የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 9/15 ገጽ 14-15
  • ‘የዮካል’ ማኅተም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የዮካል’ ማኅተም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አያሸንፉህም”
  • ትኩረት የሚስብ አዲስ ግኝት
  • ይሖዋ ኤርምያስን እንዲሰብክ ላከው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የኤርምያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • እንደ ኤርምያስ ደፋር ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 9/15 ገጽ 14-15

‘የዮካል’ ማኅተም

በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የከለዳውያን ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን በመውረር ከተማዋን በእሳት አቃጠላት፤ ቅጥሯንም አፈራረሰ። የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከማረከ በኋላ ዓይኖቹን በማውጣት አሳወረው። ከዚህም በላይ “የባቢሎንም ንጉሥ . . . የይሁዳን መሳፍንት ሁሉ ገደላቸው።”—ኤርምያስ 39:1-8

በባቢሎናውያን ከተገደሉት ከእነዚህ መኳንንት ወይም መሳፍንት መካከል የሰሌምያ ልጅ ዮካል አንዱ ሳይሆን አይቀርም። በአሁኑ ወቅት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን ይህን ሰው በተመለከተ አዲስ መረጃ ተገኝቷል። ይህን መረጃ ከመመልከታችን በፊት ቅዱስ ጽሑፉ ስለ ዮካልና በጊዜው ስለነበሩት ሁኔታዎች ምን እንደሚል እስቲ እንመልከት።

“አያሸንፉህም”

ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የፍርድ መልእክት የማወጅ ተልእኮ ሰጥቶት ነበር። አምላክ ኤርምያስን የይሁዳ ነገሥታት፣ መሳፍንት፣ ካህናትና ሕዝብ “ይዋጉሃል” ብሎት ነበር። ቀጠል አድርጎም “ዳሩ ግን . . . እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም” አለው።—ኤርምያስ 1:17-19

ባቢሎናውያን የይሁዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን በከበቡ ጊዜ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ናቡከደነፆር ወደመጣበት ይመለስ እንደሆነ ለማወቅ እንዲሁም ከከተማው እንዲያርቅለት ወደ አምላክ እንዲጸልይለት ለመጠየቅ ሁለት ጊዜ መልእክተኞችን ወደ ኤርምያስ ልኮ ነበር። ከንጉሡ መልእክተኞች አንዱ ዮካል ወይም ሁካል ነበር። አምላክ፣ ኤርምያስ ለንጉሡ እንዲናገር ያዘዘው መልእክት ባቢሎናውያን ወይም ከለዳውያን ከተማዋን እንደሚያጠፏት የሚገልጽ ነበር። ይህ መልእክት በከተማዋ ውስጥ ለመቆየት የመረጠ ማንኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት እንደሚሞት ይናገራል። በሌላ በኩል ግን ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ በሕይወት ይተርፋል። ኤርምያስ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት የይሁዳን መሳፍንት ምን ያህል አስቆጥተዋቸው ይሆን!—ኤርምያስ 21:1-10፤ 37:3-10፤ 38:1-3

“ይህ ሰው [ኤርምያስ] በሚናገረው ነገር በዚህች ከተማ የቀሩትን ወታደሮችና ሕዝቡንም ሁሉ ተስፋ የሚያስቈርጥ ስለ ሆነ መሞት አለበት” በማለት ኤርምያስ እንዲገደል ለሴዴቅያስ ጥያቄ ካቀረቡት መሳፍንት መካከል አንዱ ዮካል ነበር። ክፉው ዮካል፣ ኤርምያስ በጭቃ በተሞላ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣል ካደረጉት ሰዎች መካከልም ይገኝበታል፤ በኋላ ግን ነቢዩ ኤርምያስ ከጉድጓዱ መውጣት ችሏል። (ኤርምያስ 37:15፤ 38:4-6) ኤርምያስ አምላክን በመታዘዙ ከኢየሩሳሌም ጥፋት የዳነ ሲሆን ዮካል ግን ሲመካበት ከነበረው የአይሁድ ሥርዓት ጋር አብሮ ጠፍቷል።

ትኩረት የሚስብ አዲስ ግኝት

ዮካልን በተመለከተ በ2005 ኢየሩሳሌም ውስጥ አዲስ መረጃ ተገኝቷል። አርኪኦሎጂስቶች የንጉሥ ዳዊትን ቤተ መንግሥት ለማግኘት ቁፋሮ በሚያደርጉበት ወቅት በኤርምያስ ዘመን ኢየሩሳሌም ስትጠፋ ባቢሎናውያን እንዳፈራረሱት የሚገምቱትን ግዙፍ የድንጋይ ሕንፃ ፍርስራሾች አገኙ።

ይህ ፍርስራሽ የዳዊት ቤተ መንግሥት ይሁን አይሁን በውል አልታወቀም። ያም ሆኖ አርኪኦሎጂስቶቹ ከተገኙት ፍርስራሾች መካከል፣ በገጽ 14 ላይ የሚታየውን 1 ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው የሸክላ ማኅተም ለመለየት ችለዋል። ማኅተሙ በጊዜ ብዛት የተበላሸን አንድ ሰነድ ለማሸግ አገልግሏል። በማኅተሙ ላይ “የሾቪ ልጅ፣ የሸሌምያሁ ልጅ፣ የየሁካል” የሚል ጽሑፍ ተቀርጿል። ይህን ማኅተም የቀረጸው የኤርምያስ ባላጋራ የነበረው የሰሌምያ ልጅ የሁካል ወይም ዮካል መሆኑ ግልጽ ነው።

ማኅተሙን የመረመሩት አርኪኦሎጂስቷ አላት ማሳር፣ ዮካል ከሳፋን ልጅ ከገማርያ ቀጥሎ “በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣን” መሆኑን ገልጸዋል። የሳፋን ስም በዳዊት ከተማ ውስጥ በተገኘ የሸክላ ማኅተም ላይ ተቀርጿል።a

እርግጥ ነው፣ በአምላክ ላይ ያለን እምነት አንዳንድ የጥንት ቅርሶች በመገኘታቸው ላይ የተመካ አይደለም፤ ይሁንና በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት ትንቢቶች መፈጸማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ለማመን የሚያስችል አሳማኝ ምክንያት ነው። የታሪክ ማስረጃዎች ኤርምያስ የኢየሩሳሌምን ጥፋት በትክክል አስቀድሞ ተናግሮ እንደነበር ያረጋግጣሉ። የኤርምያስ ባላጋራዎች የቀመሱት አሳፋሪ ሽንፈት እንደ እርሱ ታማኞች ከሆንን ‘ይሖዋ ከእኛ ጋር ስለሚሆን’ ጠላቶቻችን ‘እንደማያሸንፉን’ ያለንን ጽኑ እምነት ይበልጥ ያጠናክርልናል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስለ ገማርያና ስለ ሳፋን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በታኅሣሥ 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 19-22 ላይ የወጣውን “ሳፋንን እና ቤተሰቡን ታውቃቸዋለህ?” የሚል ርዕስ ተመልከት።

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኤርምያስ ለደረሰበት ተጽዕኖ በመንበርከክ የአምላክን ቃል አለዝቦ አልተናገረም

[ምንጭ]

Gabi Laron/Institute of Archaeology/ Hebrew University ©Eilat Mazar

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ