ነው? አሁን። ኢየሱስ ሰው በነበረበት ጊዜ የሰው ልጅ የሚያጋጥሙትን ችግሮችና ሸክሞች ቀምሷል። የተራበባቸውና የተጠማባቸው ጊዜያት ነበሩ። ፍጹም ሰው ቢሆንም ደክሞታል። ይህ ሊያጽናናን ይገባል። ለምን? ኢየሱስ የተፈጥሮ ድካምን የቀመሰ ስለሆነ ብዙ ጊዜ የሚሰማንን ስሜት ያውቃል። በተጨማሪም ኢየሱስ በሐዋርያቱ መካከል የተነሳውን የቅንዓት ፉክክር ማስታገስ አስፈልጎት ነበር። (ማርቆስ 9:33–37፤ ሉቃስ 22:24) ያልተጠበቁ የሚያበሳጩ ሁኔታዎች አጋጥመውታል። ታዲያ ይህ ያልተጠበቁ ነገሮች ሲከሰቱ ወይም ተስፋ ስንቆርጥ የተሰማንን ስሜት እንደሚረዳልን እርግጠኛ እንድንሆን ሊያደርገን አይገባምን? ይገባል።

ተስፋ ስትቆርጡ ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ? ጳውሎስ ሊቀ ካህናችሁ በአእምሮና በአካል ፍጹማን እስከሚያደርጋችሁ እስከ አዲሱ ሥርዓት ድረስ ዝም ብላችሁ መጠበቅ አለባችሁ ብሏልን? አላለም። ጳውሎስ “ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ” ብሏል። ይህ ደግሞ የአሁኑን ጊዜ ይጨምራል። ከዚህ በተጨማሪም ኢየሱስ ሰው በነበረበት ጊዜ መከራና ሥቃይ ተቀብሏል። “በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው”። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እየደረሰብን ያለውን ችግር በመገንዘብ እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው። ታዲያ ይህ ወደ እርሱ እንድትሳብ አያደርግህምን?

አሁን ቁጥር 16ን ልብ እንበል። ጳውሎስ ቅቡዓንም ሆንን ወይም የሌሎች በጎች ክፍል በነፃነት ወደ አምላክ ቀርበን ለመናገር እንደምንችል ተናገረ። (ዮሐንስ 10:16) ሐዋርያው የፈለግነውን ማንኛውንም ነገር፣ አምላካዊ አክብሮት የጎደላቸውን የቁጣ ቃላት ጭምር በጸሎት ለመናገር እንችላለን ማለቱ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ኃጢአተኞች ብንሆንም በኢየሱስ መሥዋዕትና ኢየሱስ ሊቀ ካህን ሆኖ በሚያከናውነው ሥራ ምክንያት አምላክን ለማነጋገር እንችላለን ማለቱ ነው።

አሁንም እንኳ ቢሆን ከሊቀ ካህናችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የክህነት አገልግሎት ጥቅም ልናገኝ የምንችልበት ሌላው መንገድ ደግሞ ኃጢአታችንን ወይም ስህተታችንን በሚመለከት ነው። ኢየሱስ መሥዋዕቱ የሚያስገኘውን ጥቅም በዚህ የነገሮች ሥርዓት ይፈጽመዋል ብለን በፍጹም ተስፋ አናደርግም። ጥቅም ላይ ቢያውለውም እንኳ በአሁኑ ጊዜ የዘላለም ሕይወት ማግኘት አንችልም። በሉቃስ 5:18–26 ላይ የተገለጸውንና ኢየሱስ የነበረበት ቤት ጣራ ተነድሎ ከነአልጋው እንዲወርድ የተደረገውን ሽባ ሰው ታስታውሳለህን? ኢየሱስ “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ” ብሎታል። ሰውዬው ሽባ የሆነው አንድ ዓይነት የተለየ ኃጢአት ስለሠራ ነው ማለት አይደለም። የሰውዬው ኃጢአት በጠቅላላ፣ በመጠኑም ቢሆን የበሽታው ምክንያት የሆነውን በውርሻ ያገኘውን አለፍጽምና ጭምር ማለቱ ነበር።

በስርየት ቀን ወደ በረሐ የሚለቀቀው ፍየል የእስራኤልን ኃጢአት እንደሚያስወግድ ሁሉ ኢየሱስም በሚያቀርበው መሥዋዕት የሰዎችን ኃጢአት ሊያስወግድ ይችላል። (ዘሌዋውያን 16:7–10) ሆኖም ሽባው ሰው ከተፈወሰ በኋላም ቢሆን አለፍጽምና ያለበት ሰው ነበር። እንደገና ኃጢአት ሊሠራ ይችላል፤ ኃጢአተኛ ደግሞ መሞት ስላለበት ይህ ሰው ከጊዜ በኋላ ሞቷል። (ሮሜ 5:12፤ 6:23) ኢየሱስ የተናገረው ቃል ሰውዬው ወዲያውኑ የዘላለም ሕይወት እንዳገኘ አያመለክትም። ይሁን እንጂ ሰውዬው በዚያ ጊዜ መጠነኛ የሆነ የኃጢአት ይቅርታ አግኝቷል።

አሁን የኛን ሁኔታ እንመልከት። ፍጹማን ባለ መሆናችን በየዕለቱ እንሳሳታለን። (ያዕቆብ 3:2) ታዲያ ለዚህ ምን ማድረግ እንችላለን? በሰማይ ወደ ይሖዋ ሊያቀርበን የሚችል መሐሪ ሊቀ ካህን አለን። አዎን፣ ጳውሎስ እንደጻፈው ሁላችንም “ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት” ለመቅረብ እንችላለን። ስለዚህ በዛሬው ጊዜ የሚኖሩት የሌሎች በጎች አባላት ንጹሕ ሕሊናን ጨምሮ ከክርስቶስ የክህነት አገልግሎት በጣም አስደናቂ የሆኑ ጥቅሞች በማግኘት ላይ ናቸው።

ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች በሙሉ እየቀረበ ባለው አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኙትን ታላላቅ በረከቶች በጉጉት ይጠባበቃሉ። ከዚያም ሰማያዊው ሊቀ ካህናችን የመሥዋዕቱን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ያውለዋል፤ ይህም ፍጹም የኃጢአት ይቅርታ ያስገኛል። እንዲሁም የሕዝቦቹን አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ጤንነት በመንከባከብ አስደናቂ በረከቶችን ይዘረጋል። በእስራኤል ውስጥ የካህናቱ ትልቁ ሥራ ሕዝቡን ማስተማር እንደነበረ ሁሉ ኢየሱስም በምድር ላይ ለአምላክ ሕዝቦች ትልቅ የትምህርት ዘመቻ ያስፋፋል። (ዘሌዋውያን 10:8–11፤ ዘዳግም 24:8፤ 33:8, 10) በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ከኢየሱስ የክህነት አገልግሎት ጥቅም የምናገኝ ቢሆንም ከፊታችን ደግሞ ከዚህ የላቁ በረከቶች ይጠብቁናል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ