የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 6/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እውነተኛ ሰላም—ከየት ይገኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • “የአምላክ ሰላም” ልባችሁን ይጠብቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ሰዎች በሰላም መኖር ያቃታቸው ለምን ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • እውነተኛውን ሰላም ፈልጉ፣ ተከተሉትም!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 6/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ዓለም አቀፍ ሰላም የሕልም እንጀራ ሆኖ የቀረው ለምንድን ነው?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ዓለም አቀፍ ሰላም ማምጣት የሚችለው የሰዎችን ልብ መለወጥ የሚችል መንግሥት ብቻ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶችን ይጠቅሳል። አንደኛው፣ የሰው ልጆች ድንቅ ነገሮችን ያከናወኑ ቢሆንም ራሳቸውን የመምራት ችሎታ አልተሰጣቸውም። ሁለተኛው፣ “መላው ዓለም በክፉው ኃይል” ማለትም በሰይጣን ዲያብሎስ ሥር ስለሆነ ሰዎች የሚያቅዱት ነገር አይሳካም። በመሆኑም የሰዎች ጥረት ዓለም አቀፍ ሰላም ማስገኘት አልቻለም።—ኤርምያስ 10:23⁠ን እና 1 ዮሐንስ 5:19⁠ን አንብብ።

በተጨማሪም ሰዎች ራስ ወዳድና የሥልጣን ጥም የተጠናወታቸው በመሆናቸው ዓለም አቀፍ ሰላም የሕልም እንጀራ እንደሆነ ቀርቷል። በዓለም ላይ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ሰዎች መልካም የሆነውን እንዲወዱና ለሌላው አሳቢነት እንዲያሳዩ የሚያስተምር ዓለም አቀፍ መንግሥት ከተቋቋመ ብቻ ነው።—ኢሳይያስ 32:17⁠ን እና 48:18, 22⁠ን አንብብ።

በምድር ላይ ሰላምን የሚያሰፍነው ማን ነው?

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መላውን የሰው ዘር የሚገዛ አንድ መንግሥት እንደሚያቋቁም ቃል ገብቷል። ይህ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታትን ይተካል። (ዳንኤል 2:44) የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ የሰላም ልዑል በመሆን ይገዛል። ከምድር ላይ ክፋትን ጠራርጎ የሚያስወግድ ከመሆኑም ሌላ ለሰዎች የሰላምን መንገድ ያስተምራል።—ኢሳይያስ 9:6, 7⁠ን እና 11:4, 9⁠ን አንብብ።

ዛሬም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ አመራር ሥር ሆነው፣ ከሌሎች ጋር እንዴት በሰላም መኖር እንደሚቻል የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ለሰዎች እያስተማሩ ነው። በቅርቡ ደግሞ ዓለም አቀፍ ሰላም እውን ይሆናል።—ኢሳይያስ 2:3, 4⁠ን እና 54:13⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ