የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 5/1 ገጽ 5-6
  • 2 ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት ቅሰም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት ቅሰም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • አምላክ የሚባለው ማን ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • 2 አምላክ ስለ እኛ አያስብም​—ይህ እውነት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላክን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 5/1 ገጽ 5-6

2 ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት ቅሰም

“የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ስለሆንከው ስለ አንተ . . . እውቀት መቅሰማቸውን መቀጠል አለባቸው።”—ዮሐንስ 17:3

እንቅፋት የሚሆነው ነገር ምንድን ነው? አንዳንዶች አምላክ የሚባል ነገር የለም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ አምላክ የተወሰነ አካል የሌለው ታላቅ ኃይል ነው በማለት ይናገራሉ። አምላክ እውን አካል እንደሆነ የሚያምኑትም ስለ ማንነቱና ስለ ባሕርያቱ እርስ በርስ የሚቃረኑ ትምህርቶችን ያስተምራሉ።

እንቅፋቱን እንዴት ልትወጣው ትችላለህ? ስለ አምላክ እውቀት መቅሰም የምትችልበት አንደኛው መንገድ የፈጠራቸውን ነገሮች መመልከት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ “[የአምላክ] የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል።” (ሮም 1:20) ትኩረት ሰጥተህ ተፈጥሮን በመመልከት ፈጣሪያችን ስላለው ጥበብና ኃይል ብዙ ትምህርት ማግኘት ትችላለህ።—መዝሙር 104:24፤ ኢሳይያስ 40:26

ይሁንና እያንዳንዱ ሰው ስለ አምላክ ባሕርያት ትክክለኛ እውቀት ለማግኘት የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ራሱ መመርመር ይኖርበታል። የሌሎችን አመለካከት በጭፍን ከመቀበል ይልቅ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ተከተል፦ “የዚህን ሥርዓት የአኗኗር ዘይቤ መኮረጅ አቁሙ፤ ከዚህ ይልቅ ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ።” (ሮም 12:2) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ የሚናገራቸውን የሚከተሉትን እውነታዎች እንደ ምሳሌ ተመልከት።

አምላክ የግል ስም አለው። የአምላክ ስም በመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ላይ በሺህ በሚቆጠሩ ቦታዎች ላይ ይገኝ ነበር። በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የአምላክን ስም በዘፀአት 6:3 ላይ ያስገቡት ሲሆን ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ በስሜም እግዚእ ይሖዋ አልታወቅሁላቸውም።”—የ1879 ትርጉም

ይሖዋ አምላክ ስሜት ያለው ሲሆን ሰዎች በሚያደርጉት ነገር ሊደሰት ወይም ሊያዝን ይችላል። ይሖዋ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነፃ ካወጣቸው በኋላ፣ ጥበብ ያዘሉ ምክሮቹን ችላ ያሉባቸው ጊዜያት ነበሩ። በእነዚህ ጊዜያት የዓመፀኝነት አካሄድ መከተላቸው ‘ያሳዘነው’ ከመሆኑም በላይ ድርጊታቸው ‘የእስራኤልን ቅዱስ አስቈጥቶታል።’—መዝሙር 78:40, 41

ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ ያስብልናል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “ሁለት ድንቢጦች የሚሸጡት አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም አይደለም? ሆኖም ከእነሱ አንዷም እንኳ አባታችሁ ሳያውቅ መሬት ላይ አትወድቅም። የእናንተ ግን የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል። ስለዚህ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።”—ማቴዎስ 10:29-31

አምላክ አንዱን ዘር ወይም ባሕል ከሌላው አስበልጦ አይመለከትም። ሐዋርያው ጳውሎስ በአቴንስ ይኖሩ ለነበሩ ግሪካውያን “በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም [አምላክ] የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ” ብሏቸው ነበር። በተጨማሪም “እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ . . . አይደለም” ሲል ተናግሯል። (የሐዋርያት ሥራ 17:26, 27) ሐዋርያው ጴጥሮስም እንዲህ ብሏል፦ “አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና የጽድቅ ሥራ የሚሠራ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ምን በረከት ያስገኛል? አንዳንዶች “በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ አይሁን እንጂ ለአምላክ ቅንዓት [አላቸው]።” (ሮም 10:2) አምላክን በተመለከተ ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማግኘትህ በሐሰት ትምህርት ከመታለል የሚጠብቅህ ከመሆኑም ሌላ ‘ወደ አምላክ እንድትቀርብ’ ይረዳሃል።—ያዕቆብ 4:8

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?a ከተባለው መጽሐፍ ላይ “አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?” የሚለውን ምዕራፍ 1⁠ን ተመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ስለ አምላክ እውቀት መቅሰም የምትችልበት አንደኛው መንገድ የፈጠራቸውን ነገሮች መመልከት ነው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ