የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w00 7/1 ገጽ 3-4
  • ውስጣዊ ሰላም ማግኘት ትችላለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውስጣዊ ሰላም ማግኘት ትችላለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ጥረዋል
  • ውስጣዊ ሰላም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በዚህ አስጨናቂ ዓለም ውስጥ ሰላም ማግኘት ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ዮሐንስ 14:27—“ሰላምን እተውላችኋለሁ”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ሰላም ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
w00 7/1 ገጽ 3-4

ውስጣዊ ሰላም ማግኘት ትችላለህን?

በ1854 አሜሪካዊው ደራሲ ሄንሪ ቶርኦ እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር:- “ብዙዎቹ ወንዶች በውስጣቸው የተስፋ መቁረጥ ስሜት አምቀው ይኖራሉ።”

ከዚህ መረዳት የሚቻለው ይህ ደራሲ በኖረበት ዘመን አብዛኞቹ ሰዎች ውስጣዊ ሰላም አልነበራቸውም። ይሁን እንጂ ይህ የሆነው ከ150 ዓመት ገደማ በፊት ነው። ዛሬስ ሁኔታው ከዚህ የተለየ ነውን? ወይስ ቶርኦ የተናገራቸው ቃላት ዛሬም ይሠራሉ? አንተስ በግልህ ምን ይሰማሃል? ሰላም አግኝተህ ረክተሃል? ወይስ በፍርሃትና ወደፊት ምን እንደሚከሰት ባለማወቅ ቶርኦ እንዳለው በውስጥህ ‘የተስፋ መቁረጥ ስሜት’ አምቀህ ይዘሃል?

የሚያሳዝነው በዚህ ዓለም ላይ የሰዎችን ውስጣዊ ሰላም የሚነሱ ብዙ ነገሮች አሉ። እስቲ ጥቂቶቹን ብቻ እንጥቀስ። በብዙ አገሮች ሥራ አጥነት እንዲሁም ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ድህነትንና ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሏል። በሌሎች አገሮች ብዙዎች ሃብትና ቁሳዊ ንብረት ለማሳደድ ሲሉ ይህ ነው የማይባል ጉልበት ያጠፋሉ። ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ በፉክክር የተሞላው አኗኗር ከጭንቀት በስተቀር ሰላም አያስገኝም። በተጨማሪም ሕመም፣ ጦርነት፣ ወንጀል፣ የፍትሕ መዛባትና ጭቆና ሰዎች ሰላም እንዲርቃቸው አድርጓል።

ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ጥረዋል

ብዙዎች በዚህ ዓለም ውስጥ የሚታዩትን ነገሮች ችለው መኖር ይቸግራቸዋል። አንቶንዮa በብራዚል ሳኦ ፖሎ በሚገኝ አንድ ትልቅ ፋብሪካ ውስጥ የሠራተኛ ማኅበር ሊቀ መንበር ነበር። የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል ለማድረግ በማሰብ በተቃውሞና በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ይካፈል ነበር፤ ሆኖም እንዲህ ማድረጉ ውስጣዊ ሰላም አላስገኘለትም።

አንዳንዶች ትዳር ሕይወታቸውን እንደሚያረጋጋላቸው ይሰማቸዋል፤ ሆኖም እንደጠበቁት ሆኖ ሳያገኙት ሲቀሩ ይበሳጫሉ። ማርኮስ የተዋጣለት ነጋዴ ነበር። በፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መካፈል ጀመረና በአንዲት የኢንዱስትሪ ከተማ ከንቲባ ሆኖ ተሾመ። ይሁን እንጂ በቤተሰብ ሕይወቱ ምንም አልተሳካለትም። ልጆቹ ጥለውት ሄዱ፤ እሱና ሚስቱም በመካከላቸው በተፈጠረው የከረረ አለመግባባት ምክንያት ተለያዩ።

በሳልቫዶር ብራዚል የጎዳና ተዳዳሪ የነበረው ጌርዞን ጀብዱ መሥራት ይወዳል። ከጭነት መኪና ሾፌሮች ጋር በመሆን ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ይዞራል። ብዙም ሳይቆይ የዕፅ ሱሰኛ ከመሆኑም በላይ ለዚህ ሱሱ ሲል ሰዎችን መዝረፍ ጀመረ። ለበርካታ ጊዜያት በፖሊስ ተይዟል። ምንም እንኳን ጌርዞን እብሪተኛና ጠበኛ ሰው ቢሆንም ውስጣዊ ሰላም እንዲኖረው ይመኝ ነበር። ውስጣዊ ሰላም ማግኘት ይችል ይሆን?

ቫኒ ገና ልጅ ሳለች እናቷ ስለሞተችባት ሕመምተኛ የሆነች ታናሽ እህቷን ማስታመምን ጨምሮ የቤቱ ኃላፊነት በእርሷ ጫንቃ ላይ ወደቀ። ቫኒ ቤተ ክርስቲያን ትሄዳለች ግን አምላክ እንደተዋት ይሰማታል። ምንም የአእምሮ ሰላም አልነበራትም።

ሌላው ደግሞ ማርሴሉ ነው። ማርሴሉ የሚፈልገው ሁሌ መደሰት ነበር። ከሌሎች ወጣቶች ጋር ተገናኝቶ መደነስ፣ መጠጣትና ዕፅ መውሰድ ያስደስተዋል። አንድ ቀን ከአንድ ልጅ ጋር ተጣልቶ ተደባደበና ልጁን ክፉኛ አቆሰለው። በኋላም ስላደረገው ነገር በጣም በመጸጸቱ አምላክ እንዲረዳው ጸለየ። እሱም ቢሆን የአእምሮ ሰላም ማግኘት ይፈልጋል።

እነዚህ ተሞክሮዎች የአእምሮ ሰላም ሊያሳጡ የሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎችን በግልጽ ያሳያሉ። ታዲያ የሠራተኛ ማኅበር ሊቀ መንበር የሆነው፣ ፖለቲከኛው፣ የጎዳና ተዳዳሪው፣ ከአቅሟ በላይ የምትሠራው ልጅ እንዲሁም ጭፈራ የሚወደው ልጅ የናፈቁትን ውስጣዊ ሰላም የሚያገኙበት መንገድ ይኖር ይሆን? በእነርሱ ላይ ከደረሰው ሁኔታ የምንማረው ነገር ይኖር ይሆን? ለእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ አዎን፣ የሚል ሲሆን ይህንንም በሚቀጥለው ርዕስ ላይ እናገኛለን።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ትናፍቃለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ