የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 7/15 ገጽ 3-4
  • “እንዴት እንደሚጸለይ አስተምረን”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “እንዴት እንደሚጸለይ አስተምረን”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምስሎችና “አማላጅ ቅዱሳን”
  • በመቁጠሪያ የመጠቀም ልማድ አመጣጥ
  • ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይኖርብናል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ቅዱሳን
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ለድንግል ማርያም ጸሎት ማቅረብ ተገቢ ነው?
    ንቁ!—2005
  • ወደ “ቅዱሳን” መጸለይ ተገቢ ነው?
    ንቁ!—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 7/15 ገጽ 3-4

“እንዴት እንደሚጸለይ አስተምረን”

“ጌታ ሆይ፣ እንዴት እንደሚጸለይ አስተምረን።” ይህን ጥያቄ ያቀረበው ከኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነው። (ሉቃስ 11:1 አዓት) ይህ ስሙ ያልተጠቀሰ ደቀ መዝሙር ለጸሎት ጥልቅ አድናቆት እንደነበረው አያጠያይቅም። በዛሬው ጊዜ ያሉትም አምላክን በእውነት የሚያመልኩ ሰዎች የጸሎትን አስፈላጊነት በሚገባ ይገነዘባሉ። እንዲያውም ጸሎት በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ላለው ለመጨረሻው ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ሐሳባችንን የምንገልጽበት መንገድ ነው! እስቲ አስበው! ‘ጸሎት ሰሚው’ አምላክ ለሚያሳስቡንና ለሚያስጨንቁን ነገሮች በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ይሰጣል። (መዝሙር 65:2) ከሁሉ በላይ በጸሎት አማካኝነት ለአምላክ ምስጋና እና ውዳሴ ማቅረብ እንችላለን።—ፊልጵስዩስ 4:6

ሆኖም “እንዴት እንደሚጸለይ አስተምረን” የሚሉት ቃላት አንዳንድ አሳሳቢ ጥያቄዎች ያስነሳሉ። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ ሃይማኖቶች ወደ አምላክ ለመቅረብ የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው። ሆኖም ጸሎት የሚቀርብበት መንገድ ትክክለኛ ወይም የተሳሳተ ሊሆን ይችላልን? ለመልሱ ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው ከጸሎት ጋር የተያያዙ ሃይማኖታዊ ልማዶችን አስቀድመን እንመልከት። በላቲን አሜሪካ ልማዶች ላይ እናተኩራለን።

ምስሎችና “አማላጅ ቅዱሳን”

በጥቅሉ ሲታይ በላቲን አሜሪካ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በጣም ሃይማኖተኛ ናቸው። ለምሳሌ አንድ ሰው ሰፊ ተቀባይነት ያለውን “ለአማላጅ ቅዱሳን” የመጸለይ ልማድ በመላው ሜክሲኮ መመልከት ይችላል። እንዲያውም በሜክሲኮ ከተሞች የተወሰነ ቀን መድቦ “አማላጅ ቅዱሳንን” ማክበር የተለመደ ነው። በተጨማሪም የሜክሲኮ ካቶሊኮች ብዛት ወዳላቸው የተለያዩ ምስሎች ይጸልያሉ። ሆኖም ሃይማኖተኛው የትኛውን “ቅዱስ” መለመን እንዳለበት የሚወስነው ለመጠየቅ በፈለገው ነገር መሠረት ነው። አንድ ሰው የትዳር ጓደኛ ከፈለገ “ለቅዱስ” አንቶኒ ሻማ ማብራት ይችላል። አንድ ሰው በመኪና ሊጓዝ ሲል የተጓዦች በተለይም በመኪና የሚጓዙ ሰዎች ጠባቂ የሆነው “ቅዱስ” ክርስቶፈር ከአደጋ እንዲጠብቀው ሊለምን ይችላል።

ለመሆኑ እነዚህ ልማዶች የመጡት ከየት ነው? ስፔናውያን ሜክሲኮ ሲደርሱ አረማዊ አማልክት የሚያመልኩ ሰዎች እንዳገኙ ታሪክ ያሳያል። ቪክቶር ቮልፍጋንግ ቮን ሃገን ሎስ አስቴካስ ሆምብሬ ኢ ትሪቡ (አዝቴክስ፣ ሰውዬውና ጎሣው) በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “ሁሉም ነገር አምላክ ነበረው። እያንዳንዱ ተክል አምላክ ነበረው፣ ሁሉም ተግባር የወንድ ወይም የሴት አምላክ ነበረው። ሌላው ቀርቶ ራስን መግደል እንኳ አምላክ ነበረው። ያካቴኩትሊ የነጋዴዎች አምላክ ነበረ። ብዙ አማልክት በሚመለኩበት በዚህ ዓለም ሁሉም አማልክት የየራሳቸው ተግባር ነበራቸው።”

እነዚህ አማልክት ከካቶሊክ “ቅዱሳን” ጋር መመሳሰላቸው የስፔይን ድል አድራጊዎች የአገሩን ተወላጆች “ክርስቲያን” ለማድረግ ሲሞክሩ ሕዝቡ ለጣዖቶቻቸው ይሰጡ የነበሩትን ክብር “ለቅዱሳኑ” መስጠት እንደጀመሩ በግልጽ ያሳያል። ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ላይ የወጣ አንድ ዓምድ ሜክሲኮ ውስጥ በአንዳንድ ቦታዎች የሚፈጸሙ የካቶሊክ ልማዶች የመጡበትን አረመኔያዊ ምንጭ ገልጿል። በአንድ አካባቢ ሕዝቡ ከሚያመልካቸው 64 “ቅዱሳን” መካከል አብዛኞቹ “ከተወሰኑ የማያን አማልክት” ጋር እንደሚመሳሰሉ ገልጿል።

ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ እንዲህ በማለት የማስተባበያ ምክንያቱን ያቀርባል፦ “በአንድ ቅዱስና ወደ እርሱ በሚጸልዩት ሰዎች መካከል ጽኑ ትስስር አለ። . . . ይህ ትስስር ከክርስቶስና ከአምላክ ጋር ያለውን ዝምድና የሚገታ ሳይሆን ዝምድናውን የሚያዳብርና የሚያጠናክር ነው።” ሆኖም አንድ ሰው አረማዊ ከሆኑ አማልክት ጋር ያለው እንዲህ ያለ ትስስር ከእውነተኛው አምላክ ጋር ያለውን ዝምድና እንዴት ሊያጠነክርለት ይችላል? እንደነዚህ ላሉ “ቅዱሳን” የሚቀርቡ ጸሎቶች በእርግጥ አምላክን ያስደስቱታልን?

በመቁጠሪያ የመጠቀም ልማድ አመጣጥ

ሌላው በሰፊው የሚሠራበት ልማድ በመቁጠሪያ መጠቀም ነው። ዲክሲዮናሪዮ ኢንሲክሎፔዲኮ ሂስፓኖ-አሜሪካኖ (ሂስፓኒክ-አሜሪካን ኢንሳይክሎፔዲክ ዲክሽነሪ) መቁጠሪያን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፦ “ሃምሳ ወይም መቶ ሃምሳ ዶቃዎች ያሉበት ክር ነው፤ ዶቃዎቹ ከፍ ያለ መጠን ባላቸው በሌሎች ዶቃዎች አማካኝነት በአሥር በአሥሩ የተከፋፈሉ ሲሆን መጋጠሚያው ላይ መስቀል ይደረግበታል። በአሁኑ ጊዜ ከመስቀሉ በፊት ሦስት ዶቃዎች ማድረግ ተጀምሯል።”

አንድ የካቶሊክ ጽሑፍ ስለ መቁጠሪያ አጠቃቀም ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ቅዱስ መቁጠሪያ ከአእምሮ በላይ ስለሆነው የቤዛው ዝግጅት በድምፅና በልብ ጸሎት የሚቀርብበት አንዱ መንገድ ነው። እያንዳንዳቸው አሥር ዶቃዎች የያዙ አሥራ አምስት መደቦች አሉት። በእያንዳንዱ አሥር ዶቃዎች አንድ ጊዜ የጌታ ጸሎት፣ አሥር ጊዜ እመቤታችን ማርያም ሆይ፣ እና አንድ ጊዜ ግሎሪያ ፓትሪ የተባለው ጸሎት ይደገማል። በእያንዳንዱ አሥር ዶቃዎች ምሥጢረ ሃይማኖት ማሰላሰል ያስፈልጋል።” ምሥጢረ ሃይማኖት የሚባለው ካቶሊኮች ማወቅ ያለባቸው መሠረተ ትምህርቶች ወይም ማንኛውም ትምህርቶች ሲሆኑ እዚህ ላይ የክርስቶስ ኢየሱስን ሕይወት፣ መከራና ሞት ያመለክታል።

ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፔድያ እንዲህ ይላል፦ “ጥንታዊዎቹ በመቁጠሪያ የሚቀርቡ ጸሎቶች የጀመሩት በመካከለኛዎቹ ዘመናት ሲሆን የተስፋፉት ግን በ1400ዎቹ እና በ1500ዎቹ ዘመናት ነው።” በመቁጠሪያ የሚጠቀሙት ካቶሊኮች ብቻ ናቸውን? አይደሉም። ዲክሲዮናሪዮ ኢንሲክሎፔዲኮ ሂስፓኖ-አሜሪካኖ “በእስልምና፣ በላማይስትና በቡድሂስት አምልኮ ይህን በመሰለ ዶቃ ይጠቀማሉ” ብሏል። እንዲያውም ኢንሳይክሎፔዲያ ኦቭ ሪሊጅን ኤንድ ሪሊጅንስ “መሐመዳውያን መቁጠሪያን የወረሱት ከቡድሂስቶች እንደሆነና ክርስቲያኖች ደግሞ በመስቀል ጦርነት ወቅት ከመሐመዳውያን እንደወረሱት ይነገራል” ብሏል።

መቁጠሪያ የሚያገለግለው ብዙ ጸሎቶችን መድገም ሲያስፈልግ ለማስታወስ እንዲረዳ ብቻ ነው በማለት አንዳንዶች የተቃውሞ ሐሳብ ያቀርቡ ይሆናል። ሆኖም አምላክ በመቁጠሪያ ስንጠቀም ይደሰታልን?

ስለ እነዚህ ልማዶች ማሰብ ወይም ተገቢ ወይም ትክክል ናቸው ብለን መከራከር አያስፈልገንም። ኢየሱስ ተከታዮቹ እንዴት እንደሚጸለይ እንዲያስተምራቸው ላቀረቡለት ጥያቄ እምነት የሚጣልበት መልስ ሰጥቷቸዋል። የተናገረው ነገር አዲስ እውቀት ከመፈንጠቁም በላይ ምናልባትም አንዳንድ አንባብያንን ያስገርም ይሆናል።

[በገጽ 13 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ካቶሊኮች ብዙውን ጊዜ በመቁጠሪያ ይጠቀማሉ። መቁጠሪያ የመጣው ከየት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ