የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 12/1 ገጽ 16-17
  • ጥሩ ጓደኞች መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥሩ ጓደኞች መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን የሚወዱ ጓደኞችን ምረጥ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • የምትፈልገው ምን ዓይነት ጓደኞችን ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 12/1 ገጽ 16-17

ከአምላክ ቃል ተማር

ጥሩ ጓደኞች መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው?

ይህ ርዕስ በአእምሮህ ሊመላለሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን በማንሳት መልሶቹን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ቦታ ላይ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁምሃል። የይሖዋ ምሥክሮች ለጥያቄዎቹ በተሰጡት መልሶች ላይ ከአንተ ጋር ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።

1. ጓደኞቻችንን በጥበብ መምረጥ የሚኖርብን ለምንድን ነው?

ብዙዎቻችን በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት እንፈልጋለን። ይህ ፍላጎታችን ደግሞ ብዙውን ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን እንድንመስል ያነሳሳናል። በመሆኑም ጓደኞቻችን በዝንባሌያችን ላይ ይህ ነው የማይባል ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ስለዚህ የጓደኛ ምርጫችን በባሕርያችን ላይ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።​—ምሳሌ 4:23⁠ን እና ምሳሌ 13:20⁠ን አንብብ።

በመንፈስ መሪነት የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍል የጻፈው ዳዊት ጓደኞቹን በጥበብ መርጧል። ወዳጆቹ፣ የአምላክ አገልጋይ ሆኖ ንጹሕ አቋሙን እንዲጠብቅ ሊረዱት የሚችሉ ነበሩ። (መዝሙር 26:4, 5, 11, 12) ለምሳሌ ዳዊት፣ ዮናታንን ለጓደኝነት የመረጠው ዮናታን በይሖዋ እንዲታመን ያበረታታው ስለነበረ ነው።​—1 ሳሙኤል 23:16-18⁠ን አንብብ።

2. የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ ሁሉን ቻይ ቢሆንም የእሱ ወዳጅ መሆን እንችላለን። ለምሳሌ አብርሃም የአምላክ ወዳጅ ነበር። አብርሃም በይሖዋ ይታመንና ይታዘዘው ስለነበር ይሖዋ እንደ ወዳጅ ተመልክቶታል። (ዘፍጥረት 22:2, 9-12፤ ያዕቆብ 2:21-23) እኛም በይሖዋ የምንታመንና የሚያዝዘንን የምንፈጽም ከሆነ የአምላክ ወዳጅ መሆን እንችላለን።​—መዝሙር 15:1, 2⁠ን አንብብ።

3. ጥሩ ጓደኞች ሊጠቅሙህ የሚችሉት እንዴት ነው?

እውነተኛ ጓደኞች ታማኝ ከመሆናቸውም ሌላ ትክክል የሆነውን ነገር እንድታደርግ ያበረታቱሃል። (ምሳሌ 17:17፤ 18:24) ለምሳሌ ያህል፣ ዮናታን ዳዊትን 30 ዓመት ገደማ የሚበልጠው ከመሆኑም ሌላ የእስራኤል ንጉሥ የመሆን መብት የነበረው ቢሆንም እንኳ ዳዊት በይሖዋ የተመረጠ ንጉሥ እንደሆነ በመቀበል በታማኝነት ደግፎታል። እውነተኛ ጓደኞች ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ስትፈጽም እርማት ይሰጡሃል። (መዝሙር 141:5) ጓደኞችህ አምላክን የሚወዱ ከሆነ መልካም ባሕርያት እንድታዳብር ይረዱሃል።​—1 ቆሮንቶስ 15:33⁠ን አንብብ።

ትክክል ለሆነው ነገር ያለህን ፍቅር የሚጋሩ ሰዎችን በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ማግኘት ትችላለህ። አምላክን ለማስደሰት ጥረት ስታደርግ የሚያበረታቱህ ጓደኞች እዚያ ታገኛለህ።​—ዕብራውያን 10:24, 25⁠ን አንብብ።

ይሁን እንጂ አምላክን የሚወዱ ጓደኞች እንኳ አንዳንድ ጊዜ ቅር ሊያሰኙን ይችላሉ። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ቢያጋጥምህ ለመቆጣት አትቸኩል። (መክብብ 7:9, 20-22) ፍጹም የሆነ ጓደኛ እንደሌለና አምላክን የሚወዱ ሰዎች ውድ እንደሆኑ መዘንጋት አይኖርብንም። የአምላክ ቃል የእምነት ባልንጀሮቻችንን ስህተት እንዳንለቃቅም ይነግረናል።​—ቆላስይስ 3:13⁠ን አንብብ።

4. ጓደኞቼ የምትላቸው ሰዎች ቢቃወሙህስ?

ብዙ ሰዎች የአምላክን ቃል ማጥናት ሲጀምሩ ከቀድሞ ጓደኞቻቸው መካከል አንዳንዶቹ ይቃወሟቸዋል። ምናልባት ጓደኞችህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘኸውን ጠቃሚ ምክር ወይም እርግጠኛ የሆነ ተስፋ አልተረዱ ይሆናል። እነዚህን ሰዎች ልትረዳቸው ትችል ይሆናል።​—ቆላስይስ 4:6⁠ን አንብብ።

ጓደኞቼ የምትላቸው ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው ምሥራች ላይ ያፌዙ ይሆናል። (2 ጴጥሮስ 3:3, 4) ሌሎች ደግሞ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ስትሞክር ሊያሾፉብህ ይችላሉ። (1 ጴጥሮስ 4:4) ሁኔታው እንዲህ ከሆነ ከጓደኞችህ አሊያም ከአምላክ አንዱን መምረጥ ይኖርብሃል። የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ከመረጥክ ከሁሉ የበለጠውን ወዳጅነት መርጠሃል ማለት ነው።​—ያዕቆብ 4:4, 8⁠ን አንብብ

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 12 እና 19 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ