የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 3/15 ገጽ 10-11
  • የሰው ባሪያዎች ወይስ የአምላክ አገልጋዮች?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰው ባሪያዎች ወይስ የአምላክ አገልጋዮች?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዎችን መከተል የሚያስከትለው አደጋ
  • የይሖዋ ምስክሮች መናፍቃን ናቸውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የይሖዋ ምሥክሮች
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ክርስቲያኖችና ዛሬ ያለው ሰብአዊ ኅብረተሰብ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖት ከአሜሪካ የመጣ ኑፋቄ ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 3/15 ገጽ 10-11

የሰው ባሪያዎች ወይስ የአምላክ አገልጋዮች?

“የይሖዋ ምሥክሮች በአጠቃላይ ሲታዩ የሚደነቁ ናቸው።” ይህን ያሰፈረው ዛር ግሩብላር ኢንቱዚያስቲን የተባለው የጀርመን መጽሐፍ ነው። ምንም እንኳ ከይሖዋ ምሥክሮች ላይ ስህተት ለመለቃቀም ቢጥርም የሚከተለውን አምኖ ተቀብሏል:- “በአጠቃላይ ሲታዩ ያለ ነቀፋ የሚመላለሱና መካከለኛ ኑሮ ያላቸው ናቸው። ለሥራቸው ትጉና ጠንቃቃ ሲሆኑ ሰላማዊ ዜጎች እንዲሁም በታማኝነት ቀረጥ የሚከፍሉ ናቸው። ከመጠን በላይ ሀብትን ከማሳደድ ይቆጠባሉ። . . . በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ የሚያሳዩት የታረመ ጠባይ ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነው። ከሌላ ከማንኛውም ሃይማኖታዊ ቡድን እኩል የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ ቢኖራቸውም እንኳ በአገልግሎት ግን ከሁሉም ይበልጣሉ። በዘመናችን ካሉት ከሌሎች የክርስትና ሃይማኖቶችና ቡድኖች የላቀ ቦታ የሚያሰጣቸው በሕይወታቸው እንኳ ሳይቀር ቆርጠው ሃይማኖታዊ ትምህርታቸውን በማንኛውም አጋጣሚ ለማወጅ ባላቸው ፍጹም ቆራጥነት ነው።”a

ይህን የመሰሉ አዎንታዊ አስተያየቶች የተሰጡ ቢሆንም ስለ ይሖዋ ምሥክሮች የሚሰነዘሩት አንዳንድ አስተያየቶች ግን ከዚህ ጨርሶ የተለዩ ናቸው። ምሥክሮቹ ለብዙ አሥርተ ዓመታት በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ሃይማኖታዊ አገልግሎታቸውን አለአንዳች መሰናክል በይፋ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ማንነታቸውን ያውቃሉ፣ ያከብሯቸዋል እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴያቸውን የማከናወን መብት እንዳላቸው ይስማማሉ። ታዲያ የይሖዋ ምሥክሮችን ማንነት በተመለከተ ጥርጣሬዎች የሚነሱት ለምንድን ነው?

ለዚህ አንዱ ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ሕፃናትን በማስነወር፣ በቡድን ራስን በመግደልና በአሸባሪነት ስለሚካፈሉ ነው። እርግጥ እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት ሃይማኖተኛ በሆኑ ሰዎች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ቦታ በመፈጸም ላይ ነው። ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች ሃይማኖትን በተመለከተ ከፍተኛ ጥርጣሬ አልፎ ተርፎም የከረረ ጥላቻ እያደረባቸው ነው።

ሰዎችን መከተል የሚያስከትለው አደጋ

“ኑፋቄ” [ሴክት] የሚለው ቃል “የተለየ ሃይማኖታዊ ትምህርትን ወይም አንድን መሪ የሚከተል ቡድንን” ያመለክታል። በተመሳሳይም “አነስተኛ ሃይማኖታዊ ቡድን” [ከልት] የሚለው ቃል “ለአንድ ሰው፣ ለአንድ ጽንሰ ሐሳብ ወይም ለአንድ ነገር ያደሩ” ሰዎችን ያመለክታል። ሰብዓዊ መሪዎችንና ጽንሰ ሐሳባቸውን የሙጥኝ የሚሉ የየትኛውም ሃይማኖታዊ ቡድን አባላት የሰው ባሪያዎች የመሆን አደጋ ተደቅኖባቸዋል። ከልክ በላይ በሰዎች የመመራት መንፈስ በአእምሮ ላይ ጤናማ ያልሆነ ስሜት ለማሳደር እንዲሁም በመንፈሳዊ ጥገኛ ወደ መሆን ሊመራ ይችላል። አንድ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ የኑፋቄ ትምህርት እየተሰጠው ካደገ በዚህ አደጋ ውስጥ እንዲታጠር ሊያደርገው ይችላል።

ሃይማኖትን በሚመለከት እንዲህ ያለ አመለካከት ያላቸው እምነት የሚጣልበት መረጃ ማግኘት ይኖርባቸዋል። አንዳንዶች የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት ተከታዮቹን ባሪያ እንደሚያደርጋቸው፣ በእነሱ ላይ የፈላጭ ቆራጫነት መብት እንዳለው፣ ከልክ በላይ ነፃነታቸውን እንደሚነፍጋቸውና ከኅብረተሰቡ ተገልለው እንዲኖሩ እንደሚያደርጋቸው ተነግሯቸው ሊሆን ይችላል።

የይሖዋ ምሥክሮች እነዚህ አመለካከቶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውን ያውቃሉ። ስለዚህ ይህን ጉዳይ በተመለከተ አንተ ራስህ መርምረህ እውነቱ ላይ እንድትደርስ ግብዣ ያቀርቡልሃል። በጥንቃቄ ከመረመርክ በኋላ ወደ አንድ ዓይነት መደምደሚያ ልትደርስ ትችላለህ። የይሖዋ ምሥክሮች በእርግጥ እንደሚሉት የአምላክ አገልጋዮች ናቸው ወይስ የሰው ባሪያዎች? ይህን ያህል ቆራጥ የሆኑት ለምንድን ነው? የሚከተሉት ከገጽ 12-23 የሚገኙት ሁለት ርዕሰ ትምህርቶች እንዲህ ለመሳሰሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጣሉ።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በ1950 የታተመው የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጂ ከላይ ያለውን ሐሳብ አልያዘም። ይህ ሐሳብ የሚገኘው በ1982 ድጋሚ በታተመው የዚህ መጽሐፍ ቅጂ ላይ ሲሆን ስለ ይሖዋ ምሥክሮች የተሻለ ግንዛቤ ላይ መደረሱን የሚያመለክት ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ