የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 2/15 ገጽ 30
  • የቀያፋ ቤተሰብ የሆነች ሴት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የቀያፋ ቤተሰብ የሆነች ሴት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ በምድር ላይ እንደኖረ የሚያረጋግጥ የአርኪኦሎጂ ማስረጃ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • በኢየሱስ ላይ ሞት የፈረደበት ሊቀ ካህን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • አልዓዛር ከሞት ሲነሣ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 2/15 ገጽ 30

የቀያፋ ቤተሰብ የሆነች ሴት

[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የአፅም ማስቀመጫ ሣጥኖች ማከማቻ

አርኪኦሎጂያዊ ግኝቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ አንድ ባለታሪክ በእርግጥ በሕይወት እንደኖረ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያረጋግጡበት ጊዜ አለ። በ2011 የእስራኤል ምሁራን ያሳተሙት መረጃ ለዚህ እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል። ምሁራኑ፣ የሞተ ሰው በድን ከበሰበሰ በኋላ አፅሙ ተሰብስቦ የሚቀመጥበት ሣጥን አግኝተዋል፤ የ2,000 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ ሣጥን በሚያምር መንገድ ከኖራ የተሠራ ነው።

[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በዚህ ሣጥን ላይ “ከቤት ኣምሪ የመዓዝያ ክህነት ምድብ፣ የቀያፋ ልጅ የሆነው የየሹዋ ሴት ልጅ ሚርያም” የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል። ቀያፋ ኢየሱስን ለፍርድ እንዳቀረበውና እንዳስገደለው የተገለጸው የአይሁድ ሊቀ ካህናት ነው። (ዮሐ. 11:48-50) ታሪክ ጸሐፊው ፍላቪየስ ጆሴፈስ ስለዚህ ሰው ሲናገር “ቀያፋ የሚባለው ዮሴፍ” ብሏል። ይህ የአፅም ማስቀመጫ ሣጥን ከእሱ የቅርብ ዘመዶች መካከል የአንዷ ሳይሆን አይቀርም። ከዚህ ቀደም በተገኘና የሊቀ ካህናቱ እንደሆነ በሚታመን የአፅም ማስቀመጫ ሣጥን ላይ የሆሴፍ ባር ኬያፋ ወይም የቀያፋ ልጅ ዮሴፍa የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል፤ በመሆኑም ሚርያም የቀያፋ ዘመድ ነች።

የእስራኤል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ባወጣው መረጃ መሠረት የሚርያም አፅም የተቀመጠበት ሣጥን የተገኘው አንድን ጥንታዊ የመቃብር ቦታ በዘረፉ ሌቦች እጅ ነው። በዚህ ጥንታዊ ሣጥንና በላዩ በተቀረጸበት ጽሑፍ ላይ የተደረገው ምርምር እንደሚያሳየው ሣጥኑ ላይ ያለው መረጃ ትክክለኛ ነው።

የሚርያም አፅም የተቀመጠበት ሣጥን ሌላም አዲስ መረጃ ይዟል። ሣጥኑ ላይ “መዓዝያ” የሚል ጽሑፍ የሚገኝ ሲሆን ይህም በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስ በ24 ምድብ ተከፋፍለው በዙር ያገለግሉ ከነበሩት የካህናት ቡድኖች የመጨረሻው ምድብ ነው። (1 ዜና 24:18) በዚህ ሣጥን ላይ የተቀረጸው ጽሑፍ “የቀያፋ ቤተሰብ ከመዓዝያ ምድብ እንደነበረ” የሚጠቁም መሆኑን የእስራኤል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ተናግሯል።

በተጨማሪም በሣጥኑ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍ ቤት ኣምሪን ይጠቅሳል። ይህ ሐሳብ ምን እንደሚያመለክት ሁለት ድምዳሜዎች ላይ መድረስ ይቻላል። የእስራኤል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲህ ይላል፦ “በአንድ በኩል፣ ቤት ኣምሪ የአንድ ካህን ቤተሰብ ይኸውም የኢሜር ልጆች (ዕዝራ 2:36, 37፤ ነህ. 7:39-42) መጠሪያ ሊሆን ይችላል፤ ከኢሜር ልጆች ዘሮች መካከል የመዓዝያ ምድብ አባላት የሆኑ ካህናት ይገኙበታል።” ባለሥልጣኑ አክሎ እንዲህ ብሏል፦ “ሌላው አማራጭ ደግሞ [ቤት ኣምሪ] የሟቿን ወይም የመላው ቤተሰቧን የትውልድ ሥፍራ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል የሚል ነው።” በዚያም ሆነ በዚህ የሚርያም አፅም ያለበት ሣጥን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በታሪክ ውስጥ በእርግጥ የነበሩ እንደሆኑ ያረጋግጣል።

a የቀያፋ አፅም የተቀመጠበትን ሣጥን በተመለከተ በጥር 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 10-13 ላይ የሚገኘውን “በኢየሱስ ላይ ሞት የፈረደበት ሊቀ ካህን” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ