የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 9/15 ገጽ 28
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የሚቀበለው የእነማንን አምልኮ ነው?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
  • ክርስቲያኖች አምላክን በመንፈስና በእውነት ያመልካሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በአምላክ መንፈስ መመራት ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • በአምላክ መንፈስ መመራት​—በመጀመሪያው መቶ ዘመንና በዛሬው ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 9/15 ገጽ 28

የአንባብያን ጥያቄዎች

ይሖዋን “በመንፈስ” ማምለክ ማለት ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ ሲካር በተባለችው ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የያዕቆብ ጉድጓድ ውኃ ልትቀዳ ለመጣች አንዲት ሳምራዊት ሴት ሲመሰክር “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፣ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” ብሏል። (ዮሐንስ 4:​24) እውነተኛ አምልኮ “በእውነት” ማለትም ይሖዋ አምላክ ስለ ራሱና ስለ ዓላማው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከገለጸው ጋር በሚስማማ መንገድ መቅረብ ይገባዋል። በተጨማሪም አምላክን ማገልገል ያለብን በመንፈስ ይኸውም ከልብ ፈንቅሎ በሚወጣ ፍቅርና እምነት በሚመነጭ ቅንዓት መሆን ይገባዋል ማለት ነው። (ቲቶ 2:​14) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ‘አምላክን በመንፈስ ስለ ማምለክ’ የተናገረው ሐሳብ ይሖዋን ከምናገለግልበት ውስጣዊ ስሜት የበለጠ ነገር እንደሚጠይቅ በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ያሳያል።

ኢየሱስ በውኃው ጉድጓድ አጠገብ ከሴትየዋ ጋር ያደረገው ውይይት በአምልኮ ረገድ ግለት ማሳየትን ወይም ግለት ማጣትን የሚመለከት አልነበረም። የሐሰት አምልኮም እንኳ በቅንዓትና በፍቅር ሊቀርብ ይችላል። ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ፣ አምላክ ወደፊት ሰማርያ በሚገኘው ተራራ ላይ ወይም ኢየሩሳሌም ባለው ቤተ መቅደስ አማካኝነት እንደማይመለክ ከገለጸላት በኋላ አምላክ መመለክ የሚፈልግበትን አዲስ መንገድ ጠቆማት። (ዮሐንስ 4:​21) ኢየሱስ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 4:​24) እውነተኛው አምላክ ሥጋዊ አካል ስለሌለው ሊታይ ወይም ሊዳሰስ አይችልም። ለእርሱ የሚቀርበው አምልኮ በዓይን በሚታይ ቤተ መቅደስ ወይም ተራራ ላይ ተመሥርቶ መቅረብ የለበትም። ስለሆነም ኢየሱስ በዓይን በሚታዩ ነገሮች ላይ ከተመሠረተ አምልኮ አልፎ የሚሄድ የአምልኮ ገጽታ መጠቆሙ ነበር።

በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አምልኮ በእውነት ላይ ተመሥርቶ ከመቅረቡም ባሻገር በዓይን የማይታየው የአምላክ አንቀሳቃሽ ኃይል በሆነው ቅዱስ መንፈስ መመራት አለበት። ሐዋርያው ጳውሎስ “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና” ሲል ጽፏል። አክሎም “እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም” ብሏል። (1 ቆሮንቶስ 2:​8-12) አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ለማምለክ መንፈሱን ማግኘትና በእርሱ መመራት ይገባናል። ከዚህም በላይ መንፈሳችን ወይም ውስጣዊ ስሜታችን ቃሉን በማጥናትና ተግባራዊ በማድረግ ከእርሱ መንፈስ ጋር አንድ መሆን ያስፈልገዋል።

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አምላክን ‘በመንፈስና በእውነት አምልክ’

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ