የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 11/15 ገጽ 20-21
  • ‘ለይሖዋ መባ አድርገን እናቅርብ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ለይሖዋ መባ አድርገን እናቅርብ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን “በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ” ማገልገል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ከልብ ተነሳስቶ በደስታ መስጠት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ‘የልግስና ስጦታ ለመስጠት የሚያስችል መብት’ በማግኘትህ ደስተኛ ነህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • “የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 11/15 ገጽ 20-21

‘ለይሖዋ መባ አድርገን እናቅርብ’

አንድ ሰው ደግነት ሲያሳይህ አድናቆትህን ለመግለጽ ምን ታደርጋለህ? በእስራኤል የነበሩ የጦር አዛዦች ከምድያማውያን ጋር ከተዋጉ በኋላ ለይሖዋ ምስጋናቸውን ለመግለጽ ምን እንዳደረጉ እንመልከት። ጦርነቱ የተካሄደው እስራኤላውያን የፌጎርን በኣል በማምለክ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ ነበር። በዚህ ጦርነት አምላክ ለሕዝቡ ድል ያጎናጸፋቸው ሲሆን የተገኘው ምርኮ ለሁለት ተከፍሎ ለ12,000ዎቹ ወታደሮችና ለተቀሩት እስራኤላውያን ተከፋፈለ። ከዚያም ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ወታደሮቹ ከራሳቸው ድርሻ የተወሰነውን ለካህናቱ የሰጡ ሲሆን የተቀሩት እስራኤላውያን ደግሞ ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ የተወሰነውን ለሌዋውያኑ ሰጡ።—ዘኍ. 31:1-5, 25-30

ይሁንና የጦር አዛዦቹ በዚህ አልረኩም። ለሙሴ “እኛ አገልጋዮችህ በእጃችን ሥር ያሉትን ወታደሮች ቈጥረናል፤ አንድም የጐደለ የለም” አሉት። በመሆኑም ወርቅና የተለያዩ ጌጣ ጌጦችን ለይሖዋ መባ አድርገው ለመስጠት ወሰኑ። ለይሖዋ የሰጡት የወርቅ ጌጣ ጌጥ በአጠቃላይ ከ190 ኪሎ ግራም በላይ ይመዝን ነበር።—ዘኍ. 31:49-54

በዛሬው ጊዜም በርካታ ሰዎች ይሖዋ ላደረገላቸው ነገር ከዚህ ጋር በሚመሳሰል መንገድ አመስጋኝነታቸውን ይገልጻሉ። ደግሞም እንዲህ ያለ አመስጋኝነት የሚያሳዩት የአምላክ አገልጋዮች ብቻ አይደሉም። በቦሎኛ፣ ጣሊያን በ2009 በተደረገው ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ላይ ልዑካንን ወደ ስታዲየም ሲያመላልሳቸው የነበረን አንድ የአውቶቡስ ሹፌር እንደ ምሳሌ እንመልከት። ሹፌሩ በእርጋታና በጥንቃቄ ያሽከረክር ስለነበር በአውቶቡሱ ላይ ተሳፍረው የነበሩት ወንድሞችና እህቶች ምስጋናቸውን የሚገልጽ ካርድና የተወሰነ ጉርሻ እንዲሁም ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ሊሰጡት ፈለጉ። ሹፌሩም እንዲህ አላቸው፦ “ካርዱንና መጽሐፉን በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ገንዘቡን ግን ለምትሠሩት ሥራ እንድታውሉት መዋጮ ማድረግ እፈልጋለሁ። የይሖዋ ምሥክር ባልሆንም እንኳ የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር ተነሳስታችሁ እንደምታከናውኑ ስለተመለከትሁ ይህን መዋጮ ማድረግ እፈልጋለሁ።”

ይሖዋ ላደረገልህ ነገር አመስጋኝነትህን መግለጽ የምትችልበት አንዱ መንገድ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚያከናውኑት ዓለም አቀፍ ሥራ መዋጮ ማድረግ ነው። (ማቴ. 24:14) አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች በሣጥኑ ውስጥ ተዘርዝረዋል።

አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

ለዓለም አቀፉ ሥራ የሚደረጉ መዋጮዎች

ብዙዎች “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ።

ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ በአገራቸው ሥራውን ለሚቆጣጠረው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። ከዚህ በተጨማሪ በፈቃደኝነት የሚደረጉ የገንዘብ መዋጮዎችን በቀጥታ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ በሚለው አድራሻ ወይም ባላችሁበት አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ መላክ ይቻላል። (ከታች በተዘረዘሩት መንገዶች በፈቃደኝነት የሚደረጉ ስጦታዎችንም ባላችሁበት አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ መላክ ይቻላል።) ቼኮች ለ“የይሖዋ ምሥክሮች” የሚከፈሉ መሆናቸው መገለጽ አለበት። ከውድ ማዕድናት የተሠሩ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ዕቃዎችንም መስጠት ይቻላል። የተላከው ዕቃ ሙሉ በሙሉ ስጦታ መሆኑን የሚገልጽ አጭር ደብዳቤ ተያይዞ መላክ ይኖርበታል።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

አንድ ሰው ገንዘቡን የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት ዓለም አቀፉን ሥራ ለማካሄድ እንዲጠቀምበት በአደራ መልክ ሊሰጥና ሲያስፈልገው ድርጅቱን በመጠየቅ መልሶ ማግኘት ይችላል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከላይ በተገለጸው አድራሻ በመጻፍ ወይም በስልክ ቁጥር 011-6603611 በመደወል የይሖዋ ምሥክሮችን ቅርንጫፍ ቢሮ መጠየቅ ይቻላል።

በእቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብ በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶችም አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

ኢንሹራንስ፦

የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ስም ሊዛወርለት ይችላል።

የባንክ ሒሳብ፦

የአገሩ ባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦች፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምሥክር ወረቀት ወይም የግል ጡረታ ሒሳቦች በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት ሊሰጥ ይችላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦

አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት መስጠት ይቻላል፤ ወይም ደግሞ በሞት ጊዜ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዲሰጥ ስም ሊዛወርለት ይችላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦

ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል ቋሚ ንብረት በስጦታ መስጠት ወይም መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ተጠቅሞበት ከዚያ በኋላ ማውረስ ይቻላል። አንድ ሰው ማንኛውንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ከማዛወሩ በፊት በአገሩ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር መነጋገር ይኖርበታል።

የስጦታ አበል፦

የስጦታ አበል አንድ ሰው ገንዘቡን ወይም የባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን የይሖዋ ምሥክሮችን ወክሎ ለሚሠራው ድርጅት ለማዛወር የሚያደርገውን ዝግጅት ያመለክታል። በምላሹም ለጋሹ ወይም እሱ የወከለው ግለሰብ በሕይወት እስካለበት ጊዜ ድረስ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየዓመቱ በአበል መልክ ይከፈለዋል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦

ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት በውርስ ሊሰጥ ወይም የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ ተደርጎ ስሙ ሊዛወር ይችላል።

“በእቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ እቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በእቅድ በሚደረግ ስጦታ ለመደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በእቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር በእንግሊዝኛና በስፓንኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ሰዎች ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ ለመተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ ለመስጠት ነው። ብዙዎች ይህን ብሮሹር ካነበቡ በኋላ ከሕግ ወይም ከቀረጥ አማካሪዎቻቸው ጋር በመማከር በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ ለመደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት ችለዋል። ይህን ብሮሹር ለማግኘት በእቅድ የሚደረግ ስጦታን ጉዳይ የሚከታተለውን ቢሮ በቀጥታ መጠየቅ ይቻላል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ተጠቅመህ ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላለህ። አሊያም ባለህበት አገር ለሥራው አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ ማነጋገር ትችላለህ።

የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት

ፖ.ሣ.ቁ. 5522

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

ስልክ:- 011-6603611

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ