የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 11/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመማፀኛ ከተሞች የአምላክ የምሕረት ዝግጅት ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጋችሁታል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • “በመማፀኛው ከተማ” ውስጥ ቆይተህ ሕይወትህን አድን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ‘የይሖዋን ስም መጠጊያችሁ አድርጉት’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 11/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ሐዋርያው ጳውሎስ “የኢየሱስ ባሪያ [መሆኑን] የሚያሳይ መለያ ምልክት” በሰውነቱ ላይ እንዳለ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?—ገላትያ 6:17

▪ ጳውሎስ የተናገረውን ይህን ሐሳብ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በተለያየ መንገድ ተረድተውት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ በጥንት ጊዜ የጦር እስረኞች፣ የቤተ መቅደስ ዘራፊዎች ወይም ከጌቶቻቸው የኮበለሉ ባሪያዎች በጋለ ብረት ምልክት ይደረግባቸው ነበር። እንዲህ ያለው ምልክት የሚያሳፍር እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር።

ይሁንና መለያ ምልክቶች አሳፋሪ እንደሆኑ ተደርገው የሚታዩት ሁልጊዜ አልነበረም። በጥንት ጊዜ የነበሩ ብዙ ሕዝቦች የአንድ ጎሣ ወይም ሃይማኖት አባል መሆናቸውን ለማሳወቅ እንደዚህ ያለ መለያ ምልክት በሰውነታቸው ላይ ያደርጉ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ቲኦሎጂካል ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ኒው ቴስታመንት የተባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው “የሶርያ ሰዎች ሐዳድ እና አታርጋቲስ ለተባሉት አማልክት ራሳቸውን መቀደሳቸውን ለማሳየት የእጃቸውን አንጓ ወይም አንገታቸውን በመተኮስ ምልክት ይደረግባቸው ነበር፤ . . . ዳዮናይሰስ [የተባለው አምላክ] ተከታዮች ደግሞ [ሰውነታቸውን በመተኮስ] የሐረግ ቅጠል ምልክት ያደርጋሉ።”

በዘመናችን ያሉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች፣ ጳውሎስ የጠቀሰው ምልክት የሚስዮናዊነት አገልግሎቱን ሲያከናውን በተለያዩ ጊዜያት በመደብደቡ በሰውነቱ ላይ የቀረውን ጠባሳ የሚጠቁም እንደሆነ ይናገራሉ። (2 ቆሮንቶስ 11:23-27) ምናልባትም ጳውሎስ ከላይ ያለውን ሐሳብ ሲናገር ቃል በቃል በሰውነቱ ላይ ምልክት እንዳለ መናገሩ ሳይሆን የተከተለው የሕይወት ጎዳና ክርስቲያን መሆኑን ለይቶ እንደሚያሳውቅ መግለጹ ሊሆን ይችላል።

በጥንቷ እስራኤል የነበሩት የመማጸኛ ከተሞች የወንጀለኞች መደበቂያ ሆነው ነበር?

▪ በጥንቶቹ አረማውያን ዘመን በርካታ ቤተ መቅደሶች ለኮበለሉ ሰዎች ወይም ለወንጀለኞች መደበቂያ ነበሩ። በመካከለኛው ዘመን ደግሞ በሕዝበ ክርስትና ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ይሸሸጉ ነበር። ይሁንና በጥንቷ እስራኤል የነበረው ሕግ፣ መማጸኛ ከተሞች የወንጀለኞች መደበቂያ እንዳይሆኑ ይከላከል ነበር።

የሙሴ ሕግ፣ አንድ ሰው በመማጸኛ ከተሞች ውስጥ ጥበቃ ማግኘት የሚችለው ሕይወት ያጠፋው ሳያስበው ከሆነ ብቻ እንደሆነ ይገልጻል። (ዘዳግም 19:4, 5) ግለሰቡ፣ የሟቹ የቅርብ ዘመድ የሆነ ሰው አግኝቶ እንዳይበቀለው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የመማጸኛ ከተማ መሸሽ ይችላል። ሸሽቶ ወደ መማጸኛ ከተማ የሄደው ሰው የተፈጸመውን ነገር ለከተማው ሽማግሌዎች ይናገራል፤ ከዚያም ሟቹ የተገደለበትን አካባቢ በሚያስተዳድሩት ሽማግሌዎች ፊት ለፍርድ ይቀርባል። በዚህ ጊዜ፣ የሰው ሕይወት ያጠፋው ባለማወቅ እንደሆነ ለማስረዳት አጋጣሚ ያገኛል። ሽማግሌዎቹ፣ በሞተው ሰውና ሳያስበው ሕይወት ባጠፋው ሰው መካከል ያለውን ግንኙነት ማለትም ከዚህ ቀደም በመካከላቸው ቅራኔ መኖር አለመኖሩን ይመረምራሉ።—ዘኍልቍ 35:20-24፤ ዘዳግም 19:6, 7፤ ኢያሱ 20:4, 5

ሸሽቶ የመጣው ግለሰብ፣ ጥፋተኛ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ወደ መማጸኛው ከተማ የሚመለስ ሲሆን ከዚያ በኋላም ከከተማው ወሰን መውጣት አይኖርበትም። እነዚህ ከተሞች እስር ቤቶች አልነበሩም። ሸሽቶ የመጣው ሰው ይሠራ እንዲሁም ለኅብረተሰቡ ጠቃሚ ድርሻ ያበረክት ነበር። ወደ መማጸኛው ከተማ ሸሽተው የመጡ ሰዎች ሁሉ ሊቀ ካህናቱ ሲሞት ከተማውን ለቀው መሄድ ይችላሉ።—ዘኍልቍ 35:6, 25-28

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

የመማጸኛ ከተሞች

1 ቃዴስ

2 ጎላን

3 ራሞት ገለዓድ

4 ሴኬም

5 ቦሶር

6 ኬብሮን

ዮርዳኖስ ወንዝ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ