የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 11/15 ገጽ 22
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ፍጹም የሆነ ሕይወት ሕልም አይደለም!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ‘እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ወዶናል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • የይሖዋ ዓላማ ይፈጸማል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 11/15 ገጽ 22

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ አድማጮቹን “በሰማይ ያለው አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” ብሏቸው ነበር። በዛሬው ጊዜስ ሰዎች ‘ፍጹማን ሊሆኑ’ የሚችሉት እንዴት ነው?—ማቴ. 5:48

ይህን ጥያቄ ለመመለስ ቁልፍ የሆነው ነገር “ፍጹም” እና “ፍጽምና” የሚሉት ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት እንደተሠራባቸው መረዳት ነው። ቅዱሳን መጻሕፍት “ፍጹም” ብለው የሚገልጿቸው ነገሮች፣ ሙሉ በሙሉ ፍጹም የሆነን ነገር ላያመለክቱ ይችላሉ። እርግጥ ነው፣ ይሖዋ ሙሉ በሙሉ ፍጹም ነው። ሰዎች ወይም ነገሮች ግን ፍጹም ሊሆኑ የሚችሉት በአንጻራዊ ሁኔታ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ፍጹም” ተብለው የተተረጎሙት የዕብራይስጥና የግሪክኛ ቃላት ብዙውን ጊዜ፣ ሥልጣን ያለው አካል ባወጣው መሥፈርት መሠረት “የተሟላ” ወይም “እንከን የለሽ” መሆን ወይም “የበሰለና ያደገ” የሚል ፍቺ አላቸው።

አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ በሥነ ምግባር እንዲሁም በመንፈሳዊና በአካላዊ ሁኔታ ፍጹም ነበሩ። ፈጣሪያቸው ባወጣው መሥፈርት መሠረት ፍጹም ነበሩ። ይሁንና አዳምና ሔዋን ባለመታዘዛቸው የፈጣሪያቸውን መሥፈርት ሳያሟሉ ቀርተዋል፤ በዚህም ምክንያት ፍጽምናቸውን ያጡ ከመሆኑም በላይ አለፍጽምናን ለዘሮቻቸው አወረሱ። በመሆኑም በአዳም አማካኝነት ኃጢአት፣ አለፍጽምናና ሞት ለሰው ዘር ተዳረሰ።—ሮም 5:12

ይሁን እንጂ ኢየሱስ በተራራው ስብከቱ ላይ እንደገለጸው ፍጹም ያልሆኑ ሰዎችም እንኳ በአንጻራዊ ሁኔታ ፍጹም ሊሆኑ ይችላሉ። ኢየሱስ ፍጹም ወይም የተሟላ ለሆነ ፍቅር መሥፈርቱ ምን እንደሆነም በተራራ ስብከቱ ላይ ተናግሯል። ፍጹም የተባለው ይህ ፍቅር፣ አምላክ ለሰው ዘር ያሳየው ዓይነት ፍቅር ነው። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ለጠላቶቻችሁ ፍቅር ማሳየታችሁን እንዲሁም ስደት ለሚያደርሱባችሁ መጸለያችሁን ቀጥሉ፤ ይህን ብታደርጉ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። ምክንያቱም እሱ በክፉና በጥሩ ሰዎች ላይ ፀሐዩን ያወጣል፤ ጻድቅ በሆኑና ጻድቅ ባልሆኑ ሰዎች ላይም ዝናብ ያዘንባል።” (ማቴ. 5:44, 45) የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለጠላቶቻቸው እንኳ ፍቅር በማሳየት አምላክ የተወውን ፍጹም ምሳሌ ይከተላሉ።

በዛሬው ጊዜ በምድር ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች እንዲህ ዓይነቱን ላቅ ያለ ፍቅር ለሌሎች ለማሳየት ጥረት ያደርጋሉ። የይሖዋ ምሥክሮች የተለያየ የኑሮ ደረጃ፣ ዘርና ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ የመርዳት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። በአሁኑ ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች በ236 አገሮች ከ7,000,000 የሚበልጡ ፍላጎት ያላቸው ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ እያስጠኑ ነው።

ኢየሱስ “የሚወዷችሁን ብቻ ብትወዱ ምን ብድራት ታገኛላችሁ? ቀረጥ ሰብሳቢዎችስ የሚያደርጉት ይህንኑ አይደለም? ደግሞስ ወንድሞቻችሁን ብቻ ሰላም ብትሉ ምን የተለየ ነገር ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ የሚያደርጉት ይህንኑ አይደለም?” በማለት ጠይቋል። (ማቴ. 5:46, 47) እውነተኛ ክርስቲያኖች የሰዎችን የትምህርት ደረጃ ወይም ዘር በመመልከት አያዳሉም፤ የሚወዱትም ብድራት የሚመልሱላቸውን ሰዎች ብቻ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ድሃ፣ በሽተኛ፣ ወጣት አረጋዊ ሳይሉ ሁሉንም ዓይነት ሰው ይረዳሉ። እንዲህ በማድረግ ክርስቲያኖች ፍቅር በማሳየት ረገድ የይሖዋን አርዓያ ይከተላሉ፤ በዚህ መንገድ በአንጻራዊ ሁኔታ ፍጹማን ይሆናሉ።

አዳም ያጣውን ፍጽምና መልሰን እናገኝ ይሆን? አዎን፣ በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ እምነት ያሳደሩ ታዛዥ የሰው ልጆች በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት ሙሉ በሙሉ ፍጹም ወደመሆን ደረጃ ይደርሳሉ፤ በዚህ ወቅት ‘የአምላክ ልጅ የዲያብሎስን ሥራ ያፈርሳል።’—1 ዮሐ. 3:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ