የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 5/1 ገጽ 29
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ነቅቶ መጠበቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የክርስቶስ መገኘት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 5/1 ገጽ 29

የአንባብያን ጥያቄዎች

በማቴዎስ 24:​34 ላይ ስለ ተጠቀሰው “ትውልድ” ስለ ተባለው ቃል በቅርቡ ያገኘነው ግንዛቤ የነገሮች ሥርዓት ፍጻሜ ገና ሩቅ እንደሆነ ያሳያል ለማለት ይቻላልን?

በፍጹም አይቻልም። እንዲያውም ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ ፍጻሜውን እንድንጠባበቅ ሊያደርገን ይገባል። እንዴት?

በኅዳር 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ “ይህ ትውልድ” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት በእርሱ ዘመን የነበሩትን ክፉ ሰዎች ለማመልከት ነው። (ማቴዎስ 11:​7, 16-19፤ 12:​39, 45፤ 17:​14-17፤ ሥራ 2:​5, 6, 14, 40) ይህም በተወሰነ ወቅት ላይ የሚጀምርና የተወሰነ የጊዜ ርዝመት ያለውን ዘመን ለመግለጽ የተነገረ ቃል አልነበረም።

በዚሁ መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ የወጣው “የአንባብያን ጥያቄዎች” የሚከተሉትን ሁለት ቁልፍ ነጥቦች አበክሮ ገልጾ ነበር:- “የአንድ ሕዝብ ትውልድ የተወሰነ ዓመት ርዝመት ያለው ዘመን ሆኖ ሊወሰድ አይችልም” እንዲሁም “የአንድ ሕዝብ ትውልድ የሚኖረው በአንጻራዊ ሁኔታ ለአጭር ጊዜ ነው።”

“ትውልድ” የሚለውን ቃል ብዙውን ጊዜ የምንጠቀመው በዚህ መንገድ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ‘በናፖሊዮን ትውልድ የነበሩት ወታደሮች ስለ አውሮፕላንና ስለ አቶሚክ ቦምብ የሚያውቁት ነገር አልነበረም’ እንላለን። እንዲህ ስንል ናፖሊዮን በተወለደበት ዓመት የተወለዱትን ወታደሮች ማመልከታችን ነውን? እንዲሁ እርሱ ከመሞቱ በፊት የሞቱትን ወታደሮች ማመልከታችን ነውን? በፍጹም አይደለም፤ “ትውልድ” የሚለውን ቃል በዚህ መንገድ ስንጠቀም የተወሰነ ዓመታት ርዝመት ያለውን ጊዜም ለይተን ማመልከታችን አይደለም። ይሁን እንጂ በዚህ አነጋገራችን በመቶ የሚቆጠሩ ዓመታትን ሳይሆን በአንጻራዊ ሁኔታ አጠር ያለ ጊዜ ማመልከታችን ነው።

ኢየሱስ በደብረ ዘይት የተናገረውንም ትንቢት የምንረዳው በተመሳሳይ ሁኔታ ነው። የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ ቅርብ እንደሆነ የምናምንበት በቂ ምክንያት አለን። (ማቴዎስ 24:​32, 33) ራእይ 12:​9, 10 እንደሚለው በ1914 የአምላክ መንግሥት ሲቋቋም ሰይጣን ወደ ምድር አካባቢ እንደተጣለ አስታውስ። የራእይ መጽሐፍ ሰይጣን እንደተቆጣም ጭምር ይናገራል። የተቆጣው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ‘ጥቂት ዘመን እንደቀረው ስላወቀ’ ነው።​— ራእይ 12:​12

ስለዚህ የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ “ነቅታችሁ ጠብቁ!” የሚል ንዑስ ርዕስ ማውጣቱ ተገቢ ነበር። ከዚህ ንዑስ ርዕስ ቀጥሎ ያለው አንቀጽ እንዲህ ይላል:- “ሁኔታዎቹ የሚፈጸሙበትን ትክክለኛ ጊዜ ማወቅ አያስፈልገንም። ከዚህ ይልቅ ትኩረታችን ቀንን በማስላት ላይ ሳይሆን ነቅቶ በመጠበቅ፣ ጠንካራ እምነት በመገንባትና ይሖዋን በማገልገሉ ተግባር በመጠመድ ላይ መሆን ይኖርበታል።” ከዚያም የኢየሱስን ቃል በመጥቀስ እንዲህ ብሏል:- “የተወሰነው ጊዜ መቼ እንደሆነ ስለማታውቁ አትዘናጉ፤ ነቅታችሁ ኑሩ። ለእናንተ እንደ ነገርኳችሁ ሁሉ ለሁሉም ነቅታችሁ ጠብቁ እላለሁ።”​— ማርቆስ 13:​33, 37 NW

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ