የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 12/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን ነው?
    ንቁ!—2001
  • ፀረ ክርስቶስ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ፀረ ክርስቶስ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ፀረ ክርስቶስ ማን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 12/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

• የምትወዱት ሰው ይሖዋን ማምለኩን ሲያቆም ሁኔታውን ለመቋቋም ምን ሊረዳችሁ ይችላል?

ራሳችሁንም ሆነ በታማኝነት ይሖዋን እያገለገሉ ያሉትን የቤተሰባችሁን አባላት በመንፈሳዊ ለማነጽ ጥረት አድርጉ። በሁሉም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ተካፈሉ። ሌሎችን ለመርዳት ራሳችሁን አቅርቡ። የምትወዱት ሰው አይመለስም ብላችሁ ተስፋ አትቁረጡ። ራሳችሁን አትኮንኑ። ለአምላክ የተግሣጽ ዝግጅት አድናቆት ይኑራችሁ፤ እንዲሁም ስሜታችሁን አውጥታችሁ ለወዳጆቻችሁ ተናገሩ።—9/1 ገጽ 18-21

• በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ‘የመጨረሻውን ዘመን’ ለመለየት የሚያስችሉን ሁለት መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ‘በዓለም መጨረሻ’ ማለትም በዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ላይ የሚኖሩ ክስተቶችን ተንብዮአል። (ማቴዎስ 24:3, 7, 8፤ ሉቃስ 21:11) ከዚህም በላይ “በመጨረሻው ዘመን” በሚኖሩ ሰዎች ባሕርይም ሆነ ድርጊት ላይ ለውጥ እንደሚኖር ይናገራል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) በዚህ ጊዜ የመንግሥቱ ምሥራችም መሰበክ አለበት።—9/15 ገጽ 4-6

• አንድ ክርስቲያን መኪና በሚያሽከረክርበት ጊዜ አደጋ አድርሶ የሰው ሕይወት ቢጠፋ ጉባኤው ምን የማድረግ ኃላፊነት አለበት?

ሽማግሌዎች ጉዳዩን ከተመለከቱ በኋላ አደጋው የተከሰተው ከአሽከርካሪው አቅም በላይ በሆነ ምክንያት እንደሆነ ካመኑ ይህ ሰው ከደም ዕዳ ነጻ እንደሆነ ሊወስኑ ይችላሉ። ሆኖም ግለሰቡ በደም ዕዳ ተጠያቂ መሆኑ ከተረጋገጠና ንስሐ ከገባ ቅዱስ ጽሑፋዊ ተግሣጽ የሚሰጠው ሲሆን ግለሰቡ በጉባኤ ውስጥ ያሉትን ኃላፊነቶች ለመሸከምም ብቁ አይሆንም።—9/15 ገጽ 30

• በሳይንሱ መስክ የሚደረጉ እድገቶች የዘላለም ሕይወት ሊያስገኙ የማይችሉት ለምንድን ነው?

ሳይንቲስቶች የሰውን ሕይወት ማርዘም የሚቻልበትን መንገድ ለማግኘት ሲሉ ሴሎች ራሳቸውን የሚያድሱበት ሂደት እንዳይቆም ለማድረግ ወይም ቴራፒዮቲክ ክሎኒንግ በሚባለው የምርምር መስክ ለሕመምተኛው አዲስና ፍጹም ተስማሚ የሰውነት ክፍሎችን ለመተካት ጥረት እያደረጉ ነው። ሆኖም ሰዎች የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችሉት በኢየሱስ ቤዛ አማካኝነት ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—10/1 ገጽ 3-5

• የክርስቲያኖች ጥምቀት የመጣው ከአይሁዳውያን የመንጻት ሥርዓት ነው?

አይደለም። እያንዳንዱ አይሁዳዊ፣ ሃይማኖታዊ የመንጻት ሥርዓቱን የሚያካሂደው ራሱ ስለነበር ዮሐንስ ሲያከናውነው የነበረው ጥምቀት የተለየ ነው። የሙሴ ሕግ አንድ አምላኪ የሚያረክስ ድርጊት በፈጸመ ቁጥር የመንጻት ሥርዓቱን መፈጸም እንዳለበት ሲደነግግ ክርስቲያናዊ ጥምቀት ግን የሚከናወነው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።—10/15 ገጽ 12-13

• የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ምንድን ነው?

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ ማገልገል ለሚችሉ ያላገቡ ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች የሚሰጥ የስምንት ሳምንት ሥልጠና ነው። ሥልጠናውን ከጨረሱ በኋላ ቀደም ሲል በነበሩበት ጉባኤ፣ በአገራቸው በሚገኝ ሌላ አካባቢ ወይም በሌላ አገር እንዲያገለግሉ ይመደባሉ።—11/15 ገጽ 10-11

• በ1 ዮሐንስ 2:18፤ 4:3 ላይ የተገለጸው የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን ወይም ምንድን ነው?

የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚለው አገላለጽ፣ ክርስቶስን የሚቃወሙ ወይም ክርስቶስ እንደሆኑ የሚናገሩ አሊያም በሐሰት የእርሱ ወኪሎች ነን የሚሉትን ሁሉ ያጠቃልላል። ኢየሱስም ሆነ ዮሐንስ የተናገሯቸው ቃላት፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚባሉት ሃይማኖታዊ ማታለያዎችን የሚያስፋፉና የአምላክን መንግሥት የሚቃወሙ ብዙ ሰዎች እንደሆኑ በግልጽ ያሳያሉ።—12/1 ገጽ 4-6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ