የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 11/1 ገጽ 6-7
  • ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሙታን የት ናቸው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • “ሞት በድል ተዋጠ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?
    እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 11/1 ገጽ 6-7

ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?

ሮማን የቅርብ ጓደኛውን በመኪና አደጋ ያጣው ትንሽ ልጅ እያለ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ጓደኛዬን ማጣቴ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ ትቷል። ‘ስንሞት ምን እንሆናለን?’ የሚለው ጉዳይ ከአደጋው በኋላ ለበርካታ ዓመታት ያሳስበኝ ነበር።”

ይህ ጥያቄ የሚነሳው ለምንድን ነው?

የሰው ልጆች ሞት ተፈጥሯዊ ነገር እንደሆነ አይሰማንም። በየትኛውም ዕድሜ ላይ ብንገኝ አብዛኛውን ጊዜ መሞት አንፈልግም። ብዙዎች ‘ከሞት በኋላ ምን እንሆናለን?’ የሚለው ነገር ያስፈራቸዋል።

አንዳንዶች ምን መልስ ይሰጣሉ?

ብዙዎች፣ ሰው ሲሞት ከግለሰቡ ተለይታ መኖሯን የምትቀጥል ነገር እንዳለች ያምናሉ። ጥሩ ሰዎች በሰማይ ሽልማት ሲያገኙ መጥፎ ሰዎች ደግሞ ለሠሩት ኃጢአት ለዘላለም ቅጣታቸውን እንደሚቀበሉ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ሰው ሲሞት ከሕልውና ውጭ እንደሚሆንና ውሎ አድሮም ሙሉ በሙሉ ተረስቶ እንደሚቀር ያስባሉ።

መልሳቸው ምን አንድምታ አለው?

የመጀመሪያው መልስ፣ ሰው ሲሞት ሙሉ በሙሉ ከሕልውና ውጭ አይሆንም የሚል አንድምታ አለው። ሁለተኛው መልስ ደግሞ፣ ሕይወት ምንም ዓላማ የለውም የሚል ሐሳብ ያስተላልፋል። ሕይወት ዓላማ እንደሌለው የሚያምኑ ሰዎች “ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ” የሚለው ዓይነት አሉታዊ አመለካከት ሊያዳብሩ ይችላሉ።—1 ቆሮንቶስ 15:32

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰው ሲሞት ከግለሰቡ ተለይታ መኖሯን የምትቀጥል ነገር እንዳለች አያስተምርም። ንጉሥ ሰሎሞን በአምላክ መንፈስ መሪነት እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም።” (መክብብ 9:5) ‘ምንም የማያውቁ’ ሰዎች በዙሪያቸው ስለሚከናወነው ነገር ምንም ዓይነት ግንዛቤ የላቸውም። ስሜት ሊኖራቸው የማይችል ከመሆኑም በላይ ምንም ነገር መሥራት አይችሉም። በመሆኑም ሙታን በሕይወት ያሉ ሰዎችን መርዳትም ሆነ መጉዳት አይችሉም።

ብዙዎች ከሚያምኑት በተቃራኒ አምላክ ሰዎች እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። የመጀመሪያውን ሰው አዳምን የፈጠረው በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖር አስቦ ነው። አምላክ ስለ ሞት የጠቀሰው፣ አለመታዘዝ የሚያስከትለውን ቅጣት ለአዳም በነገረው ጊዜ ብቻ ነው። አዳም የአንድን ዛፍ ፍሬ እንዳይበላ የተከለከለ ሲሆን ፍሬውን ከበላ “በእርግጥ ትሞታለህ” ተብሎ ነበር። (ዘፍጥረት 2:17) አዳምና ሔዋን ታዛዦች ሆነው ቢቀጥሉ ኖሮ እነሱም ሆኑ ለአምላክ ታማኝ የሆኑ ዘሮቻቸው በሙሉ በምድር ላይ ለዘላለም በኖሩ ነበር።

አዳም አምላክ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሆን ብሎ ጣሰ። የአምላክን ትእዛዝ በጣሰ ጊዜ ኃጢአት ስለሠራ ሞተ። (ሮም 6:23) አዳም ሲሞት ከአካሉ ተለይታ በሕይወት መኖሯን የቀጠለች ነገር የለችም። ከዚህ ይልቅ አዳም ሲሞት ሕልውናው አከተመ። አምላክ ለአዳም እንዲህ ብሎት ነበር፦ “ከምድር ስለ ተገኘህ፣ ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።” (ዘፍጥረት 3:19) የሰው ዘር በሙሉ የተገኘው ከአዳም በመሆኑ ሁላችንም ኃጢአትንና ሞትን ከእሱ ወርሰናል።—ሮም 5:12

አዳም ታዛዥ ባይሆንም እንኳ አምላክ ምድርን ፍጹማን በሆኑ የአዳም ዝርያዎች ለመሙላት የነበረውን ዓላማ መፈጸሙ አይቀርም። (ዘፍጥረት 1:28፤ ኢሳይያስ 55:11) በቅርቡ ይሖዋ ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኞቹን ያስነሳቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚያ ጊዜ ሲናገር “ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት [ይነሳሉ]” ብሏል።—የሐዋርያት ሥራ 24:15

ቀደም ሲል የተጠቀሰው ሮማን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞትና ስለ ይሖዋ አምላክ ምን እንደሚል ተማረ። ያወቀው ነገርም በሕይወቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። የእሱን ታሪክ “መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል” በሚለው ርዕስ ላይ ማግኘት ትችላለህ።

ሰው ሲሞት ምን እንደሚሆን ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 6 ተመልከት። ይህን መጽሐፍ www.jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይም ማግኘት ይቻላል

ኢየሱስ ስለ ሞት ምን ብሏል?

ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩት የሃይማኖት መሪዎች በሚያስፋፉት የሙታን “ትንሣኤ የለም” በሚለው ሐሳብ አልተስማማም። (ሉቃስ 20:27) በሌላ በኩል ደግሞ ሰው ሲሞት ከግለሰቡ ተለይታ መኖሯን የምትቀጥል ነገር እንዳለች አላስተማረም። ኢየሱስ ያስተማረው ከዚህ በታች የቀረቡትን ሐሳቦች ነው።

ሞት እንደ እንቅልፍ ነው። ኢየሱስ፣ ወዳጁ አልዓዛር በሞተ ጊዜ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ከእንቅልፍ ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” ብሎ ነበር። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ይህን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ በወቅቱ አልገባቸውም። በመሆኑም “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶ ከሆነ ይሻለዋል” አሉት። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንዲህ ይላል፦ “እርግጥ ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው ስለመሞቱ ነው። እነሱ ግን ለማረፍ ብሎ እንቅልፍ ስለመተኛቱ የተናገረ መሰላቸው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ እንዲህ አላቸው፦ ‘አልዓዛር ሞቷል።’”—ዮሐንስ 11:11-14

ሙታን ይነሳሉ። ኢየሱስ ወደ አልዓዛር መንደር ሲደርስ የአልዓዛርን እህት ማርታን “ወንድምሽ ይነሳል” በማለት አጽናናት። ከዚያም ኢየሱስ የሚከተለውን አስገራሚ ተስፋ ሰጠ፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። በእኔ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል።” ኢየሱስ የሰጠው ተስፋ የሕልም እንጀራ አይደለም። አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን ቢሆነውም ኢየሱስ በብዙ ሰዎች ፊት አስነስቶታል።—ዮሐንስ 11:23, 25, 38-45

ኢየሱስ ለሐዋርያው ዮሐንስ በሰጠው ራእይ ላይም ሙታን እንደሚነሱ በድጋሚ ቃል ገብቷል። በምሳሌያዊ ሁኔታ የሞት ምርኮኞች የሆኑ ሁሉ ወደፊት ነፃ እንደሚወጡ ኢየሱስ ገልጿል።—ራእይ 20:13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ