የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 11/15 ገጽ 20
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ነጠላነት አሳብ ሳይከፋፈል ለማገልገል የሚያስችል አጋጣሚ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • “ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ነጠላነታችሁን በጥበብ ተጠቀሙበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • በይሖዋ አገልግሎት ደስተኛ የሆኑ ያላገቡ ክርስቲያኖች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 11/15 ገጽ 20

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ በ⁠ማቴዎስ 19:10-12 ላይ የተናገረው ሐሳብ ነጠላ ሆነው ለመኖር የሚመርጡ ሰዎች የነጠላነት ስጦታን በተአምራዊ መንገድ እንዳገኙ ይጠቁማል?

ኢየሱስ ስለ ነጠላነት ሲናገር የነበረውን ሁኔታ እንመልከት። ኢየሱስ፣ ፈሪሳውያን ወደ እሱ መጥተው ከፍቺ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲያቀርቡለት ይሖዋ ስለ ትዳር ያለውን አመለካከት በግልጽ ነገራቸው። ሕጉ አንድ ወንድ በሚስቱ ላይ “አሳፋሪ ነገር” ካገኘባት የፍቺ ወረቀት ጽፎ እንዲሰጣት ይፈቅድ የነበረ ቢሆንም ይህ ከመጀመሪያው አንስቶ የተፈቀደ ነገር አልነበረም። (ዘዳ. 24:1, 2) በመሆኑም ኢየሱስ “በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ምንዝር ይፈጽማል” ሲል ተናገረ።—ማቴ. 19:3-9

ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲሰሙ “በባልና በሚስት መካከል ያለው ሁኔታ እንዲህ ከሆነስ አለማግባት ይመረጣል” አሉ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ስጦታው ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር ይህን ሁሉም ሰው ሊቀበለው አይችልም። ምክንያቱም ገና ከእናታቸው ማህፀን ጀምሮ ጃንደረባ ሆነው የሚወለዱ አሉ፤ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦችም አሉ፤ እንዲሁም ለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ጃንደረቦችም አሉ። ይህን ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።”—ማቴ. 19:10-12

ሰዎች ቃል በቃል ጃንደረባ የሚሆኑት እክል ኖሮባቸው በመወለዳቸው ወይም በአደጋ ሳቢያ አሊያም ተሰልበው ሊሆን ይችላል። ይሁንና በራሳቸው ምርጫ ጃንደረባ የሆኑም አሉ። እነዚህ ሰዎች ማግባት የሚችሉ ቢሆንም “ለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ” ራሳቸውን ገዝተው ነጠላ ሆነው ይኖራሉ። እንደ ኢየሱስ ነጠላ ሆነው ለመኖር የመረጡት በመንግሥቱ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ለመካፈል ሲሉ ነው። እነዚህ ሰዎች የነጠላነት ስጦታን ይዘው አልተወለዱም፤ ወይም እንዲህ ያለ ስጦታ አልተሰጣቸውም። ከዚህ ይልቅ ነጠላ ሆኖ መኖርን እንደ ስጦታ አድርገው ተቀብለውታል፤ በሌላ አባባል ነጠላ ሆነው ለመኖር መርጠዋል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ በተናገረው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ነጠላ የሆኑትም ሆኑ ያገቡ ክርስቲያኖች በሙሉ አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማገልገል እንደሚችሉ ገልጿል፤ አክሎም ነጠላ ሆነው ለመኖር ‘በልባቸው የቆረጡ’ ሰዎች ‘የተሻለ እንደሚያደርጉ’ ተናግሯል። እንዴት? ያገቡ ሰዎች ለጌታ አገልግሎት ከሚያውሉት ጊዜና ኃይል ከፍለው የትዳር ጓደኛቸውን ለማስደሰትና ለመንከባከብ ማዋል ይጠበቅባቸዋል። በሌላ በኩል ነጠላ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ ኃላፊነት ስለሌለባቸው ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለጌታ አገልግሎት ማዋል ይችላሉ። በመሆኑም ይህን አጋጣሚ ከአምላክ እንዳገኙት “ስጦታ” አድርገው ይቆጥሩታል።—1 ቆሮ. 7:7, 32-38

ትዳር ያልመሠረቱ ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች አገልግሎት ላይ

ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚናገሩት አንድ ክርስቲያን የነጠላነት ስጦታን ተአምራዊ በሆነ መንገድ አያገኝም። ከዚህ ይልቅ ነጠላነት ትኩረቱ ሳይከፋፈል ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማስቀደም እንዲችል ሳያገባ በመኖር የሚያዳብረው ነገር ነው። በዛሬው ጊዜ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ለመንግሥቱ ሲሉ ነጠላ ሆነው ለመኖር በልባቸው ቆርጠዋል፤ ሌሎች ደግሞ ለእነሱ የብርታት ምንጭ ሊሆኑላቸው ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ