የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 7/1 ገጽ 16-17
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 7/1 ገጽ 16-17

ከአምላክ ቃል ተማር

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች በመልሶቹ ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት በሰማይ የሚገኝ መስተዳድር ነው። ሌሎች ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ አጥፍቶ የአምላክ ፈቃድ በሰማይና በምድር ላይ እንዲሆን ያደርጋል። በመሆኑም ጥሩ አገዛዝ ለማግኘት ያለንን ፍላጎት የሚያሟላልን የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው።​—ዳንኤል 2:44⁠ን እና ማቴዎስ 6:9, 10⁠ን አንብብ።

የትኛውም መንግሥት ንጉሥ እንደሚያስፈልገው የታወቀ ነው። ይሖዋ ልጁን ኢየሱስን የመንግሥቱ ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል።​—ሉቃስ 1:30-33⁠ን አንብብ።

2. ኢየሱስ ብቃት ያለው መሪ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

የአምላክ ልጅ ብቃት ያለው መሪ ነው፤ ምክንያቱም እሱ ደግ ብሎም ትክክል የሆነውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይል ነው፤ እንዲሁም ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም አለው። (ማቴዎስ 11:28-30) ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ በመሄድ ሥልጣኑን እስኪያገኝ ድረስ በይሖዋ ቀኝ ሆኖ ይጠባበቅ ጀመር። (ዕብራውያን 10:12, 13) በመጨረሻም አምላክ በሰማይ ሆኖ መግዛት እንዲጀምር ሥልጣን ሰጠው።​—ዳንኤል 7:13, 14⁠ን አንብብ።

3. ከኢየሱስ ጋር አብረው የሚገዙ አሉ?

አምላክ፣ ከኢየሱስ ጋር በመሆን በሰማይ የሚገዛ “ቅዱሳን” ተብሎ የሚጠራ አንድ ቡድን መርጧል። (ዳንኤል 7:27) ቅዱሳን በተባለው ቡድን ውስጥ እንዲታቀፉ በመጀመሪያ የተመረጡት የኢየሱስ ታማኝ ሐዋርያት ነበሩ። ይሖዋ ቅዱሳን በተባለው ቡድን ውስጥ የሚካተቱ ታማኝ ወንዶችንና ሴቶችን አሁንም መምረጡን ቀጥሏል። እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ ኢየሱስ መንፈሳዊ አካል ይዘው ከሞት ይነሳሉ።​—ዮሐንስ 14:1-3⁠ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:42-45⁠ን አንብብ።

ወደ ሰማይ የሚሄዱት ሰዎች ምን ያህል ናቸው? ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች “ትንሽ መንጋ” በማለት ጠርቷቸዋል። (ሉቃስ 12:32) አጠቃላይ ቁጥራቸው 144,000 ሲሆን ከኢየሱስ ጋር በመሆን ምድርን ይገዛሉ።​—ራእይ 5:9, 10⁠ን እና 14:1⁠ን አንብብ።

4. የአምላክ መንግሥት መግዛት የጀመረው መቼ ነው?

ኢየሱስ በ1914 መግዛት ጀምሯል።a ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰይጣንንና አጋንንቱን ወደ ምድር ወርውሯቸዋል። (ራእይ 12:7-10, 12) ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሄዷል። ጦርነት፣ የምድር ነውጥ፣ ረሃብ፣ ወረርሽኝና ዓመፅ አሁን ያለው ሥርዓት በመጨረሻዎቹ ቀኖች ላይ እንደሚገኝ የሚጠቁመው ምልክት ክፍል ናቸው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) የአምላክ መንግሥት ከሚያመጣው በረከት ጥቅም ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ የንጉሡ የኢየሱስ ተከታዮች መሆን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ መማር ይኖርባቸዋል።​—ሉቃስ 21:7, 10, 11, 31, 34, 35⁠ን አንብብ።

5. የአምላክ መንግሥት ምን ያከናውናል?

የአምላክ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የስብከት ሥራ አማካኝነት ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ አምላክ እንዲማሩ እየረዳ ነው። (ማቴዎስ 24:14) ይህ መንግሥት በምድር ላይ ያለውን ክፉ ሥርዓት በሚያጠፋበት ጊዜ የኢየሱስ ታማኝ ተገዢ የሆኑትን “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ያድናቸዋል።​—ራእይ 7:9, 10, 13-17⁠ን አንብብ።

ይህ መንግሥት በ1,000 ዓመት ውስጥ ምድርን ቀስ በቀስ ወደ ገነትነት ይለውጣል። በመጨረሻም ኢየሱስ መንግሥቱን ለአባቱ ያስረክባል። (1 ቆሮንቶስ 15:24-26) ታዲያ አንተ ስለ አምላክ መንግሥት ልትነግረው የምትችለው ሰው አለ?​—መዝሙር 37:10, 11, 29⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 እና 9 ተመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ኢየሱስ በ1914 መግዛት መጀመሩን የሚጠቁሙት እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 215-218 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ