የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 7/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በዛሬው ጊዜ የአምላክን ሕዝቦች የሚመራው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • በዛሬው ጊዜ የበላይ አካሉ ሥራውን የሚያከናውነው እንዴት ነው?
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
  • “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • “በአንድ ልብ ወሰንን”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 7/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

የመጀመሪያው የአስተዳደር አካል አባላት በሙሉ አይሁዳውያን ወንዶች ነበሩ። አምላክ ከአንድ ዘር ወይም ነገድ ብቻ በመምረጡ አዳልቷል ማለት ነውን?

ማዳላቱ አልነበረም። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ የጠራቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በሙሉ አይሁዳውያን ነበሩ። በ33 እዘአ በዋለው የጰንጠቆስጤ ቀን በመንፈስ ቅዱስ ለመቀባትና ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ለመግዛት ብቁ የሆኑት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አይሁዶችና ወደ ይሁዲነት የተለወጡ አሕዛብ ነበሩ። ሳምራውያንና ያልተገረዙ አሕዛብ የተጨመሩት በኋላ ነበር። ስለዚህ በዚያ ጊዜ የነበረው የአስተዳደር አካል ከአይሁዳውያን ማለትም ሥራ 15:2 እንደሚለው ‘በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች’ የተውጣጣ የሆነበት ምክንያት ግልጽ ነው። እነዚህ ሰዎች ሰፋ ያለ የቅዱሳን ጽሑፎች እውቀትና በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ የበርካታ ዓመታት ተሞክሮ ነበራቸው። የጎለመሱ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ለመሆን የሚያስችላቸውን እድገት ለማድረግ በቂ ጊዜ አግኝተዋል።—ሮሜ 3:1, 2

በሥራ ምዕራፍ 15 ላይ የተመዘገበው ይህ የአስተዳደር አካል ስብሰባ በተደረገበት ጊዜ ብዙ አሕዛብ ክርስቲያኖች ሆነው ነበር። ይህ ደግሞ አፍሪካውያንን፣ አውሮፓውያንንና ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰዎችንም ይጨምራል። ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን ያልሆኑ ሰዎች ወደ ክርስትና እንዲሳቡ ለማድረግ ከአሕዛብ መካከል የአስተዳደር አካሉ አባል የሆነ ሰው እንደነበረ የሚገልጽ ምንም መረጃ አናገኝም። እነዚህ ወደ ክርስትና የመጡ አሕዛብ ከአይሁዳውያን ጋር በእኩልነት የሚታዩ “የእግዚአብሔር እስራኤል” አባላት ነበሩ። ይሁን እንጂ እነዚህ አሕዛብ በዚያ ጊዜ የአስተዳደር አካል አባላት የሆኑት እንደ ሐዋርያት የመሳሰሉት አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ያገኙትን ጉልምስናና ተሞክሮ በአክብሮት መመልከታቸው አይቀርም። (ገላትያ 6:16) በሥራ 1:21, 22 ላይ እንዲህ ያለው ተሞክሮ ምን ያህል ትኩረት ይሰጠው እንደነበረ ልብ በል።—ዕብራውያን 2:3፤ 2 ጴጥሮስ 1:18፤ 1 ዮሐንስ 1:1–3

አምላክ ለብዙ መቶ ዘመናት የእስራኤልን ብሔር ልዩ በሆነ መንገድ ተንከባክቦት ነበር። ኢየሱስ ደግሞ ሐዋርያቱን የመረጠው ከዚህ ብሔር ነው። በአሁኑ ጊዜ ደቡብ አሜሪካ፣ አፍሪካ ወይም ሩቅ ምሥራቅ በመባል ከሚታወቁት የምድር ክፍሎች አንድም ሐዋርያ አለመምረጡ ስህተት ወይም የፍትህ መጓደል አልነበረም። በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ወንዶችና ሴቶች በጊዜው በምድር ላይ ሐዋርያ ከመሆን ወይም የመጀመሪያው መቶ ዘመን የአስተዳደር አካል አባል ከመሆን ወይም በዘመናችን በሚገኙት የአምላክ ሕዝቦች መካከል ማንኛውንም ዓይነት ሹመት ከማግኘት በጣም የሚበልጥ መብት ያገኛሉ።—ገላትያ 3:27–29

አንድ ሐዋርያ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደሆነ በእውነት አስተዋልኩ” ብሏል። (ሥራ 10:34, 35) አዎን፣ ከክርስቶስ ቤዛ የሚገኙት ጥቅሞች ያለምንም አድልዎ ለሁሉ ሰው ተዘርግተዋል። በሰማያዊው መንግሥትና በምድር ላይ ለዘላለም በሚኖሩት እጅግ ብዙ ሰዎች ከሁሉም ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ብሔሮች መካከል የተውጣጡ ግለሰቦች ይኖራሉ።

ብዙ ሰዎች ስለ ዘር፣ ስለ ቋንቋ ወይም ስለ ብሔር በጣም የሚሰማቸው እየሆኑ መጥተዋል። ይህ ሁኔታ በሥራ 6:1 ላይ በምናነበው በግሪክ ተናጋሪ ክርስቲያኖችና በዕብራይስጥ ተናጋሪ ክርስቲያኖች መካከል ማጉረምረም አስነስቶ በነበረው አከራካሪ ጉዳይ ላይ በሚገባ ተገልጿል። በአስተዳደጋችን ምክንያት ወይም በአካባቢያችን ያለው ሁኔታ ተጽእኖ ስላደረገብን ስለ ቋንቋ፣ ስለ ዘር፣ ስለ ብሔር ወይም ስለ ጾታ የከረረ አመለካከት ይኖረን ይሆናል። እንደዚህ ከሆነ ስሜታችንንና ዝንባሌያችንን ከአምላክ አመለካከት ጋር በሚስማማ መንገድ ማስተካከልና መቅረጽ ይኖርብናል። ውጫዊው መልካችን ምንም ዓይነት ቢሆን የሰው ልጆች ሁሉ በአምላክ ፊት እኩል ናቸው። አምላክ ሽማግሌዎችና ዲያቆናት ማሟላት ያለባቸውን ብቃት ሲያጽፍ ስለ ዘር ወይም ስለ ብሔር ምንም ነገር አልጠቀሰም። ከዚህ ይልቅ አምላክ ትኩረት ያደረገው በወቅቱ ለአገልግሎት ራሳቸውን ዝግጁ ያደረጉ ወንዶች ማሟላት በሚኖርባቸው መንፈሳዊ ብቃት ላይ ነው። በዛሬው ጊዜ የጉባኤ ሽማግሌዎች፣ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች፣ የቅርጫፍ ቢሮ ሠራተኞች የሚመረጡት በዚህ ብቃት መሠረት ነው። አምላክ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የአስተዳደር አካሉን ባቋቋመበት ጊዜም ቢሆን የተመለከተው መንፈሳዊ ብቃታቸውን ብቻ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ