የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 9/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መንፈሳዊ ፍጥረታት ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • መላእክት በሕይወታችን ውስጥ ምን ሚና ይጫወታሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 9/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መላእክት ሊረዱን ይችላሉ?

ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ሳለ አንድ መልአክ ከጉዳት ሲጠብቀው

መላእክት በጥንት ጊዜ የአምላክ ታማኝ አገልጋይ የነበረውን ዳንኤልን እንደረዱት ሁሉ በዛሬው ጊዜም ሰዎች ምሥራቹ እንዲደርሳቸው ይረዳሉ

ይሖዋ አምላክ ሰዎችን ከመፍጠሩ ከረጅም ጊዜ በፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ መላእክትን ፈጥሯል። (ኢዮብ 38:4, 7) እነዚህ መላእክት አምላክን የሚያገለግሉ ኃያል መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ አምላክ በምድር ላይ ላሉ አገልጋዮቹ መመሪያ ለመስጠትና ጥበቃ ለማድረግ መላእክትን ይልካል። (መዝሙር 91:10, 11) በዛሬው ጊዜ መላእክት፣ የኢየሱስ ተከታዮች የሚሰብኩት ምሥራች ለሰዎች እንዲደርስ እርዳታ ያደርጋሉ።—ራእይ 14:6, 7⁠ን አንብብ።

መላእክት እንዲረዱን ወደ እነሱ መጸለይ ይኖርብናል? አይኖርብንም። ጸሎት አምልኮ ስለሆነ ሊቀርብ የሚገባው ለአምላክ ብቻ ነው። (ራእይ 19:10) ደግሞም መላእክት የአምላክ አገልጋዮች ስለሆኑ የሚሰሙት አምላክን እንጂ ሰዎችን አይደለም። በመሆኑም ምንጊዜም ጸሎታችንን በኢየሱስ በኩል ወደ አምላክ ብቻ ማቅረብ ይኖርብናል።—መዝሙር 103:20, 21፤ ማቴዎስ 26:53⁠ን አንብብ።

መጥፎ መላእክት አሉ?

እንደ ሰዎች ሁሉ መላእክትም የተፈጠሩት የመምረጥ ነፃነት እንዲኖራቸው ተደርገው ነው፤ በመሆኑም ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ነገር ለማድረግ መምረጥ ይችላሉ። የሚያሳዝነው ነገር፣ ብዙ መላእክት በአምላክ ላይ ዓመፁ። (2 ጴጥሮስ 2:4) መጀመሪያ ያመፀው ሰይጣን ነው፤ ከዚያም ሌሎች መላእክት እንደ እሱ በማመፅ አጋንንት ሆነዋል። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ሰይጣንና አጋንንቱ ከሰማይ ተባርረው ወደ ምድር ተጥለዋል።—ራእይ 12:7-9⁠ን አንብብ።

ከ1914 ወዲህ ክፋትና ዓመፅ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አምላክ በቅርቡ የሰይጣንንና የአጋንንቱን እንቅስቃሴ እንደሚያስቆም ያመለክታል። ከዚያም አምላክ መጀመሪያ ለምድር ያወጣው ዓላማ ይፈጸማል።—ራእይ 12:12፤ 21:3, 4⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ