የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 4/1 ገጽ 24-25
  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?
    ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • እንደ ኤልያስ ታማኝ ትሆናላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 4/1 ገጽ 24-25

ልጆቻችሁን አስተምሩ

ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ሰዎች ብቸኛ እንደሆኑ ይሰማቸዋል፤ እነዚህ ሰዎች የሚያስብላቸው እንዳለ አይሰማቸውም። ብዙውን ጊዜ በዕድሜ የገፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ስሜት ያጠቃቸዋል። ይሁንና በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ልጆችም ሌላው ቀርቶ አምላክን የሚያገለግሉት እንኳ ብቸኝነትና ፍርሃት ይሰማቸዋል። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?—a

በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። እስቲ ከረጅም ጊዜ በፊት የኖረን አንድ ሰው እንደ ምሳሌ እንመልከት። ይህ ሰው የኖረው ኢየሱስ ከመወለዱ ከአንድ ሺህ ዓመት ገደማ በፊት ሲሆን ስሙ ኤልያስ ይባላል። ኤልያስ የኖረው እስራኤላውያን እውነተኛውን አምላክ ይሖዋን ማገልገላቸውን በተዉበት ወቅት ነበር። አብዛኞቹ የሐሰት አምላክ የሆነውን በኣልን ማምለክ ጀምረው ነበር። ኤልያስ “የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ” በማለት ተናግሯል። ይሁንና በእርግጥ አምላክን እያገለገለ የነበረው ኤልያስ ብቻ ይመስልሃል?—

ኤልያስ አይወቀው እንጂ በእስራኤል የሚኖሩ ሌሎች ሰዎችም አምላክን በታማኝነት እያመለኩ ነበር። ይሁንና እነዚህ ሰዎች ስለፈሩ ተደብቀው ነበር። ለምን እንደፈሩ ታውቃለህ?—

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የእስራኤል ንጉሥ የሆነው አክዓብ አምላክን የሚያገለግል ሰው አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ ክፉ የሆነችው ሚስቱ ኤልዛቤል የምታመልከውን በኣልን ያመልክ ነበር። ስለዚህ ኤልዛቤልና አክዓብ ይሖዋን የሚያገለግሉ ሰዎችን በተለይ ደግሞ ኤልያስን አድነው ለመግደል ጥረት እያደረጉ ነበር። ኤልያስ የሸሸው በዚህ ምክንያት ነው። ኤልያስ 483 ኪሎ ሜትር ያህል በምድረ በዳ ተጉዞ ወደ ኮሬብ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስፍራ ሲና ብሎም ይጠራዋል። ኤልያስ ከኖረበት በመቶ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ይሖዋ አሥርቱን ትእዛዛትና ሌሎቹን ሕግጋት ለሕዝቡ የሰጠው በዚሁ ቦታ ነበር። ኤልያስ በኮሬብ በሚገኝ አንድ ዋሻ ውስጥ ብቻውን ተደበቀ። ኤልያስ መፍራቱ ተገቢ ይመስልሃል?—

ቀደም ሲል ይሖዋ ታላላቅ ተአምራትን ለመፈጸም በኤልያስ ተጠቅሞ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በአንድ ወቅት ይሖዋ እሳት ከሰማይ ወርዶ መሥዋዕቱን እንዲበላ ኤልያስ ላቀረበው ጸሎት መልስ ሰጥቶ ነበር። በዚህ መንገድ ይሖዋ እውነተኛው አምላክ እሱ እንጂ በኣል እንዳልሆነ አስመሥክሯል። አሁን ደግሞ ይሖዋ፣ ኤልያስን በዋሻው ውስጥ እያለ አናገረው።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ይሖዋ “እዚህ ምን ታደርጋለህ?” በማለት ኤልያስን ጠየቀው። ኤልያስ ‘አንተን ከሚያመልኩት ውስጥ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ’ በማለት የተናገረው በዚህ ጊዜ ነው። ከዚያም ይሖዋ ‘አሁንም እኔን የሚያገለግሉ ሰባት ሺህ ሰዎች አሉኝ’ በማለት ኤልያስ አመለካከቱን እንዲያስተካክል በደግነት ረዳው። ይሖዋ፣ ኤልያስ ገና ብዙ ሥራ እንዳለው በመግለጽ እንዲመለስ ነገረው።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኤልያስ ካጋጠመው ሁኔታ ምን ትምህርት ማግኘት የምንችል ይመስልሃል?— አንዳንድ ጊዜ ይሖዋን የሚያገለግሉ ሰዎች እንኳ ፍርሃት ሊሰማቸው ይችላል። ስለዚህ ልጅ አዋቂ ሳንል ሁላችንም የይሖዋን እርዳታ መጠየቅ እንዳለብን ማስታወስ ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ . . . ቅርብ ነው” የሚል ማረጋገጫ ይሰጣል።

ኤልያስ ካጋጠመው ሁኔታ የምንማረው ሌላም ቁም ነገር አለ፤ በመላው ዓለም ይሖዋንም ሆነ እኛን የሚወዱ ወንድሞችና እህቶች አሉን። መጽሐፍ ቅዱስ “በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት [ወንድሞቻችን] ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ” ይናገራል። ታዲያ ፈጽሞ ብቻችንን እንዳልሆንን ማወቅህ አያስደስትህም?—

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ

  • 1 ነገሥት 19:3-18⁠ን፤

  • ዘዳግም 5:1-22⁠ን፤

  • መዝሙር 145:18⁠ን እና

  • 1 ጴጥሮስ 5:9⁠ን አንብብ።

a ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ