የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 9/1 ገጽ 30-31
  • ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነ አባት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነ አባት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠፍቶ የነበረው ተገኘ
  • ለእኛ የሚሆኑ ትምህርቶች
  • ጠፍቶ የነበረው ልጅ ተመለሰ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የጠፋው ልጅ ታሪክ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ለሚመለሱት የሚደረግ የሞቀ አቀባበል
    በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት
  • “ይሖዋ፣ መሐሪና ሞገስ ያለው አምላክ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 9/1 ገጽ 30-31

የይሖዋን ፈቃድ ፈጽመዋል

ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነ አባት

እስከ ዛሬ ከተጻፉት አጫጭር ታሪኮች ሁሉ የላቀ እንደሆነ ይነገርለታል፤ ደግሞም እንዲህ መባሉ ትክክል ነው። ኢየሱስ፣ አንድ አባት ለጠፋው ልጁ ስለነበረው ፍቅር የተናገረው ምሳሌ አምላክ ንስሐ ለሚገቡ ኃጢአተኞች ያለውን ርኅራኄ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስኮት ነው።

ጠፍቶ የነበረው ተገኘ

አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። ታናሹ ልጅ እንዲህ አለው:- ‘ለእኔ የሚደርሰኝን ውርስ አሁን ስጠኝ፤ አንተ እስክትሞት ድረስ አልጠብቅም።’ አባቱም በመስማማት ከሁለት ወንዶች ልጆች መካከል ታናሽ የሆነው የሚያገኘውን ሕጋዊ ድርሻ ማለትም የንብረቱን ሲሶ የሰጠው ይመስላል። (ዘዳግም 21:​17) ወጣቱ ንብረቱን ሁሉ በችኮላ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር በመሄድ ሥነ ምግባር የጎደለው ልቅ አኗኗር በመከተል ገንዘቡን ሁሉ አባከነ።​—⁠ሉቃስ 15:​11-13

ከዚያ በኋላ ጽኑ ረሃብ ተከሰተ። ወጣቱ ተስፋ በመቁረጥ የእሪያ ጠባቂ ሆነ። ይህ ደግሞ ለአንድ አይሁዳዊ የተናቀ ሥራ ነበር። (ዘሌዋውያን 11:​7, 8) ከፍተኛ የምግብ እጥረት ስለነበር እሪያዎች ከሚበሉት አሰር ለመመገብ ይመኝ ጀመር! በመጨረሻም ወጣቱ ወደ ልቡ ተመለሰ። ‘የአባቴ አገልጋዮች ከእኔ የተሻለ ይመገባሉ’ በማለት አሰበ። ‘ወደ ቤት ተመልሼ በመሄድ ኃጢአቴን በሙሉ እናዘዝና አባቴን ከሞያተኞቹ መካከል እንደ አንዱ እንዲያደርገኝ እለምነዋለሁ።’a​—⁠ሉቃስ 15:​14-19

ወጣቱ ሰው ወደ ቤቱ ማዝገም ጀመረ። ቁመናው በጣም ተለውጦ እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም። ቢሆንም አባቱ ‘ገና ሩቅ ሳለ’ ለይቶ አወቀው። በሃዘኔታ ተገፋፍቶ ወደ ልጁ በመሮጥ “አቀፈውና ሳመው።”​—⁠ሉቃስ 15:​20

ይህ ፍቅራዊ አቀባበል ወጣቱ ሸክሙን በቀላሉ እንዲያራግፍ ረድቶታል። ልጁ “አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፣ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው።” አባቱ ግን ባሪያዎቹን በመጥራት እንዲህ ሲል አዘዛቸው:- “ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፣ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤ የሰባውን ፍሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፣ እንብላም ደስም ይበለን ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።”​—⁠ሉቃስ 15:​21-24

በዘፈንና በጭፈራ የታጀበ ከፍተኛ ድግስ ተደረገ። ታላቁ ልጅ ከእርሻ ሲመለስ የዘፈኑንና የጭፈራውን ድምፅ ሰማ። ወንድሙ ተመልሶ መምጣቱንና ይህ ሁሉ ድግስ የተደረገው ለእሱ ሲባል መሆኑን ሲያውቅ ተናደደ። “ይህን ያህል ዓመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሃለሁ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጥቦት ስንኳ አልሰጠኸኝም” በማለት ለአባቱ ቅሬታውን ገለጸ። ‘ነገር ግን ሀብትህን አጥፍቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ፣ ግብዣ አዘጋጀህለት።’ አባቱ ግን በለሰለሰ አንደበት እንዲህ ሲል መለሰለት:- ‘ልጄ ሆይ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፣ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው። ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል።’​—⁠ሉቃስ 15:​25-32

ለእኛ የሚሆኑ ትምህርቶች

በኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው አባት መሐሪ የሆነውን አምላካችንን ይሖዋን ያመለክታል። አንዳንድ ሰዎች ልክ ጠፍቶ እንደነበረው ልጅ ዋስትና ያለው ሕይወት ከሚያስገኘው የአምላክ ቤት ይወጡና ከጊዜ በኋላ ግን ይመለሳሉ። ይሖዋ እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች የሚመለከታቸው እንዴት ነው? ከልብ ንስሐ ገብተው ወደ ይሖዋ የሚመለሱ ሰዎች እርሱ ‘ሁልጊዜ እንደማይቀሥፍና ለዘላለምም እንደማይቆጣ’ እርግጠኞች ሊሆኑ ይችላሉ። (መዝሙር 103:​9) በምሳሌው ላይ የተጠቀሰው አባት ልጁን ለመቀበል ሮጧል። በተመሳሳይም ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ከመሆኑም በላይ በደስታ ይቀበላቸዋል። እርሱ ‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነና ‘ይቅርታውም ብዙ’ ነው።​—⁠መዝሙር 86:​5 NW፤ ኢሳይያስ 55:​7፤ ዘካርያስ 1:​3

በኢየሱስ ምሳሌ ላይ አባትየው ያሳየው እውነተኛ ፍቅር ልጁ ለመመለስ የሚያስችለውን ድፍረት በቀላሉ እንዲያገኝ አስችሎታል። ይሁን እንጂ እስቲ አስበው:- አባትየው ከእንግዲህ ወዲህ ልጄ አይደለህም ብሎት ቢሆን ወይም በንዴት በመጮህ ሁለተኛ ተመልሶ እንዳይመጣ ነግሮት ቢሆን ኖሮ ምን ይከሰት ነበር? ይህን የመሰለው ሁኔታ ልጁን ለዘለቄታው ሊያርቀው ይችል ነበር።​—⁠ከ2 ቆሮንቶስ 2:​6, 7 ጋር አወዳድር።

በሌላ አነጋገር አባትየው ልጁ በሄደበት ጊዜ ተመልሶ እንዲመጣ የሚያስችለውን መሠረት ጥሎለት ነበር ማለት ነው። ዛሬም አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞችን ከጉባኤው ማስወገድ አለባቸው። (1 ቆሮንቶስ 5:​11, 13) ይህን ሲያደርጉ ኃጢአተኛው ወደፊት መመለስ ቢፈልግ ሊወስዳቸው የሚችሉ እርምጃዎችን ፍቅራዊ በሆነ ሁኔታ በመጠቆም ለመመለስ የሚያስችለውን መንገድ ሊያስተካክሉለት ይችላሉ። በመንፈሳዊ ጠፍተው የነበሩ ብዙ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ከልብ የመነጨ ልመና ማስታወሳቸው ንስሐ እንዲገቡና ወደ አምላክ ቤት እንዲመለሱ ገፋፍቷቸዋል።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 4:​2

በተጨማሪም አባትየው ልጁ በሚመለስበት ጊዜ ርኅራኄ አሳይቷል። ልጁ ከልብ ንስሐ መግባቱን ለማወቅ ረጅም ጊዜ አልወሰደበትም። ስለዚህ ልጁ የሠራውን እያንዳንዱን በደል ዘርዝሮ እንዲነግረው ከማድረግ ይልቅ እሱን በማስተናገዱ ላይ ከማትኮሩም በላይ ይህን በማድረጉም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል። ክርስቲያኖች ይህን ምሳሌ ሊኮርጁት ይችላሉ። ጠፍቶ የነበረ አንድ ሰው በመገኘቱ ደስ ሊላቸው ይገባል።​—⁠ሉቃስ 15:​10

የአባትየው ድርጊት አስቸጋሪ የነበረው ልጁ ተመልሶ እንደሚመጣ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በተስፋ ይጠባበቅ እንደነበረ በግልጽ ያሳያል። በእርግጥ ይህ ይሖዋ የእሱን ቤት ጥለው የሄዱ ሰዎች ሁሉ እንዲመለሱ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑን በጥቂቱ የሚያሳይ ነው። እሱ “ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ” ይፈልጋል። (2 ጴጥሮስ 3:​9፤ ጋደል አድርገን የጻፍነው እኛ ነን።) ስለዚህ ከኃጢአታቸው ንስሐ የሚገቡ ሰዎች ‘ከይሖዋ ፊት የመጽናናት ዘመን እንደሚመጣላቸው’ እርግጠኞች ሊሆኑ ይችላሉ።​—⁠ሥራ 3:​19

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ባሪያ የሆነ ሰው የቤተሰቡ አባል ተደርጎ ሲታይ ሞያተኛ ግን በማንኛውም ወቅት ሊባረር የሚችል የቀን ሠራተኛ ነበር። ወጣቱ በአባቱ ቤት ውስጥ የመጨረሻውን ዝቅተኛ ቦታ እንኳን ለመቀበል ፈቃደኛ ነበር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ