የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w03 7/1 ገጽ 8
  • የላቀው የፍቅር ዓይነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የላቀው የፍቅር ዓይነት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ከሁሉ የላቀውን” የፍቅርን መንገድ ለመከተል ጥረት ታደርጋለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ፍቅር (አጋፔ ) ምን አያደርግም? ምንስ ያደርጋል?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ‘ከሁሉ በላይ ከልብ ተዋደዱ’
    ነቅተህ ጠብቅ!
  • ‘እሱ አስቀድሞ ወዶናል’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
w03 7/1 ገጽ 8

የላቀው የፍቅር ዓይነት

በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው “ፍቅር” የሚለው ቃል በአብዛኛው የተተረጎመው አጋፔ ከተባለው የግሪክ ቃል ነው።

ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል a የተባለው የማመሳከሪያ መጽሐፍ ይህን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል:- “[አጋፔ ] የተባለው የፍቅር ዓይነት ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት እርስ በርስ በመቀራረብ የሚፈጠር ስሜት አይደለም። የሞራል ግዴታ እንዳለብን ተሰምቶን ለሌሎች ጥቅም ከልብ በማሰብ የምናሳየው የፍቅር ዓይነት ነው። አጋፔ (ፍቅር) በግለሰብ መካከል በሚፈጠር ጥላቻ የማይገደብ ሲሆን አንድ ሰው በጥላቻ ተነሳስቶ ትክክለኛ መሠረታዊ መመሪያን ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ አጸፋውን እንዳይመልስ ያግደዋል።”

በተጨማሪም አጋፔ ከውስጥ ፈንቅሎ የሚወጣ ስሜት ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ‘እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ [አጋፔ]’ በማለት ማሳሰቢያ ሰጥቷል። (1 ጴጥሮስ 4:8) አጋፔ አስበን የምናደርገው ብቻ ሳይሆን ከልብም የሚመነጭ የፍቅር ዓይነት ነው። እንዲህ ያለው የላቀ የፍቅር ዓይነት ያለውን ኃይልና ስፋት ለመመልከት ጥቂት ጥቅሶችን ለምን አትመረምርም? የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን እንድታደርግ ሊረዱህ ይችላሉ:- ማቴዎስ 5:43-47፤ ዮሐንስ 15:12, 13፤ ሮሜ 13:​8-10፤ ኤፌሶን 5:2, 25, 28፤ 1 ዮሐንስ 3:15-​18፤ 4:16-21

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ