የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 1/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ስም
    ንቁ!—2017
  • በአምላክ ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አምላክ ስም አለው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የአምላክን ስም ታውቀዋለህ? በስሙስ ትጠቀማለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 1/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የአምላክ ስም ማን ነው?

የቤተሰባችን አባላት በሙሉ የየራሳቸው ስም አላቸው። የቤት እንስሶች እንኳ ስም ይወጣላቸዋል! ታዲያ አምላክስ ስም ያለው መሆኑ ምክንያታዊ አይደለም? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ በርካታ የማዕረግ ስሞች እንዳሉት ተጠቅሷል፤ ከእነዚህም መካከል ኤልሻዳይ፣ ሉዓላዊ ጌታ፣ ፈጣሪ እና ሌሎችም ይገኙበታል። ይሁንና አምላክ የራሱ መጠሪያ ስም አለው።—ዘፀአት 6:3ን አንብብ።

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በ⁠መዝሙር 83:18 ላይ የአምላክን የግል ስም አስፍረዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም (እንግሊዝኛ) ላይ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “ይህም ሰዎች፣ ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ በመላው ምድር ላይ አንተ ብቻ ከሁሉ በላይ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ነው።”

በአምላክ ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የቅርብ ጓደኞቻችንን ጨምሮ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ስናወራ የምናነጋግራቸው ስማቸውን እየጠራን ነው

አምላክ በግል ስሙ እንድንጠቀም ይፈልጋል። የቅርብ ጓደኞቻችንን ጨምሮ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ስናወራ የምናነጋግራቸው ስማቸውን እየጠራን ነው። ከአምላክ ጋር ስንነጋገርስ እንዲህ ማድረግ አይኖርብንም? ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ ስም እንድንጠቀም አበረታትቶናል።—ማቴዎስ 6:9ን እና ዮሐንስ 17:26ን አንብብ።

ይሁን እንጂ የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ስሙን ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ ስለ አምላክ ማንነት እንዲሁም ወደ እሱ መቅረብ ይቻል እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ስለ እነዚህ ጉዳዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ማግኘት ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ