የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 6/15 ገጽ 28
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ እስራኤሎችን ማተም
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
  • ሰማያዊ ዜግነት ያላቸው ክርስቲያን ምሥክሮች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • አይሁዳውያን
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • “የአምላክ እስራኤል” እና “እጅግ ብዙ ሰዎች”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 6/15 ገጽ 28

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሐዋርያው ጳውሎስ “እስራኤል ሁሉ ይድናሉ” በማለት ተናግሯል። (ሮሜ 11:26) ጳውሎስ ይህን ሲል አይሁዳውያን በሙሉ በሆነ ወቅት ላይ ወደ ክርስትና እንደሚለወጡ መናገሩ ነበር?

ጳውሎስ እንደዚያ ማለቱ አልነበረም። በብሔር ደረጃ ሲታይ የአብርሃም ዘሮች፣ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን አልተቀበሉም። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በነበሩት ዓመታትም ቢሆን አይሁዳውያን በብሔር ደረጃ ወደ ክርስትና እንዳልተለወጡ በግልጽ ታይቷል። ያም ሆኖ ጳውሎስ “እስራኤል ሁሉ ይድናሉ” በማለት መናገሩ እውነት ነበር። እንዴት?

ኢየሱስ፣ በዘመኑ ለነበሩት የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች “የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች” ብሏቸው ነበር። (ማቴ. 21:43) በቡድን ደረጃ የእስራኤል ብሔር ኢየሱስን ስላልተቀበለው ይሖዋ በመንፈሱ የተቀቡ ግለሰቦችን ያቀፈ አዲስ ብሔር አቋቋመ። ጳውሎስ ይህን ብሔር ‘የአምላክ የሆነው እስራኤል’ በማለት ጠርቶታል።—ገላ. 6:16

በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ጥቅሶች ‘የአምላክ የሆነው እስራኤል’ በመንፈስ የተቀቡ 144,000 ክርስቲያኖችን ያቀፈ እንደሆነ ያረጋግጣሉ። (ሮሜ 8:15-17፤ ራእይ 7:4) ይህ ቡድን አይሁዳውያን ያልሆኑ ሰዎችንም እንደሚጨምር ራእይ 5:9, 10 ያረጋግጣል፤ ምክንያቱም ጥቅሱ ቅቡዓን ክርስቲያኖች “ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ” የተውጣጡ እንደሆኑ ይገልጻል። የመንፈሳዊ እስራኤል አባላት “መንግሥትና ካህናት” እንዲሆኑ እንዲሁም ‘በምድር ላይ እንዲነግሡ’ ተለይተው ተመርጠዋል። ምንም እንኳ ይሖዋ እስራኤልን እንደተመረጠ ብሔር አድርጎ መመልከቱን ያቆመ ቢሆንም እስራኤላዊ የሆኑ ግለሰቦች በእሱ ፊት ጥሩ አቋም ሊኖራቸው ይችላል። ሐዋርያትም ሆኑ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በይሖዋ ፊት ተቀባይነት ማግኘታቸው ይህንን ያረጋግጣል። እርግጥ ነው፤ እንደ ሌላው የሰው ዘር ሁሉ እነዚህ አይሁዳውያንም በኢየሱስ ክርስቶስ ደም መዋጀት ነበረባቸው።—1 ጢሞ. 2:5, 6፤ ዕብ. 2:9፤ 1 ጴጥ. 1:17-19

በትውልድ አይሁዳዊ የሆኑ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አብዛኞቹ ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ተባባሪ ገዢ ለመሆን የነበራቸውን አጋጣሚ ማጣታቸው የአምላክ ዓላማ እንዲደናቀፍ አላደረገም። የአምላክ ዓላማ በምንም ዓይነት ሊጨናገፍ አይችልም፤ ይሖዋ “ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል” በማለት በነቢዩ አማካኝነት ተናግሯል።—ኢሳ. 55:11

ይህ ጥቅስ፣ አምላክ 144,000 ተባባሪ ገዢዎች ከልጁ ጋር በሰማይ እንዲገዙ ያወጣውን ዓላማ በሚመለከትም ይሠራል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ 144,000 ሰዎችን እንደሚቀባ በግልጽ ይናገራል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ አንድም ሰው አይጎድልም!—ራእይ 14:1-5

በመሆኑም ጳውሎስ “እስራኤል ሁሉ ይድናሉ” በማለት ሲጽፍ አይሁዳውያን በሙሉ ወደ ክርስትና እንደሚለወጡ ትንቢት መናገሩ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ አምላክ፣ መንፈሳዊ እስራኤላውያን የሆኑ 144,000 ሰዎች ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰማይ እንዲገዙ ያወጣው ዓላማ ፍጻሜውን እንደሚያገኝ መግለጹ ነበር። አምላክ በወሰነው ጊዜ 144,000ዎቹ በሙሉ ይኸውም “እስራኤል ሁሉ” ይድናሉ፤ ከጊዜ በኋላ በመሲሐዊው መንግሥት ውስጥ ነገሥታትና ካህናት በመሆን ይገዛሉ።—ኤፌ. 2:8

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ቅቡዓን “ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ” የተውጣጡ ናቸው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ