የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 12/1 ገጽ 30-31
  • “የነጎድጓድ ልጆች” ተብለው ተጠርተዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የነጎድጓድ ልጆች” ተብለው ተጠርተዋል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሁልጊዜ ቅድሚያ ማግኘት ትፈልጋለህ?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ከኢየሱስ ታናሽ ወንድም ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ስለ ኢየሱስ የጻፉ ሰዎች
    ልጆቻችሁን አስተምሩ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 12/1 ገጽ 30-31

ልጆቻችሁን አስተምሩ

“የነጎድጓድ ልጆች” ተብለው ተጠርተዋል

ኃይለኛ ዝናብ እየዘነበ ሳለ ነጎድጓድ ሰምተህ ታውቃለህ? ታዲያ በዚህ ጊዜ ፈራህ?​—a የሚገርመው ነገር ኢየሱስ ከተከታዮቹ መካከል ሁለቱን “የነጎድጓድ ልጆች” በማለት ጠርቷቸዋል። እንደዚህ ብሎ የጠራቸው ለምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

እነዚህ የኢየሱስ ተከታዮች ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው። ያዕቆብና ዮሐንስ ወንድማማቾች ሲሆኑ የዘብዴዎስና የሰሎሜ ልጆች ናቸው። ሰሎሜ ደግሞ የኢየሱስ እናት የሆነችው የማርያም እህት ሳትሆን አትቀርም። ስለዚህ ያዕቆብና ዮሐንስ የኢየሱስ የአክስት ልጆች ብቻ ሳይሆኑ አብሮ አደጎቹም ጭምር ሊሆኑ ይችላሉ።

ዘብዴዎስ እንዲሁም ያዕቆብና ዮሐንስ ዓሣ አጥማጆች ነበሩ። እነዚህ ወንድማማቾች፣ ኢየሱስ ተከታዮቹ እንዲሆኑ መጀመሪያ ከመረጣቸው ሰዎች መካከል ይገኙበታል። ኢየሱስ እንዲከተሉት ሲጋብዛቸው ወዲያውኑ ዓሣ የማጥመድ ሥራቸውን ትተው ተከተሉት። በኋላም ኢየሱስ ከተከታዮቹ መካከል 12ቱን ሐዋርያት አድርጎ መረጣቸው። ያዕቆብና ዮሐንስም ከእነዚህ መካከል ይገኛሉ።

ኢየሱስ ከመገደሉ ከጥቂት ወራት በፊት እሱና ሐዋርያቱ በሰማርያ በሚገኙ ተራሮች መካከል እየተጓዙ ነበር። ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ሁሉም ደክሟቸው ነበር። ሆኖም ሳምራውያኑ ኢየሱስና ሐዋርያቱ ከተማቸው ውስጥ እንዲያድሩ አልፈለጉም። ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?​— እስቲ እንመልከት።

ኢየሱስና ሐዋርያቱ አይሁዳውያን ናቸው፤ አብዛኞቹ አይሁዳውያን ደግሞ ለሳምራውያን ክፉ ነበሩ። እርግጥ ኢየሱስ በሳምራውያን ላይ ክፉ ነገር አያደርግም። ኢየሱስ በደግነት ይይዛቸው የነበረ ሲሆን ያዕቆብና ዮሐንስም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ነበረባቸው። እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት ግን ሳምራውያኑ ሊያሳድሯቸው ስላልፈለጉ በጣም ተናደዱ፤ ከዚያም ኢየሱስን “እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትፈልጋለህ?” ብለው ጠየቁት። ኢየሱስ ምን ብሎ የመለሰላቸው ይመስልሃል?​— መጥፎ ነገር መናገራቸው ስህተት እንደሆነ ገለጸላቸው። ያዕቆብና ዮሐንስ ስለ ምሕረት ትምህርት ማግኘት ያስፈልጋቸው ነበር።

የያዕቆብና የዮሐንስ ሌላው ትልቅ ችግር ደግሞ ሁልጊዜ አንደኛ ለመሆን ወይም ትልቅ ቦታ ለማግኘት መፈለጋቸው ነው። ኢየሱስ ከመሞቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት እናታቸውን ወደ ኢየሱስ ላኳት፤ እሷም “በመንግሥትህ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ፣ አንዱ በቀኝህ አንዱ ደግሞ በግራህ እንዲቀመጡ አድርግልኝ” አለችው። የቀሩት አሥሩ ደቀ መዛሙርት ያዕቆብና ዮሐንስ ያደረጉትን ነገር ሲሰሙ ተናደዱ። አንተስ በእነሱ ቦታ ብትሆን ትናደድ ነበር?​—

ትናደድ ይሆናል። ሌሎች አንደኛ ለመሆን ወይም ትልቅ ቦታ ለማግኘት ሲሞክሩ ደስ አይለንም። ያዕቆብና ዮሐንስ ያደረጉት ነገር ስህተትና ደግነት የጎደለው መሆኑን ከጊዜ በኋላ ሲገነዘቡ ለውጥ አድርገው አፍቃሪና ደግ ሐዋርያት ሆነዋል። ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን?​—

እኛም ብንሆን ለሌሎች ደግነት ማሳየት እንዳለብን ከኢየሱስ እንማራለን። ኢየሱስ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን በሙሉ በደግነት ይይዝ ነበር። የእሱን ምሳሌ ለማስታወስና በሥራ ላይ ለማዋል ሁልጊዜ ጥረት ታደርጋለህ?​—

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ

  • ማርቆስ 3:17⁠ን

  • ማቴዎስ 27:55, 56⁠ን፤ ማርቆስ 15:40, 41⁠ን

  • ማቴዎስ 4:18-22⁠ን

  • ዮሐንስ 4:4-15, 21-26⁠ን፤ ሉቃስ 9:51-55⁠ን እና

  • ማቴዎስ 20:20-24⁠ን፤ ማርቆስ 10:35-37, 41⁠ን አንብብ።

a ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ