የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w07 2/1 ገጽ 31
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የሰላሙን መስፍን” አርማጌዶን ከፊቱ ይጠብቀዋል
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
  • አርማጌዶን
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • አርማጌዶን—አስደሳች ጅማሬ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • አርማጌዶን—ጦርነቶችን ሁሉ የሚያስቀረው የአምላክ ጦርነት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
w07 2/1 ገጽ 31

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በአርማጌዶን የሚከናወነው ‘ሁሉን የሚችል አምላክ ጦርነት’ ምንድን ነው? ውጤቱስ ምን ይሆናል?—ራእይ 16:14, 16

በአጭር አገላለጽ አርማጌዶን፣ ይሖዋ ንጉሥ አድርጎ የሾመው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደፊት የአምላክን ጠላቶች የሚያጠፋበት ዓለም አቀፍ ጦርነት ነው። እነዚህ ጠላቶች ማለትም ‘የዓለም ሁሉ ነገሥታት በአጋንንት መናፍስት’ እየተነዱ “ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት . . . በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ” እንደሚሰበሰቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።—ራእይ 16:14, 16

እነዚህ ነገሥታት ከአምላክ ጋር ለመዋጋት የሚሰበሰቡበት ቦታ ቃል በቃል አንድን ስፍራ አያመለክትም። አርማጌዶን የሚለው ቃል “የመጊዶ ተራራ” የሚል ትርጉም አለው። (ራእይ 16:16፤ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር የግርጌ ማስታወሻ) ይሁን እንጂ በዚህ ስም የሚጠራ ተራራ ኖሮ አያውቅም። ከዚህም በተጨማሪ “የምድር ነገሥታትና ሰራዊታቸው” ቃል በቃል በአንድ ስፍራ ሊሰበሰቡ አይችሉም። (ራእይ 19:19) ከዚህ ይልቅ “ስፍራ” የሚለው ቃል የምድር ፖለቲካዊ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው ይሖዋን እንዲሁም “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ወታደራዊ አመራር ሥር ያለውን ‘የሰማይ ሰራዊት’ በመቃወም የሚሰባሰቡበትን ሁኔታ ያመለክታል።—ራእይ 19:14, 16

አርማጌዶን የሚለው ቃል ከጥንቷ የእስራኤል ከተማ ከመጊዶ ጋር የተዛመደ መሆኑ ትልቅ ትርጉም አለው። መጊዶ፣ በዚያን ጊዜ ታላላቅ የንግድ መሥመሮችንና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የምትመች ከቀርሜሎስ ተራራ በስተ ምሥራቅ ባለው ቁልፍ ቦታ ላይ የምትገኝ ከተማ ነበረች። እንዲሁም በስፍራው የማያዳግሙ ጦርነቶች ይካሄዱ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ የእስራኤል መስፍን የነበረው ባራቅ በጄኔራል ሲሣራ የሚመራውን ኃያል የከነዓናውያን ሠራዊት ድል ያደረገው “በመጊዶ ውሆች አጠገብ” ነበር። (መሳፍንት 4:12-24፤ 5:19, 20) መስፍኑ ጌዴዎንም ምድያማውያንን በዚሁ አካባቢ አሸንፏቸዋል። (መሳፍንት 7:1-22) መጽሐፍ ቅዱስ መጪውን ጦርነት ከመጊዶ ጋር አያይዞ መግለጹ፣ አምላክ በልጁ በኩል ጠላቶቹን ሙሉ በሙሉ እንደሚደመስሳቸው ያረጋግጥልናል።

ታዲያ ውጤቱ ምን ይሆናል? የአርማጌዶን ጦርነት ማንኛውንም ዓይነት የሥነ ምግባር ውድቀትና ክፋት ከምድር ገጽ ያስወግዳል። በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ልዩ የሆነ አዲስ ምዕራፍ እንዲከፈት መንገድ ይጠርጋል። (ራእይ 21:1-4) በአምላክ መንግሥት ፍቅራዊ አመራር ሥር ምድር ወደ ገነትነት የምትለወጥ ሲሆን በዚያም ጻድቃን ለዘላለም ይኖራሉ።—መዝሙር 37:29

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ