የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 5/1 ገጽ 4
  • ትንቢት 1. የምድር ነውጦች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትንቢት 1. የምድር ነውጦች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታላላቅ የምድር ነውጦች—የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ሌሎች ከባድ የመሬት ነውጦች እንደሚከሰቱ ይጠበቃል
    ንቁ!—2010
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2010
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 5/1 ገጽ 4

ትንቢት 1. የምድር ነውጦች

“ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ።”​—ሉቃስ 21:11

● ሄይቲ ውስጥ ዊኒ የተባለች የዓመት ከአራት ወር ሕፃን ከተቀበረችበት ፍርስራሽ ወጣች። ስለ አደጋው ሲዘግብ የነበረ አንድ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ቡድን ዊኒ ስታቃስት ሰማ። በመሆኑም ሕፃኗ በሕይወት ስትተርፍ ወላጆቿ ግን በደረሰው የምድር ነውጥ ሳቢያ ሞቱ።

እውነታው ምን ያሳያል? ጥር 2010 ላይ ሄይቲ በሬክተር መለኪያ 7.0 በደረሰ ርዕደ መሬት ስትመታ ከ300,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በቅጽበት ቤት አልባ ሆነዋል። በሄይቲ የደረሰው ነውጥ ከፍተኛ ቢሆንም እንዲህ ያለ ከባድ ነውጥ በምድራችን ላይ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው አይደለም። ከሚያዝያ 2009 እስከ ሚያዝያ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 18 ከባባድ የምድር ነውጦች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተከስተዋል።

በተደጋጋሚ የሚሰነዘረው የተቃውሞ ሐሳብ ምንድን ነው? ድሮ ከኖሩት ሰዎች በበለጠ ዘመናዊው ቴክኖሎጂ የተከሰቱትን ነውጦች ብዛት እንድናውቅ ስላደረገን ነው እንጂ የሚከሰቱት የመሬት ነውጦች ቁጥር ጨምሮ አይደለም።

ይህ የተቃውሞ ሐሳብ ትክክል ነው? የሚከተለውን እውነታ ልብ በል፦ መጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት ያደረገው በመጨረሻዎቹ ቀናት በሚከሰቱት የምድር ነውጦች ብዛት ላይ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው “ታላላቅ የምድር ነውጦች” “በተለያየ ስፍራ” እንደሚከሰቱ ነው፤ ይህ ደግሞ የምንኖረው ወሳኝ በሆነ የታሪክ ወቅት ላይ መሆኑን ለይተው ከሚያሳውቁን ነገሮች አንዱ ነው።​—ማርቆስ 13:8፤ ሉቃስ 21:11

ምን ይመስልሃል? መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ታላላቅ የምድር ነውጦች እየተከሰቱ እንደሆነ ይሰማሃል?

የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የመሬት ነውጦች ብቻቸውን በቂ ማስረጃ ሆነው ላይታዩህ ይችላሉ። የመሬት ነውጥ በዛሬው ጊዜ እየተፈጸሙ ካሉት ትንቢቶች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው። እስቲ ሁለተኛውን ትንቢት እንመልከት።

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

“እኛ የሥነ ምድር ፊዚክስ ባለሙያዎች [ርዕደ መሬቶቹን] ታላላቅ የምድር ነውጦች እንላቸዋለን። ሌሎች ሰዎች ደግሞ አሰቃቂ ክስተቶች ይሏቸዋል።”​—ኬን ሃድነት፣ የዩ ኤስ የጂኦሎጂ ጥናት ተቋም

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© William Daniels/Panos Pictures

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ