የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 2/1 ገጽ 7
  • ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምንጊዜም ቢሆን እግዚአብሔር የኢየሱስ የበላይ ነበርን?
    በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ‘ወልድ አብን ለመግለጥ ፈቃደኛ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • “መንገድ፣ እውነትና ሕይወት”
    “ተከታዬ ሁን”
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 2/1 ገጽ 7

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?

የተለመዱት መልሶች፦

▪ “አዎ፣ ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው።”

▪ “አምላክ በሥጋ የተገለጠው ኢየሱስን ሆኖ ነው።”

ኢየሱስ ምን ብሏል?

▪ “የምትወዱኝ ቢሆን ኖሮ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል።” (ዮሐንስ 14:28) ኢየሱስ፣ እሱና አባቱ እኩል እንዳልሆኑ ተናግሯል።

▪ “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው።” (ዮሐንስ 20:17) ኢየሱስ እሱ ራሱ አምላክ እንደሆነ አልተናገረም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ራሱን የቻለ አካል እንደሆነ ገልጿል።

▪ “እኔ የተናገርኩት በራሴ ተነሳስቼ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ምን እንደምልና ምን እንደምናገር ያዘዘኝ የላከኝ አብ ራሱ ነው።” (ዮሐንስ 12:49) ኢየሱስ ያስተማረው ትምህርት ከራሱ ሳይሆን ከአባቱ የመነጨ ነበር።

ኢየሱስ የአምላክ ልጅ እንደሆነ ተናገረ እንጂ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም። ኢየሱስ ራሱ አምላክ ከሆነ እዚህ ምድር ሳለ ይጸልይ የነበረው ወደ ማን ነው? (ማቴዎስ 14:23፤ 26:26-29) ኢየሱስ ከሌላ አካል ጋር እየተነጋገረ እንዳለ ለማስመሰል እየሞከረ ነበር ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ አይሆንም!

ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርቱ በመንግሥቱ ውስጥ የተለየ ቦታ እንዲሰጣቸው በጠየቁት ጊዜ “በቀኜ ወይም በግራዬ የመቀመጡ ጉዳይ . . . አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” ሲል መለሰላቸው። (ማቴዎስ 20:23) ኢየሱስ የጠየቁትን ነገር የማድረግ ሥልጣን እንደሌለው በተናገረ ጊዜ እየዋሻቸው ነበር? በፍጹም! ከዚህ ይልቅ እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎችን የማድረግ ሥልጣን ያለው አባቱ ብቻ እንደሆነ በትሕትና ገልጿል። በተጨማሪም ኢየሱስ ከአባቱ በስተቀር እሱም ሆነ መላእክት የማያውቋቸው አንዳንድ ነገሮች እንዳሉ ተናግሯል።—ማርቆስ 13:32

ኢየሱስ ከአምላክ ያንስ የነበረው ሰው ሆኖ እዚህ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ብቻ ነው? አይደለም። ኢየሱስ ከሞተና ከተነሳ በኋላም እንኳ ከአምላክ እንደሚያንስ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ሐዋርያው ጳውሎስ ‘አምላክ በክርስቶስ ላይ ሥልጣን እንዳለው’ ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 11:3 የ1980 ትርጉም) መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት “ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥልጣን ሥር ከሆነ በኋላ፣ እግዚአብሔር አብ በሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው፣ ወልድ ራሱ፣ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር በአደረገለት በእግዚአብሔር አብ ሥልጣን ሥር ይሆናል” ይላል።—1 ቆሮንቶስ 15:28 የ1980 ትርጉም

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ እንዳልሆነ በግልጽ ማየት ይቻላል። ከዚህም የተነሳ አባቱን “አምላኬ” በማለት ጠርቶታል።—ራእይ 3:2, 12፤ 2 ቆሮንቶስ 1:3, 4a

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች ከተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ ላይ ገጽ 201-204⁠ን ተመልከት።

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

ኢየሱስ ከአባቱ በስተቀር እሱም ሆነ መላእክት የማያውቋቸው አንዳንድ ነገሮች እንዳሉ ተናግሯል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ