የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 8/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • መልስ የሚያገኙት የእነማን ጸሎቶች ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • መጸለይ የሚፈይደው ነገር አለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 8/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

አምላክ ሁሉንም ጸሎቶች ይሰማል?

አምላክ፣ ከየትኛውም ብሔር ቢሆኑ ሰዎች የሚያቀርቡትን ጸሎት ይሰማል። (መዝሙር 145:18, 19) ስለሚያሳስበን ማንኛውም ጉዳይ እንድንጸልይ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ያበረታታናል። (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) ሆኖም አንዳንድ ጸሎቶች አምላክን አያስደስቱትም። ለምሳሌ ያህል፣ የተሸመደዱ ጸሎቶችን ደጋግሞ ማቅረብ አምላክን አያስደስተውም።—ማቴዎስ 6:7⁠ን አንብብ።

በተጨማሪም ይሖዋ ሆን ብለው ሕጎቹን ችላ የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቧቸውን ጸሎቶች ይጠላል። (ምሳሌ 28:9) ለምሳሌ ያህል፣ በጥንት ዘመን ነፍስ በማጥፋት ተጠያቂ የነበሩት እስራኤላውያን ያቀረቧቸውን ጸሎቶች ለመስማት ፈቃደኛ አልነበረም። ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ጸሎታችን በአምላክ ዘንድ ተሰሚነት እንዲያገኝ ልናሟላቸው የሚገቡ የተወሰኑ መሥፈርቶች አሉ።—ኢሳይያስ 1:15⁠ን አንብብ።

አምላክ ጸሎታችንን እንዲሰማ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ያለ እምነት ወደ አምላክ በጸሎት መቅረብ አንችልም። (ያዕቆብ 1:5, 6) አምላክ እንዳለና እንደሚያስብልን እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት እምነታችንን ማጠናከር እንችላለን፤ ምክንያቱም እውነተኛ እምነት በማስረጃና አምላክ በቃሉ ውስጥ ዋስትና በሰጠባቸው ተስፋዎች ላይ የተመሠረተ ነው።—ዕብራውያን 11:1, 6⁠ን አንብብ።

የልባችንን አውጥተን በትሕትና መጸለይ ይኖርብናል። የአምላክ ልጅ ኢየሱስም እንኳ ይጸልይ የነበረው በትሕትና ነበር። (ሉቃስ 22:41, 42) በመሆኑም አምላክ ምን ማድረግ እንዳለበት እኛ ለእሱ ከመንገር ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ መሥፈርቶቹን ለመረዳት መጣር ይኖርብናል። ከዚያም ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ መጸለይ እንችላለን።—1 ዮሐንስ 5:14⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 17 ተመልከት

www.jw.org/am ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ