የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 6/1 ገጽ 4
  • ፍጻሜያቸውን ያገኙ ትንቢቶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፍጻሜያቸውን ያገኙ ትንቢቶች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዓለምን የሚገዛው ማን ይሆን?
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ​—ክፍል 5
    ንቁ!—2011
  • አምላክ ለዘመናችን ያስነገረውን ትንቢታዊ ቃል በትኩረት ተከታተል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ፍጻሜያቸውን ያገኙ ትንቢቶች
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 6/1 ገጽ 4

ፍጻሜያቸውን ያገኙ ትንቢቶች

“አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ተስፋ . . . አንዱም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።”​—ኢያሱ 23:14

መጽሐፍ ቅዱስን የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው? በጥንት ዘመን የነበሩ ጠቢባን የሚናገሯቸው ትንቢቶች የተድበሰበሱና አስተማማኝ ያልሆኑ እንደነበሩ የታወቀ ነው፤ ዘመናዊው ኮኮብ ቆጠራም ቢሆን ከዚህ የተሻለ አይደለም። ፊውቸሮሎጂ ማለትም ባሉት ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተንተርሶ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ለመተንበይ ሙከራ የሚደረግበት መስክም ቢሆን ከዘመናት በኋላ ስለሚፈጸሙ ነገሮች በዝርዝር አይናገርም። ከዚህ በተቃራኒ ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ‘ገና የሚመጣውን ከጥንቱ’ የሚናገሩ ቢሆንም እንኳ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚገልጹ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ትክክለኛ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ።​—ኢሳይያስ 46:10

ምሳሌ፦ በስድስተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነቢዩ ዳንኤል የሜዶ ፋርስ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ በግሪክ እጅ እንደሚወድቅ በራእይ ተመልክቶ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ድል አድራጊው የግሪክ ንጉሥ “በኀይሉ በበረታ ጊዜ” መንግሥቱ ‘እንደሚሰበር’ ወይም እንደሚበታተን ተንብዮ ነበር። ታዲያ ማን ይተካዋል? ዳንኤል ‘ከመንግሥቱ አራት መንግሥታት ይወጣሉ፤ ነገር ግን በኀይል አይተካከሉትም’ በማለት ጽፏል።​—ዳንኤል 8:5-8, 20-22

የታሪክ ምሁራን ምን ይላሉ? ዳንኤል ከኖረበት ዘመን ከ200 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ ታላቁ እስክንድር የግሪክ ንጉሥ ሆነ። እስክንድር በአሥር ዓመታት ውስጥ የሜዶ ፋርስን መንግሥት ድል በመንሳት የግሪክ ግዛት እስከ ኢንደስ ወንዝ (በዘመናችን ፓኪስታን ውስጥ ይገኛል) ድረስ እንዲስፋፋ አደረገ። ይሁንና እስክንድር በ32 ዓመቱ በድንገት ሞተ። በትንሿ እስያ በምትገኘው በኢፕሰስ አቅራቢያ በተደረገ ጦርነት ደግሞ ግዛቱ ተበታተነ። በዚህ ውጊያ ላይ ያሸነፉት አራቱ ድል አድራጊዎች ከጊዜ በኋላ የግሪክን ግዛት ተከፋፈሉት። ይሁንና አንዳቸውም ቢሆኑ የእስክንድርን ያህል ኃያል መሆን አልቻሉም።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የያዛቸው ትንቢቶች ሁልጊዜ ፍጻሜያቸውን እንዳገኙ ሊነገርለት የሚችል ሌላ መጽሐፍ አለ? ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ የሆነ መጽሐፍ ነው?

“የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች . . . እጅግ በጣም ብዙ በመሆናቸው ፍጻሜያቸውን ያገኙት በአጋጣሚ ነው ማለት ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው።”​—ኤ ሎየር ኤግዛምንስ ዘ ባይብል፣ በኧርወን ሊንተን

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ