የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 3/1 ገጽ 30-31
  • ‘ከይሖዋ ጋር ተጣበቀ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ከይሖዋ ጋር ተጣበቀ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ነፃ ምርጫ በመስጠት አክብሮናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች​—ሕዝቅያስ
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
  • አምላክ ንጉሥ ሕዝቅያስን ረዳው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 3/1 ገጽ 30-31

ልጆቻችሁን አስተምሩ

‘ከይሖዋ ጋር ተጣበቀ’

አንድን ሥዕል ወረቀት ላይ እንድታጣብቅ ተነግሮህ ያውቃል?​—a ሥዕሉን ያጣበቅከው በጥሩ ሙጫ ከሆነ ሥዕሉ ከወረቀቱ ላይ በቀላሉ አይለቅም። መጣበቅ የሚለው ቃል አጥብቆ መያዝን እንዲሁም አለመልቀቅን ያመለክታል። በዚህ ርዕስ ላይ የምንወያየው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእውነተኛው አምላክ ‘ከይሖዋ ጋር እንደተጣበቀ’ ስለተነገረለት አንድ ሰው ነው። ይህ ሰው ሕዝቅያስ ይባላል። ከእሱ ምሳሌ ምን ትምህርት እንደምናገኝ እስቲ እንመልከት።

[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሕዝቅያስ ጥሩ አስተዳደግ አልነበረውም። አባቱ ንጉሥ አካዝ ይሖዋን ማምለኩን አቁሞ ነበር። ሕዝቅያስ ትንሽ ልጅ እያለ አካዝ በሐሰት አምልኮ ተዘፍቆ ነበር። ይባስ ብሎም አካዝ ለሚያመልከው አምላክ መሥዋዕት ለማቅረብ ሲል ቢያንስ ከልጆቹ አንዱን ማለትም የሕዝቅያስን ወንድም ገድሎታል!

አካዝ መጥፎ ነገሮች ማድረጉን ቢገፋበትም ሕዝቅያስ ይሖዋን መታዘዙን ቀጠለ። ይህን ማድረግ ለሕዝቅያስ ቀላል የነበረ ይመስልሃል?​— ከባድ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። ይሁንና ሕዝቅያስ ተስፋ አልቆረጠም! ሕዝቅያስ ከይሖዋ ጋር መጣበቅ የቻለው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም የእሱን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደምንችል እስቲ እንመልከት።

ሕዝቅያስ ከይሖዋ ጋር ስለተጣበቁ ሌሎች ሰዎች ተምሮ ነበር። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ ዳዊት ነው። ዳዊት የኖረው ሕዝቅያስ ከመወለዱ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ቢሆንም ሕዝቅያስ ከቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ዳዊት መማር ይችል ነበር። ዳዊት “አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር ይቀበለኛል” በማለት ጽፏል።

ዳዊት ይሖዋን እንዲታዘዝ የረዳው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?​— እምነቱ ነው! ዳዊት ታዛዥ ከሆነ ይሖዋ እንደሚረዳው እርግጠኛ ነበር። ዳዊት በዚህ ረገድ ምንም ጥርጣሬ አልነበረውም! ሕዝቅያስ ስለ ዳዊት ማሰቡ ይሖዋን በመታዘዝ ከእሱ ጋር እንዲጣበቅ ረድቶት እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው። አንተም ይሖዋን በመታዘዝ ከእሱ ጋር የምትጣበቅ ከሆነ ይሖዋ እንደሚረዳህ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ።

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ይሁንና አባትህ ወይም እናትህ ይሖዋን የማያመልኩ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ?​— አምላክ፣ ልጆች ወላጆቻቸውን መታዘዝ እንዳለባቸው ተናግሯል። ስለዚህ አንተም ወላጆችህን መታዘዝ አለብህ። ይሁን እንጂ ወላጆችህ አምላክ እንዳታደርግ ያዘዘህን ነገር እንድታደርግ ቢነግሩህ፣ ይህን ነገር ማድረግ የሌለብህ ለምን እንደሆነ ልታስረዳቸው ትችላለህ። ማንም ቢያዝህ መዋሸት፣ መስረቅ ወይም ሌሎች አምላክ የሚከለክላቸውን ድርጊቶች መፈጸም የለብህም። አምላክን መታዘዝህ ተገቢ ነው!

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በዚህ ረገድ ልንከተላቸው የምንችላቸው ጥሩ ምሳሌዎች አሉ። ሕዝቅያስ የዳዊት ብቻ ሳይሆን የአያቱ የኢዮአታም ምሳሌም ጠቅሞታል። ኢዮአታም የሞተው ሕዝቅያስ ከመወለዱ በፊት ቢሆንም ሕዝቅያስ ስለ እሱ ማወቅ ይችል ነበር፤ እኛም በዛሬው ጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብዙ ነገር መማር እንችላለን። ልንከተላቸው የምንችላቸው ሌሎች ጥሩ ምሳሌዎችን ማስታወስ ትችላለህ?​—

እርግጥ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው እንደ ሕዝቅያስ፣ ዳዊት እና ኢዮአታም ያሉ ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች አንዳንድ ስህተቶችን ሠርተዋል። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ይሖዋን ይወዱ የነበረ ከመሆኑም ሌላ ስህተታቸውን አምነው ተቀብለዋል፤ እንዲሁም ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ጥረት አድርገዋል። ፍጹም ሰው የነበረው፣ የአምላክ ልጅ ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አስታውስ። ስለዚህ ስለ እሱ በማጥናት ምሳሌውን ለመከተል ጥረት እናድርግ።

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ

  • 2 ነገሥት 18:6⁠ን፤ 2 ዜና መዋዕል 28:1-3⁠ን

  • መዝሙር 27:10⁠ን፤ ኤፌሶን 6:1⁠ን፤ ቆላስይስ 3:20⁠ን

  • 2 ዜና መዋዕል 27:1, 2⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 2:21⁠ን አንብብ።

a ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ