የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 12/1 ገጽ 8
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አናጺው”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ሥራ መሥራት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • “የክርስቶስን አስተሳሰብ” ማወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 12/1 ገጽ 8

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሱስ—አናጢ በነበረበት ወቅት ምን ነገሮችን ይሠራ ነበር?

የኢየሱስ አሳዳጊ አባት በአናጢነት ሙያ የሚተዳደር ሰው ነበር። ኢየሱስም ይህንን ሙያ ተምሯል። አገልግሎቱን ‘በሠላሳ ዓመቱ’ ገደማ ሲጀምር ሰዎች የሚያውቁት “የአናጢው ልጅ” በመሆኑ ብቻ ሳይሆን እሱ ራሱ አናጢ እንደነበር ነው።—ሉቃስ 3:23፤ ማቴዎስ 13:55፤ ማርቆስ 6:3

ኢየሱስ ባደገበት ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እንደ ሞፈርና ቀንበር ያሉ የእርሻ መሣሪያዎችን የሚሠሩላቸው አናጢዎች ነበሩ፤ እነዚህ መሣሪያዎች ደግሞ በዋነኝነት የሚሠሩት ከእንጨት ነው። አናጢዎች ብዙውን ጊዜ ከሚሠሯቸው ሌሎች ነገሮች መካከል እንደ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ በርጩማ እና ዕቃ መደርደሪያ ያሉ የቤት ቁሳቁሶች ይገኙበታል። ከዚህም በተጨማሪ በር፣ መስኮት፣ መቀርቀሪያና ወራጅ እንጨት ይሠሩ ነበር። እንዲያውም የአናጢነት ሙያ በግንባታ ሥራዎች ላይ መካፈልን ይጨምራል።

መጥምቁ ዮሐንስ በተናገረው አንድ ምሳሌ ላይ ስለ ምሣር ወይም መጥረቢያ ጠቅሶ ነበር፤ ኢየሱስም ሆነ ሌሎች አናጢዎች ዛፍ ለመቁረጥ በዚህ መሣሪያ ሳይጠቀሙ አልቀሩም። ከዚያም የቆረጡትን ግንድ እዚያው እንዳለ ለቤት ወራጅ ተስማሚ እንዲሆን አድርገው ያስተካክሉታል ወይም ደግሞ ወደ ሥራ ቦታቸው ይወስዱታል። እንዲህ ያለው ሥራ ከፍተኛ አካላዊ ጥንካሬ እንደሚጠይቅ ምንም ጥርጥር የለውም። (ማቴዎስ 3:10) ኢሳይያስ በዘመኑ የነበሩ አናጢዎች ይጠቀሙባቸው ስለነበሩ ሌሎች መሣሪያዎች ሲዘረዝር እንዲህ ብሏል፦ “ጠራቢ በገመድ ይለካል፤ በጠመኔ ንድፍ ያወጣል፤ በመሮ ይቀርጸዋል፤ በጸርከል ምልክት ያደርግበታል።” (ኢሳይያስ 44:13) በጥንት ዘመን የነበሩ ሰዎች ከብረት የተሠሩ መጋዞችን፣ ከድንጋይ የተሠሩ መዶሻዎችንና የነሐስ ምስማሮችን ይጠቀሙ እንደነበር የአርኪኦሎጂ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። (ዘፀአት 21:6፤ ኢሳይያስ 10:15፤ ኤርምያስ 10:4) ኢየሱስ በእነዚህ መሣሪያዎች ተጠቅሞ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ምክንያታዊ ነው።

ኢየሱስ በተናገረው አንድ ምሳሌ ላይ የጠቀሳቸው ገንዘብ “ለዋጮች” እነማን ናቸው? ሥራቸውን የሚያከናውኑትስ እንዴት ነበር?

ኢየሱስ፣ አንድ ጌታ ሰነፍ የሆነ ባሪያውን “በምመለስበት ጊዜ ገንዘቤን ከነወለዱ እንዳገኘው ለለዋጮች መስጠት ይገባህ ነበር” በማለት እንደገሠጸው ተናግሯል።—ማቴዎስ 25:27

በኢየሱስ ዘመን፣ በዛሬው ጊዜ እንዳሉት ዓይነት ትላልቅ ባንኮች አልነበሩም። ይሁንና ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ ገንዘብ አበዳሪዎች፣ ለተወሰነ ጊዜ እነሱ ጋር እንዲቆይ ለወሰዱት ገንዘብ ወለድ መክፈላቸው እንዲሁም ለሌሎች በከፍተኛ ወለድ ገንዘብ ማበደራቸው የተለመደ ነበር። ዚ አንከር ባይብል ዲክሽነሪ እንደገለጸው በአራተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ግሪክ ውስጥ በወለድ ማበደር የተለመደ ነበር። ሮማውያን በግዛቶቻቸው ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርገው በነበረበት ወቅት በመላው የሮም ግዛት ለብድር የሚከፈለው ዓመታዊ የወለድ መጠን ከ4 እስከ 6 በመቶ ነበር።

የሙሴ ሕግ ችግረኛ ለሆኑ እስራኤላውያን በአራጣ ማበደርን ይከለክል ነበር። (ዘፀአት 22:25) ይህ ሕግ በዋነኝነት የሚናገረው ለድሆች ስለማበደር ሳይሆን አይቀርም። ይሁን እንጂ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሰዎች ገንዘብ አበዳሪዎች ወይም “ለዋጮች” ጋር ላስቀመጡት ገንዘብ ወለድ መጠየቃቸው የተለመደ ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ ሌላ ጊዜ እንደሚያደርገው ሁሉ በዚህም ወቅት አድማጮቹ በሚገባ የሚያውቁትን ነገር በምሳሌው ላይ ተጠቅሟል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ